የውጭ የደህንነት ተቋማት በአንድ ሀገር ውስጥ ወደፊት ስልጣን ወይም ተፅዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ ወጣቶችን ገና በለጋ እድሜያቸው የመመልመልና የራሳቸውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ግብ በሚያሳካ መልኩ ኮትኩቶ የማሳደግ ስልትን በስፋት ይተገብራሉ። ይህ ተግባር በዘርፉ "የልሂቃን ቀረጻ" (Elite Capture or Cultivation) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የተመረጡ ወጣቶችን የዓለም እይታ (Worldview) ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ የውጭ ሃገር ፍላጎትና ጥቅምን በሚያሳካ መልኩ አድርጎ መቅረጽ ነው። እነዚህ ተቋማት የአንድን ወጣት የወደፊት የመሪነት ዝንባሌ ቀድመው በመረዳት፣ በትምህርት እና በተለያዩ ስልጠናዎች ስም ከሀገሩ በማውጣት የአስተሳሰብ አድማሱን በእነሱ የፍላጎት ልክ ይቀርፁታል። ይህ "Formative age" ወይም የማንነት ቀረጻ ምቹ እድሜ የአንድ ሰው ስብዕና እና … [Read more...] about የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ
Opinions
የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር
ጎንደር ወዴየት እየሄደች ነው? ጎንደር እስከመቼ በውሸት ሪፖርት ትደበቃለች? መቼ ነው በጎንደር የጃኖ ስጦታ እና የዶሮ ፖለቲካ የተሸፈነችበት ጭምብል የሚገለጠው? ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ ያሻዋል። የጎንደር የፖለቲካ አመራር ራሳቸውን ለሥራ ያተጉ፣ ተግባራቸውን በወቅቱ የሚከወኑ ለመምሰል የሚያሳዩትን ድራማ እስከመቼ ነው የሚገፉበት? እስከመቼ ነው ዝምስ የሚባሉት? ጎንደር ለሚመጡ ባለሥልጣናት የባሕል አልባሳትን በማልበስና የጎንደርን ዶሮ በመጋብዝ ታታሪ መምሰል፣ ከዚያም በላይ “ወደ ቤት የምትወሰዱት” በማለት በአገልግል ዶሮ፣ በጀሪካ ቅቤና ማር እየሞሉ ውለታ ማስቀመጥ ፖለቲካ ሳይሆን፣ አድሮ መንግሥትን ዋጋ የማስከፈል ጉዳይ እንደሆነ እንዴት ይዘነጋል? መቼ ነው የጎንደር ባለሥልጣናት ከጃኖ ስጦታና አገልግል ቋጠራ የውለታ ፖለቲካ በመውጣት የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ በቅጡ … [Read more...] about የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር
“አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ ሪዞርት ሽንት ቤት ውስጥ አሳማ ያስቀምጣል። አሳማዋንም የከንፈር ቀለም (ሊፕስቲክ) ቀብቶ እንደ ሰው አስመስሎ። ዓላማው ሌላ ሳይሆን ፕራንክ ነበር። ክስተቱ የሪዞርቱን ባለቤት ፕራንክ አድርጎ ቢያልፍም ከዚያ በኋላ ግን አሳማ የከንፈር ቀለም ቢቀባ እንደ አሳማ መጮኹ (ኦይንክ ማድረጉ)፣ ጭቃ ላይ መንከባለሉ፣ አሰሱንም ገሰሱንም መብላቱ፣ … ባጠቃላይ አሳማነቱ አይቀርም ማለት ነው በሚል አባባል ተተካ። ከዚያም በ90ዎቹ ለቴክሳስ ሀገረግዢነት ይወዳደሩ የነበሩት አን ሪቻርድስ አባባሉን ተጠቀሙበት። ትልቁ ቡሽ በምርጫ ውድድር በነበሩበት ጊዜ የቡሽ አስተዳደር ለውጥ እንደማያመጣ አን ሲናገሩ “ዌል የአሳማዋን ከንፈር ሊፕስቲክ ቀብቶ ሞኒካ ነሽ ሊሏት ይቻላሉ፤ ግን አሳማነቷ ፈጽሞ አይቀየርም” ነበር … [Read more...] about “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
የተንጋደደው የገዱ መልስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀድሞ ጭፍራቸውን ገዱ አንዳርጋቸው በፓርላማ በስም ጠርተው ለተናገሩት ገዱ መልስ ሰጥተዋል። ይህ ጽሑፍ ዓላማ ያደረገው ለገዱ ምላሽ አስተያየት ለመስጠት አይደለም። ምክንያቱም የመጀመሪያና ትልቁ ስህተት ያለው ገዱ በጻፉት የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ ስለሆነ ነው። ያ ሳይስተካከል በገዱ ጽሑፍ ላይ ምንም ማለት አይቻልም። ገዱ የጠቅላዩን ንግግር የሰሙት እንዴት እንደሆነ ሲገልጹ “ሰዎች ቆርጠው በላኩልኝ የቪዲዮ ቅጂ” ነው ብለዋል። ገዱ የግል ታሪካቸው እንደሚያስረዳው “መጀመሪያ ዲግሪ” የያዙት በተለምዶ “የዲግሪ ወፍጮ” ወይም “ድንጋይ ማምረቻ” ከሚባለው ሲቪል ሰርቪስ “ዩኒቨርሲቲ” ነው። ሲቀጥል “ማስተርስ ዲግሪ” ከአዙዛ ነው። መቼም ስለ አዙዛ መናገር እዚህ ላይ አያስፈልግም። ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ግን ከሲቪል ሰርቪስም ሆነ ከአዙዛ የተመረቀ ሁሉ … [Read more...] about የተንጋደደው የገዱ መልስ
“ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ)
ልደቱ አያሌው ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር ያስተባበረው “አየር አንቀጥቅጥ” ትዕይንት ቅዳሜ ቀን ተካሂዷል። ልደቱ በስተመጨረሻ እንዳለው ከታሰበው በላይ የተሳካው የአየር ትዕይንት 15 ሰዎች ተናግረዋል፤ ሕዝብ በሳተላይት እና በተገኘው መንገድ ሁሉ ሰምቷል ብሏል። አገዛዙ ፈርቶ ኢንተርኔት አፍኗል፤ ዳታ ታቅቧል፤ ዩትዩብ እንዳይሠራ ተደርጓል ብለው ልደቱም፣ ቴዎድሮስም እየደጋገሙ ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህ የአየር ላይ ትዕይንት “ስልቴዎች” ማለትም ስብሃት፣ ልደቱ፣ ቴዎድሮስ በልዩ ሁኔታ የቀመሩትና ትህነግን በመታደግ ለሻዕቢያ የተሠራ ልዩ የስልቴዎች ስልት ነው። ንግግር ያደረጉት ሰዎች ጥቂቶቹን ስንቃኝ፤ … የድግሱ መሪ ቴዎድሮስ መደረጉ በራሱ ብዙ የሚለው ነገር አለ። ቴዎድሮስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወገኖቼን (የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ወያኔዎችን) የፈጀች ኢትዮጵያ ጥንቅር … [Read more...] about “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ)
በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ
መለስ ዜናዊ ከስሙ ጀምሮ ሁሉ ነገሩ የውሸት ወይም ፌክ ነው። ላደረሰብን ግፍ እንክሰሰው እንኳን ብንል በየትኛው ስሙ ነው ፍርድ ቤት የምናቆመው የነበረው? ደግነቱ ከዚህ ሁሉ በፊት ወደ ዕረፍቱ ሄዶ እኛንም አሳረፈን። መለስ የዕውቀት ችግር አልነበረውም፤ ዕድሜ ለኢትዮጵያ ከሥር መሠረቱ በነጻ አስተምራዋለች። ንጉሡም ሰው ነው፤ ነገ ሀገር ይጠቅማል ብለው ሸልመውታል ይባላል። ግን ያልታከመና ሥር የሰደደ የበታችነት ስሜት የነበረው፣ አስተሳሰቡ ደሃ የሆነ ሰው ነበር። በዚህ ደሃ አስተሳሰቡ ነበር ኢትዮጵያን ለመምራት ሥልጣን ኮርቻ ላይ የተፈናጠጠው። ሥልጣን፣ ሃብት፣ ድሎት፣ ወዘተ ቢመጣም አስተሳሰብ ደሃ ከሆነ ችግሩ ውስብስብና መፍትሔ ዓልባ ነው የሚሆነው። መለስ ኢትዮጵያን በጣም ነበር የሚጠላት፤ ለማፍረስ ይፈልግ ነበር ለማለት ብዙም አያስደፍርም። ነገርግን ልክ እንደ … [Read more...] about በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ
ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት”
የዛሬ አምስት ዓመት ግድም ነው። የሚያምሩ ሁለት ሸበቶ እናቶችን ጨምሮ ተገልጋዮች ይበላሉ። ይጠጣሉ። ያነሳቸውን ይጠይቃሉ። የወቅቱ የኢሳት ባልደረቦችም በአንድ ኮርነር ክብ ሰርተው የሚበላወንም የሚጠጣውንም በዓይነት ሤራ እያዋለዱ ይጠዘጥዛሉ። ቨርጂኒያ ዳማ ሆቴል!! በድንገት ሁለቱ ሸበቶ ሴቶች ይነሱና እንደ ብራቅ ይጮሃሉ። ክብ ሰርተው የሚመገቡትን የኢሳት የማታ ማታ ኮማንዶዎች እያመለከቱ እሳት ጎርሰው “አፈር ብሉ፣ እምዬ ማሪያም አፈር ታብላችሁ፤ ሕዝብ እያጫረሳችሁ እናንተ እዚህ ሥጋ ትቆርጣላችሁ። ደም ብሉ …. ” እናቶቹ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው “ያዙኝ ልቀቁኝ” አሉ። ወርውረው ለመማታት ገላጋዮችን ታገሉ። ተለምነው። ተገዝተው …. የገባቸው እናቶች። እንደ እኔ ያልደነዘዙ። “ሦስትን ወደ አራት” አስገራሚ ትርክት፣ አስገራሚ ሤራ ነው። ሤራው በርካቶችን የሰለበ … [Read more...] about ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት”
የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ?
ቴድሮስ አድሃኖም አዲስ አበባ አልመጣም! መሠረተቢሱ መሠረት ሚዲያ! ራሱን “ዓለምአቀፋዊ ጋዜጠኛ” ብሎ በመሰየም ለፈረንጅ ሚዲያ መሥራት እና አገርን መሸጥ፣ ባንዳ መሆንን ጌጡ ያደረገው ኤሊያስ መሠረት ህወሃት/ትህነግ ከመንበሯ ከተነቀለች ጊዜ ጀምሮ በዋንኛነት የያዘው አጀንዳ መርዘኛ ፕሮፓጋንዳውን በ“መረጃ” ስም መትፋት ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፋኖ ትግል መሪ የሆነውን እስክንድር ነጋን ፊት ለፊት በማድረግ “ከመንግሥት ጋር በውጪ ድርድር እንዲደረግ የፋኖ ክንፍ ጠየቀ” ብሎ የሐሰት ወሬ በትኖ ነበር። ይህ ሆን ብሎ የፋኖ ኃይሎችን ለመበታተን እና አንድነት በመካከላቸው እንዳፈጠር ያስወራው ተራ አሉባልታ እንደሆነ ራሱ እስክንድር ወጥቶ ተናግሯል። መሠረተ ቢሱ ኤሊያስ ይህንን መረጃ ካወጣ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “ይህ ሰው ያኔ ለወያኔ እንደሠራ አሁንም ለብልፅግና … [Read more...] about የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ?
ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ
የአማራ ፋኖዎች አንድ እየሆኑ ነው። ሆኖም አሁንም በእስክንድር ነጋ ከሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጋር በተገናኘ የተወሰኑ የፋኖ ወገኖችንም ማሰባሰብም ያስፈልጋል። እነ ኮሎኔል ፋንታሁን፣ እነ ሻለቃ መከታው፣ እነ ሻለቃ ከፍያለው ደሴ፣ እነ ሻለቃ ደረጄ በላይ የመሳሰሉትን። እነዚህ ወገኖች የህዝብ ፋኖዎች እንጂ የግለሰብ ክቡር ዘበኞች ባይሆኑ ጥሩ ነው። ለራሳቸው ሲሉ። ምን አልባት ከእስክንድር ነጋና ለእስክንድር ነጋ ቅርብ የሆኑ፣ በአገር ቤትም በውጭ አገር የሚገኙ፣ የተዛባ መረጃ ስለደረስቸው ይሆናል አሁን የያዙትን አቋም እየያዙ ያሉት። በዚህ ረገድ እነዚህ ወገኖች እውነታውን እንዲያውቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው። አሁንም "እስክንድር፣ እስክንድር" የምትሉ ወገኖች በጭፍንና በስሜት ሳይሆን ነገሮች በማስረጃ ማገናዘብ መጀመር አለባችሁ። እስክንድር ነጋ "አሜሪካ መኖር ሲችል … [Read more...] about ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ
ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ?
መግቢያ ሰሞኑን የፋሲል ቤተመንግሥት እድሳት ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ የግንቡ የውጭ ገፅታ ቀለም ከተለመደው ተቀይሮ መታየቱ ነው። ውዝግቡን ተከትሎም በእድሳቱ ስራ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸውም ሆኑ ሌሎች የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች ምላሾችን ሰጥተዋል። ሆኖም የተሰጡት ምላሾች ውዝግቡን የማቆም አቅም ያላቸው አይመስልም። በፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል ላይ ያለንን ጥያቄ ለጊዜው ያዝ እናድርገውና የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ የሆነው የፋሲል ቤተመንግሥት መታደሱን የሚቃወም የለም። በተለይም ግቢው ውስጥ የተሰራው ላንድስኬፕና ለቱርስቶች የተዘጋጀው የማረፊያ ቦታ በጥሩ ጎኑ የምንመለከተው ነው፤ እንዲሁም የግንቡ መዋቅራዊ ዝንፈቶችን ለማስተካከል የተወሰደው እርምጃም መልካም የሚባል ነው። ሆኖም የብዙዎቻችን ጥያቄና ውዝግብ መንስኤ የሆነው በግንቡ ውጫዊ ገፅታ … [Read more...] about ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ?










