አብርሆት የትውልዶችን ልቦና በእውቀት ለማብራት የተቋቋመ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሕንፃው ምሰሶዎች ጥበብ የሚለው ቃል በ18 የራሳቸው ፊደል ባላቸው ቋንቋዎች ተፅፎ የሚገኘውም ለዚህ ተልዕኮ ያለውን ቁርጠኝነት ለማመላከት ነው ብለዋል። አብርሆት ቤተመፃህፍት በብልሃት ክህሎት የተጎናፀፉ ወጣቶችን የማብቃት አላማውን በትጋት በመወጣት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ ዛሬ በአብርሆት ያገኘኋቸው ወጣቶች እንደ ሮቦቲክስ እና የፈጠራ ትግበራ ሥራዎች ላይ ተጠምደው ስላገኘኋቸው አድናቆት እና ማበረታቻ ይገባቸዋል ብለዋል። መጪው ትውልድ ከኢትዮጵያ የልማት ግቦች ጋር በተናበበ ሁኔታ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮዲንግ፣ በሳይበር ሴኩሪቲ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ክህሎታቸውን … [Read more...] about “የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል” አለብን
News
“ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ ነው” ከ190 ሀገራት 2ኛ የወጡት ተሸላሚዎች
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 ሀገራት በላይ የተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር በቅርቡ በግሪክ አቴንስ ታካሂዷል፡፡ 7 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ የፈርስት ግሎባል ቡድን በውድድሩ ተሳትፎ ከዓለም 2ኛ ደረጃ በመያዝ የብር ሜዳልያ ተሸልሟል፤ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ስሟን ማስጠራት ችሏል፡፡ ተማሪዎች የሳይንስ የቴክኖሎጂ የኢንጂነሪንግ እና የሂሳብ እውቀትን በመጠቀም ለአሁናዊ የዓለም ችግሮች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም መፍትሄ እንዲያመነጩ የተለያዩ እድሎች ይፈጠራሉ፡፡ እድሎችን በመጠቀም የራሳቸውን የቤተሰባቸውን የአከባቢያቸውን የሀገራቸውን እንዲሁም በዓለም ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ያፈላልጋሉ፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሶፎትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ ዳግማዊ ግሩም የቡድኑ መሪ ሲሆን ስለ ውድድሩ ሲናገር የዘንድሮው ውድድር ትኩረት የወደፊቷን ዓለም … [Read more...] about “ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ ነው” ከ190 ሀገራት 2ኛ የወጡት ተሸላሚዎች
የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
ከበረሃ ውንብድና አገረ መንግሥትን ወደመምራት ሳያስበው የተቀበለው ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት በነጻ አውጪ ስም አንዲት ሉዓላዊት አገር ጠርንፎ በአናሳዎች በግፍ ሲገዛ የነበረው የወንበዴዎች ቡድን ጎራ ለይቶ በአደባባይ መካሰስ ከጀመረና ውዝግቡም እየተካረረ መጥቶ ትግራይን እንደ አፍጋኒስታን ወይም ኢራቅ በጦር አበጋዞች ከፋፍሎ ወደለየለት ደረጃ እየወሰዳት መሆኑ በቅርቡ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የቡድኑ መሪ የሆነው ደብረጽዮን እነ ጌታቸው የሚከሱኝ በፊትም ጦርነት ውስጥ ያስገባንና ሚሊዮኖችን ያስጨፈጨፈው ትህነግ ነው፤ አሁንም መልሶ ጦርነት ውስጥ ሊከተን ነው፤ ጦርነት ናፋቂ ነው እያሉ ነው፤ ነገር ግን ተጨፈጨፈ የተባለው ሕዝብ ማስረጃ የታለ? ባለተጨበጠና ባልተረጋገጠ፤ ማስረጃ በሌለው እኔን መክሰስ ብቻ ስለፈለጉ ባልሞተ ሕዝብ ይከስሱኛል በማለት … [Read more...] about የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ
በአዲስ አበበ ከተማ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ። የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት፦ 1ኛ. ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ 2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 3ኛ. ዮሴፍ ባቡ ሆራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 4ኛ. አቤኔዘር ቶሎሳ ሙሉ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 5ኛ. ለሚ ሲሌ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር እና 6ኛ. መቅደስ አረጋዊ ገንዘብ ተቀባይ የሆኑት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም በሙስና ወንጀል … [Read more...] about በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጣለበት ዕግድ ተነሳለት
በፓሪስ ኦሊምፒክ ዋዜማ የተቀሰቀው የእነ ኃይሌና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውዝግብ ወደ ሕግ ማምራቱ ይፋ ሲሆን “ቀድሞም ቢሆን መሆን የነበረበት ጉዳይ ይህ ነበር። አበጃችሁ” ሲሉ ጉዳይን በረጋ መንፈስ የሚከታተሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር። በሕግ ሕግን ማስከበርና፣ በሕግ መብትን ማስጠበቅ እንደሚቻል የሚያሳይ፣ ለሌላው ወገን ደግሞ በሕግ ራስን መከላከልና በሕግ መጠየቅ እንዳለ የሚያስተምር አግባብ እንደሆነ አመልክተው ነበር። ሻለቃ ኃይሌና አትሌት ገዛኸኝ አበራ የሚመሩትና ሁለት ፌዴሬሽኖች የተካተቱበት ወገን ዶክተር አሸብር የሚመሩትን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከስሰው ኮሚቴው የሚያንቀሳቅሳቸውን የባንክ ሂሳቦችና፣ የዕለት ተለት ክንውን ማካሄድ እንዳይችል አስወስነው የነበረው በሕግ በመሆኑ ዜናው ፍሞ ነበር። ጅማሮውን የትግላቸው ውጤት አድርገው ያቀረቡም ጥቂቶች … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጣለበት ዕግድ ተነሳለት
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው
* በሁሉም ባንኮች ያለው ሒሳብ ታገደ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራት አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች ክስ ተመሰረተባቸው። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሁሉም ባንኮች ያለው ሒሳብ ታገደ። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፤ ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ፣ ዋና ፀሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴም ከተከሳሾቹ መካከል ነው። ክሱን የመሰረቱት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ_ገብረሥላሴ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው። በከሳሾቹ ጠበቆች በኩል ክሱ የቀረበለት የፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራድ ምድብ ችሎት ኮሚቴው ፤ ግንቦት 5 እና ሰኔ 4፤ 2016 ዓ.ም. ያካሄዳቸው ጠቅላላ ጉባኤዎች እና ውሳኔዎች እንዲታገዱ ትዕዛዝ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው
የ፲፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የዘንድሮና የአምናው መጠነኛ ንጽጽር
በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 36 ሺህ 409 ወይም 5.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከትላንት በስቲያ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከዚህ በታች ያለውን መረጃ ያሰባሰብነው ከመንግሥታዊ ሚዲያና ከቲክቫህ ነው። በአጠቃላይ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ 4 ትምህርት ቤቶች ከሐረሪ ክልል ውጭ ሁሉም ክልሎች ላይ አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት 273 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ 1ሺ 220 ተማሪዎች ከ500 በላይ ያመጡ ናቸው ተብሏል።እንዲሁም በዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 5.4 በመቶ ፈተናውን አልፈዋል ይህም ማለት … [Read more...] about የ፲፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የዘንድሮና የአምናው መጠነኛ ንጽጽር
የኢቲቪ ባለሥልጣናት ኦሊምፒክና አትሌቲክስ ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ እንዲሠራ አዘዙ
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለሥልጣናት በኦሊምፒክና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ትኩረት ያደረገ የፕሮፓጋንዳ ሥራ እንዲሠራ መመሪያ መስጠታቸው ተሰማ። መመሪያው ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ኢቲቪ የሚያቀርበው ዘገባ የሕግ ጥያቄ ማስደገፊያ እንዲሆን ተደርጎ ለመረጃነት እየተዘጋጀ መሆኑ ከሌሎች ወገኖች ተደምጧል። ከፓሪሱ ኦሊምፒክ መጀመር ቀደም ብሎ በማኅበራዊ ሚዲያው የተጀመረው ዘመቻ ሁለት ቡድኖች ጎራ ለይተው ውዝግብ መጀመራቸውን አመላካች እንደነበር ይታወሳል። ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴና አትሌት ገዛኸኝ አበራ ጎራ ለይተውና ተመሳሳይ አቋም ይዘው የለኮሱት ተቃውሞ ውድድሩ ከመጀመሩ ቀናት በፊት ሲሆን፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ተቃውሟቸውን ለመግዛትና ለማሰራጨት ጊዜ አልወሰደም። ከወራት በፊት በተጠናቀቀ ምርጫ ላይ ቅሬታ በማንሳት የተጀመረው ክስ ውድድሩ ከተጀመረ በኋላም ከፓሪስ በሚወጡ ዐውዳቸውን … [Read more...] about የኢቲቪ ባለሥልጣናት ኦሊምፒክና አትሌቲክስ ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ እንዲሠራ አዘዙ
ገዱ: “የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው እንክሰስው”፤ “ባለውለታ ነው እንጠቀምበት”
ሰሞኑን ለጥገኝነት ማመልከቻቸው ደጋፊ ነው የተባለለትን ዘለግ ያለ ጽሑፍ ያቀረቡት ገዱ አንዳርጋቸው በትግራይ ማኅበረሰብ ዘንድ የተከፋፈለ ዕይታ የፈጠሩ መሆናቸው ተነገረ። ““የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው፤ እጃችን ገብቷል እንክሰሰው” ባዮች በርተተው የታዩ ቢሆንም “ባለውለታችን ነውና አሁንም እንጠቀምበት” የሚሉ በሌላ ወገን ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። በዘመነ ትህነግ የሥርዓቱ ተላላኪና ጉዳይ ፈጻሚ የነበሩት ገዱ አንዳርጋቸው የዚያን ጊዜው አለቆቻቸውን ለማስደሰት ያልታዘዙትን፣ ያልተጠየቁትን እላፊ በመሄድ በመፈጸም አለቆቻቸውን እጅ በመንሳት ይታወቃሉ። ለዚህ ታማኝነታቸው በአማራ ሕዝብ ላይ የመጨረሻውን ሥልጣን እንዲያገኙና ሎሌነታቸውን የበለጠ በደስታ እንዲፈጽሙ አድርጓቸዋል የሚሉ ጥቂት አይደሉም። እንደማሳያም የወልቃይትን ጉዳይ ይጠቅሳሉ። ገዱ አንዳርጋቸው ከዚህ በታች ያለው … [Read more...] about ገዱ: “የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው እንክሰስው”፤ “ባለውለታ ነው እንጠቀምበት”
ዘመኑን የጠበቀ የወታደራዊ ሬዲዮ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተከፈተ
በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የራዲዮ መገጣጠሚያ ፋብሪካ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና የተቋሙ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት ነው ተመርቆ የተከፈተው። የመከላከያ ሰራዊታችን አገራችን በየጊዜው የገጠሟትን ፈተናዎች በሌሎች አገራት ቴክኖሎጂዎች ላይ በመመርኮዝ ግዳጅ እየተወጣ እንደዘለቀ አውስተው የተመረቀው የወታደራዊ ራዲዮ ፋብሪካ የሰራዊቱን የተልዕኮ አፈፃፀምና የግዳጅ ስምሪት የሚያቀላጥፍ እንደሆነ ተናግረዋል። "ወታደራዊ ራዲዮው በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ የመጨረሻው የዲጅታል ስታንዳርድ ራዲዮ ነው።" ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ይህንኑ እውን በማድረግ ረገድ የቻይናው ሀይቴራ ካምፓኒ እና የመከላከያ … [Read more...] about ዘመኑን የጠበቀ የወታደራዊ ሬዲዮ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተከፈተ