"ዝምታ ነው መልሴ" ሲሉ ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ድምጻቸውን በቲውተር በኩል በዘፈን ምርጫ አጅበው ብቅ ያሉት ለስንብት ሁለት ቀናት ሲቀራቸው ነው። "የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው" ሲሉ የተቀኙት ፕሬዚዳንቷ "ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" በሚል ሐረግ መልዕክታቸውን አስረውታል። ይህኔ ነው "የኔታ መስፍን ወልደማርያምን ነብሳቸውን ይማረው" ሲሉ ፋይል ያገላበጡ ፕሬዚዳንቷ በኤክስ ይፋዊ ገጻቸው ላይ ላሰፈሩት ቅኔ ምላሽ የሰጡት። አንዳንዶች "ክብርት ሆይ ሕዝብም መንግሥትም መሆን አይቻልም" ሲሉ ቀልደውባቸዋል። ግልጹ፣ ያመኑበትን ለመናገር ወደኋላ የማይሉት፣ የአደባባዩ ምሑር ፕሮፌሰር መስፍን "ለሦስት መንግሥት ያገለገለች" ሲሉ በሎሌነት የመሰሏቸው የሳህለወርቅ ዘውዴን ሹመት በፍጹም እንደማይቀበሉት ተናግረው … [Read more...] about የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን
abiy ahmed
“መፈንቅለ መንግሥት በጭራሽ አይሳካም”
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? "አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ?በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው።የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም።በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል።መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው።ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመወጣትና የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታት በምን ደረጃ ታቅዷል።" (አቶ አቤነዘር በቀለ - የተ/ም/ቤት አባል) " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ "ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም … [Read more...] about “መፈንቅለ መንግሥት በጭራሽ አይሳካም”
የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ
በአንድ ጊዜ 8ሺ ሰው በአንድ ቀን ደግሞ እስከ 40ሺ ሰው የሚስተናገድበት ትልቅ የድግስ አዳራሽ በአዲስ አበባ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ከ120 አመት በፊት ሲሠራ የነበረው የምህንድስና፣ ቅርጽና ይዘት፣ የመንግሥታዊ ድግሡ ታዳሚዎች ማንነትና የግብሩ ሥርአት፣ “ቀድሞም ጠቢብ ነበር ሰለሞን አባቱምኒልክ ይበልጣል ሰው ይዞ መብላቱ” ዳግማዊ ምኒልክ ሰዉ ሁሉ አንድ ጊዜ ተሰብስቦ የሚበላበትን ትልቅ አዳራሽ ለመስራት በመወሰን፣ በ1889 ዓ.ም ክረምቱን መናገሻ ወርደው እንጨት ሲያስጠርቡ ከረሙ፡፡ ወታደሩም በድግስ ጊዜ ሜዳ ላይ ሆነን ጸሀይና ዝናብ እንዳይመታን ለኛ ብለው አይደለምን በማለት ደስ ተሰኘ፡፡ ላዳራሹ የሚያስፈልገውን 4 ማዕዘን፣ ሳንቃና እንጨትም ላሊ እየወጣና እየዘፈነ ማመላለስ ጀመረ፡፡ በ1890 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ዳግማዊ ምኒልክ ከአውሮፓ መሀንዲሶችን … [Read more...] about የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ
ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል”
የዓባይ አጀንዳ ሲቋጭ የቀይ ባህር ጉዳይ መነሳቱ አጀንዳው እጅግ ተደርጎ የታሰበበት ለመሆኑ ማሳያ ተደርጓል። “የቀይባህር አጀንዳ ሃሳብ ማስቀየሪያ ነው” በማለት ለፕሮፓጋንዳ የሚነሱ የማይሳካላቸው በዚሁ መነሻ እንደሆነም ተመልክቷል። እጅግ ሰላማዊ በሆነና በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጮችን አቅርበው ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን እንዳለባት ያመለክቱት ዐቢይ ቀይ ባሕር “ጉዳይ የኅልውና ነው” ብለውታል። የወንበዴው መሪ መለስ ዜናዊ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” ሲል አሰብ ወደብና ቀይ ባህርን አስመልክቶ ለተከራከሩ የሰጠው መልስ ነበር። ኢትዮጵያን የሚያክል አገር የተቆለፈባት እንድትሆን የተስማማው ትህነግ፣ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብቷን እንድትበትን ፈርዶባት ኖሯል። የድርጅቱ መሪ መለስ “አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ከኤርትራ መቀማት ይቀላል” በሚል ሥጋት … [Read more...] about ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል”
“ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
ዛሬ የትግራይ ክልልን እንዲያስተዳድሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቀመጡት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚታወቁባቸው የሽፍትነት ዘመን ንግግራቸው መካከል “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” የሚለው ነው። ዛሬ ደግሞ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ሆነው አራተኛውን ሙሌት ቦታው ድረስ በመሄድ አክብረዋል። ያኔ ተሸጧል ሲባል አብረው ያመኑና ዜናውን ያራገቡ መልስ ሊሰጡበት የሚገባው ጥያቄ፤ 1ኛ. ግድቡ አልተሸጠም ነበር ወይም 2ኛ. የተሸጠው ተመልሷል ወይም 3ኛ ይህ አሁን ሞልቶ የሚታየው ግድብ ከተሸጠ በኋላ በአዲስ መልክ የተሠራ ነው። መልሱን ለአቶ ጌታቸውና ደጋፊዎቻቸው እንተውና ኢትዮ12 ስለ አራተኛው ሙሌት በተመለከተ የዘገበውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግሥት የመፈረም ፍላጎት … [Read more...] about “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
“አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት)
“አመጽ ሁሉ መመራት ያለበት ለበቀል ባለህ ጥማት ሳይሆን፤ ለፍትሕ ባለህ ከፍተኛ ፍላጎት መሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው” ደራሲ አብሂጂት ናስካር 1. ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ። በቅርብ ዓመታት ለምዕራባውያን መንግሥታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ያስተላለፈው መልዕክት "ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ" የሚል ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ድምጽ በረገጠ እቡይ መንፈስ፤ ዶ/ር ዮናስና አጋሮቻቸው፤ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ፤ ደጅ ጥናት ላይ ናቸው። ይህ ዓይነት እኩይ መንንፈስ፤ እንኳን ትላንት ወደ ፖለቲካው መድረክ አንገታቸውን ብቅ ላደረጉ ይቅርና፤ ከ40 ዓመታታ በላይ በምዕራባውያን ጉያ ውስጥ የነበረውና የኢትዮጵያን ጥቅም ለምዕራባውያን አሳልፎ ለሸጠው ለሕወሃትም አልበጀም። ገራሚው ነገር፤ ከዓመት ተኩል በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቅር ታመው … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት)
“አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ በመረጠው መንግሥት እንዲተዳደር ይነሳ የነበረው ጥያቄ፤ ከ50 ዓመታት በላይ በተደረገ ትግልና በተከፈለ ከፍተኛ መስዋዕትነት በሰኔ 2013 ምላሽ አግኝቷል። ምንም እንኳን ምርጫው አንዳንድ መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም፤ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ የምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመንግሥት ሥልጣን ምርጫ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው። ይህ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና በበርካታ ሃገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ፍትሃዊና ሚዛናዊ ምርጫ ነው ቢባልም፤ ይህ መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ አይደለም የሚሉ ግን አልጠፉም። የሕወኃት መራሹ መንግሥት ተወግዶ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ ከሕዝብ ያገኙት ድጋፍ በሃገራችን ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን፤ … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም
የቀረቡ ጥያቄዎች በጥቅሉ፤ ከኦነግ ሸኔ፣ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ዜጎች፣አርሶ አደሩ ምርቱን ለመሸጥ ከመቸገሩ ጋር በተያያዘ፣ወደ አዲስ አበባ ምርት እንዳይገባ ከመከልከሉ ጋር፣ከክልሎች የርስ በርስ መናበብ አለመቻል፣የሱዳን ወታደሮች ወረው የያዙትን የኢትዮጵያ መሬትና ያወደሟቸውን ንብረቶች የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼️ ሰላምና መረጋጋት* የአገራችን የሰላምና መረጋጋት አሁን ያለው ከነበርንበት የተሻለ ነው፤ወደተሟላ ሰላም ለመሄድ በጣም በርካታ ስራ ይጠበቅብናል፤ … [Read more...] about አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም
በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ከአድዋ ወደ ራያ የዞረው የትግራይ አስተዳደር አዲስ መሪና ከመሪው ጀርባ የሚያጦዝ አዲስ ስብሃት ነጋን አግኝቷል። አዲሱ የስብሃት ነጋ ምትክ ንጉሥ ፈጣሪ (kingmaker) ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ ሲሆን፣ የትግራይ ቲቪ ይፋ እንዳደረገው የትግራይ መሪ የሆነው ጌታቸው ረዳ ነው - ሁለቱም ከአማራ ከተወሰደው ራያ!! በይፋ በሚታዩ መረጃዎች ጌታቸው ረዳ በትግራይ ታጋይ ሳይሆን ትግራይን የመራ ብቸኛ ካድሬ ሆነው ይመዘገባል። ጌታቸው ረዳ ሌላ የሚያስመዘግበው ሪኮርድ ደግሞ በጥላቻና “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ የተፈለፈሉ ሚዲያ፣ አክቲቪስቶች፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የብሔራቸው ተቆርቋሪ መስለው ሲንቀሳቀሱና ጥላቻን ሲያሰራጩ የነበሩ፣ በየክልሉ የክልልነት ጥያቄ በማስነሳት ግጭት እና አገር ብጥበጣ ውስጥ የገቡ፣ ሁሉ በጌታቸው አመራር ሥር ስለነበሩ ቆጣሪያቸው … [Read more...] about በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል
ሰሞኑን የአዲስ አበባ መስተዳድር ለከተማዋ አስመጣሁት ካላቸው አውቶቡሶች ቢያንስ አንድ ቢሊዮን ብር መመዝበሩ ተነገረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስድስት ቀን ውስጥ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ጉዳዩ ከንቲባዋን በቀጥታ የሚመለከት ነው ተባለ። የአዲስ አበባ መስተዳድር ከቻይና ያስገባቸው 100 አውቶቡሶች ግዢ ጉዳይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል። መስተዳደሩ እንደሚለው አንዱ አውቶቡስ የተገዛው በ19 ሚሊዮን ብር ወይም 355ሺህ ዶላር አካባቢ ነው። የ200ዎቹ ድምር ዋጋ ደግሞ 3.8 ቢሊዮን ብር ወይም 71 ሚሊዮን ዶላር ነው። አውቶቡሶቹ ይህንን ያህል ለምን እንዳወጡ ለሚጠየቀው ጥያቄ የአዲስ አበባ መስተዳደር የሚሰጠው ምላሽ አውቶቡሶቹ ልዩ ናቸው የሚል ሲሆን ለዚህም የሚከተለውን ዝርዝር ያቀርባል። በሀይገር ካምፓኒ የተመረቱና ለመጀመሪያ ጊዜ … [Read more...] about በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል