የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ለማከናወን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሆነውና የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት/ የሚያስገቡበት መርሃ ግብር መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፀድቋል። በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ
Right Column
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል
በአድዋ ጦርነት ወቅት ለእናት ሀገራቸው ነፃነት የተዋደቁ ፈረሰኞችንና ፈረሶችን ለመዘከር በ1933 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ጥር 23/2013 ይከበራል፡፡ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፈረስ ትርዒት፣ በፓናል ውይይቶችና በእደ ጥበባት ኤግዚቢሽን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘውዲቱ ወርቁ ተናግረዋል፡፡ከ33 በማይበልጡ አባላት እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ እያስተዋወቀ ነው፡፡ በዓሉ የተነቃቃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የጎላ ሚና እያበረከተ ነው ተብሏል፡፡ (አብመድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል
የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ ስምምነትን የክልሎቹ መሪዎች ተፈራርመዋል።በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሰላም እና የጋራ የልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል።ጽ/ቤቱ በሁለቱ ክልሎች 12 አዋሳኝ ዞኖችች ላይ ሰላምን በማስፈን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ጥናቶችን ይፋ አድርጓል።በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተዋቀረው የሰላም እና የጋራ ልማት ዕቅድ በቀጣይ በደቡብ፣ በጋምቤላ እና በቤቢሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለመተግበር ማቀዱን ነው የኦሮሚያ ክልል ያስታወቀው።የኦሮሞ እና ሱማሌ ሕዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት የተሳሰሩ እና ከ 1 ሺህ 872 ኪ.ሜ በላይ ወሰን የሚጋሩ … [Read more...] about የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ
በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
በመቀሌ ከተማ ከ350 ሚሊዮን በላይ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ክምችት እንዳለ የፌደራል መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ። በትግራይ ክልል የመድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ወደ ጤና ተቋማት ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ተነግሯል። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከሆነ በትግራይ ክልል ለ47 ጤና ተቋማት 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ ወደ ክልሉ በመድረስ የማሰራጨት አገልግሎት ማከናወኑን አስታውቋል። ቅርንጫፉ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 የጤና ተቋማት ግብዓቶቹን በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን በተለይም በመቀሌ ለሚገኙ 4 ሆስፒታሎች ለዉቅሮ፣ ሀውዜን፣ አዲግራት፣ አክሱም ቅድሰት ማርያም፣ ኮረምና ሌሎች ሆስፒታሎች መድሃኒቶችን አሰራጭቻለሁ ብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን እና በምዕራብ አንዲሁም በማዕከል በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች የመደበኛ እና የጤና … [Read more...] about በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ
ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
ዊንጉ አፍሪካ የተባለው በምስራቅ አፍሪካ በመረጃ ማዕከልነት ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው ድርጅት አዲስ አበባ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ውስጥ 15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያለው የመረጃ ማዕከል (ዳታ ሴንተር - Ethiopia’s first-ever Carrier-Neutral Hyperscale Data Center Park) ሊገነባ ነው።ዊንጉ አፍሪካ በተሰኘ ድርጅት የሚገነባው ማዕከሉ በቀጣይም ድርጅቱ ሁለተኛ ፕሮጀክቱን ከአዳማ ከተማ በ96 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ለመገንባት ዕቅድ እንዳለውም ተነግሯል፡፡የመረጃ ማዕከላቱ ግንባታ በፓን አፍሪካ ፕሮጀክት ስር የታቀፈው ዕቅድ አንዱ አካል ነው የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል በጂቡቲ እና በናይሮቢ ከተማዎች በተመሳሳይ ስራ ላይ ተሰማርቶ ስራዎችን የሰራ ቆይቷል ተብሏል። (Extensia- ENA) … [Read more...] about ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ድሮኖችን ለማምረት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ (ምንጭ Tikvah) … [Read more...] about ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው
የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ
የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመሥራች አባላት ጉዳይን አስመልክቶ ፓርቲው ያቀረበው የመሥራች አባላት ዝርዝር ላይ ቦርዱ 50 የሚሆን ናሙና በመውሰድ ያደረገው ማጣራት ስለ ትክክለኛነቱ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባው በመሆኑ፤ ቦርዱ ጉዳዩን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልኮት እንደነበር ይታወሳል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ባደረገው የማጣራት ሥራ ከሶማሌ ክልል 1145 መሥራች አባላት፣ ከአፋር ክልል 72 መሥራች አባላት፣ ከኦሮሚያ ክልል 23 መሥራች አባላት፣ ከአ.አ. ከተማ አስተዳደር 58 መሥራች አባላት በጠቅላላው የ1298 መሥራች አባላት በተጠቀሱት አድራሻ ያለመኖራቸውን ማረጋገጡን የሚያስረዳ መግለጫ በመስጠቱ የቦርዱም ሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ የማጣራት ሥራ የሚያሣየው ፓርቲው እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው በቃለመኃላ በተረጋገጠ ሰነድ ያቀረበው የመሥራች አባላት ሥም ዝርዝር … [Read more...] about የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ
ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ
ትላንት የተደገደሉትን የህወሓት ቡድን አመራሮች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው መውሰድ እንደሚችሉ ብ/ጄ ተስፋዬ አያሌው በቪኦኤ ቀርበው ተናገረዋል። አመራሮቹ የተገደሉበት ቦታ ሩቅ እና በረሃ በመሆኑ መከላከያ የሁሉንም አስክሬን መልቀም እንደማይችልም አሳውቀዋል። ሰራዊቱም በእግሩ እየተጓዘ መሆኑ ገልፀዋል። በዚህ ተገቢ ባልሆነ ጦርነት ህይወታቸው እያለፈ የሚገኘውን አካላት ገበሬዎች እየቀበሯቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ብ/ጄ ተስፋዬ ፥ "የአመራሮችን አስክሬን ብንችል ብናመጣው ደስ ይለን ነበር" ብለዋል። በተጨማሪ ፥ ትላንት የተገደሉት አመራሮች ፎቶና ቪድዮ እንደሚደርሳቸው ገልፀው ካስፈለገ ይህን መስጠት ፣ በሚዲያ ማስተላለፍ ይቻላል ነገርግን በሚዲያ ሰው ገደልን ብሎ ማሳየት ከኢትዮጵያ ባህል አንፃር የማይሄድ እና የእርስ በእርስም ስለሆነ ይህን ማድረጉ ተቀባይነት … [Read more...] about ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ
አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል
ሕግን በማስከበር ዘመቻ ወቅት መከላከያ እና የአፋር ክልል በመቀናጀት ባደረጉት ስምሪት በህወሐት ላይ ድልን መቀዳጀት መቻላቸውን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል ዐርባ ገለፁ። ሕወሓት ለጥፋት ዓላማው ማስፈፀሚያ ከአንድ ዓመት በላይ ሲያሰለጥንና ሲያስታጥቀው የነበረውንና ራሱን የአፋር ነፃ አውጪ ብሎ የሚጠራውን ኡጉጉሙ፤ ወደ ሠላም ፣ ድርድርና ልማት ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል። በዚህም ህወሐት ኡጉጉሙን በመጠቀም ወደ ጂቡቲ ለመሻገር የወጠነው እቅድ ሊከሽፍበት ችሏል ብለዋል። የመከላከያ መረጃና የአፋር ክልል ይህንን ሴራ አስቀድመው በመረዳት በፍጥነት አካባቢውን ባይቆጣጠሩት ኑሮ ፣ ኡጉጉሙን በመጠቀም የህወሐት አመራሮች በቀላሉ ወደ ጅቡቲ ማምለጥ ይችሉ እንደነበር ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።(ቅንብር ፋና) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል
በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ
ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል። በታህሳስ ወር በተካሄደው ቅንጅታዊ የኮንትሮባንድ መከላከል ስራ ግምታዊ ዋጋቸው ብር 274 ነጥብ 8 ሚሊየን የሆኑ የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ህገወጥ ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሌላ በኩል ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ወጪ የኮንትሮባንድ አይነቶች መያዛቸውን በታህሳስ ወር የኮንትሮባንድ መካከል ስራዎች ሪፖርት ተመላክቷል። በአጠቃላይ በወሩ ብር 344 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል። በገቢ ኮንትሮባንድ የተያዙት ዕቃዎች በተለይም በጅጅጋ፣ በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በሞያሌና ኮምቦልቻ ቀዳሚውዎቹን ስፍራዎች የሚይዙ … [Read more...] about በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ