ካለፉት አራት ወይም አምስት ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ የሚታየው የፖለቲካ መካረርና ጡዘት የሁለትዮሽ የተናበበ የገፊና ጎታች ሤራ (Pull and Push Conspiracy) ነው ለማለት የሚያስችሉ በርካታ ጠቋሚዎች አሉ። የዚህ ሤራ ዓላማ ሕዝብን መስዋዕት በማድረግ መስዋዕትነቱ በሚፈጥረው ቁጭትና ሐዘን ሕዝብን ስሜት ውስጥ በማስገባት ሥርዓት አፍርሶ ሥልጣን ባቋራጭ ለመጨበጥ ያለመ ነው። ለነገሩ ይህ ዓይነት የፖለቲካ አካሄድ አመጽ በተቀላቀለበት መልኩ ሁልጊዜ ባይታይም ሠለጠነ በሚባለው ዓለም የተለመደ አካሄድ ነው። ፓርቲዎች ጎራ ለይተው ይናቆራሉ፣ ይሰዳደባሉ፤ ሚዲያው ጉዳዩን የተካረረ ፖለቲካ ያደርገዋል፤ ደጋፊዎች በስሜት በመነዳት ብዙ ርቀው ይሄዳሉ፤ አታጋይ የተባሉት ፖለቲከኞች ግን አብረው ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ ሲሳሳቁ ይገኛሉ። “የሠለጠነ ፖለቲካ” በማለት ይህንን ድራማ ሚዲያው ሌላ ቅኝት … [Read more...] about በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት