“ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም፤ በሙስና እና በሌብነት ቀንበር ስር አይወድቁም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። "መጻሕፍት የህይወት ዘመን ጓደኛ ናቸው" እንዳሉት ከተሽከርካሪ ነፃ (car free) መንገድ ያስፈልጋል፤ ከሀሳብ እና ከመጻሕፍት ነፃ የሆነ ጎዳና ግን ሊኖር አይገባም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከመደበኛ ስፍራው ባለፈ በአዲስ አበባ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ለታዳጊ ህፃናት መጻሕፍት ያቀርባል ደግሞም ያነባል፤ ያስነብባልም። ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም፤ በሙስና እና በሌብነት ቀንበር ስር አይወድቁም ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ታነባለች ጎዳናዋም በመጻሕፍት ተሞልቶ ይትረፈረፋል። “እኛ ኢትዮጵያውያን ካለብን ችግር የምንወጣው … [Read more...] about “ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
News
ታከለ ኡማ የዳያስፖራ አኩራፊዎችን ሰብስበው ድርጅት እየመሠረቱ ነው፣ ሚዲያም አቋቁመዋል
ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ወደ ኦህዴድ ከለወጡት የዶክተር መረራ ወጣቶች ክንፍ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ታከለ ኡማ አዲስ የትግል ኅብረት በመፍጠር ላይ መሆናቸው ተሰማ። ለዚህ እንቅስቃሴ የሚሆናቸው የመደበኛ ሚዲያና የማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጽ ሠራዊት እንዳመቻቹም ታውቋል። መነሻቸው ፖለቲካዊ ኩርፊያ ነው ተብሏል። ጎልጉልን ያነጋገሩ የመረጃው ባለቤቶች እንዳሉት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የማዕድን ሚኒስትር መንግሥት ላይ አቂመዋል። የለውጡ የምሥጢር ታጋይ እንደነበሩ የሚናገሩት ታከለ አሜሪካ ከተሻገሩ በኋላ በዳያስፖራ ከሚገኙ ዋነኛ አኩራፊዎች ጋር በማበር ጠበቅ ባለ እንቅስቃሴ ተጠምደዋል። ጥያቄው ከቀረበላቸው መካከል አንዱ የሆኑት የኦህዴድ የቀድሞ አመራር እንዳሉት ታከለ ኡማ ከአማራ፣ ከኦሮሞና የሰላም ስምምነቱን … [Read more...] about ታከለ ኡማ የዳያስፖራ አኩራፊዎችን ሰብስበው ድርጅት እየመሠረቱ ነው፣ ሚዲያም አቋቁመዋል
ሌቦቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይፋ ሆኑ፤ 4 ቢሊዮን ብር ያህል ባክኗል
የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲትን በተመለከተ ተቋማቸው ያካሄደውን የኦዲት ሪፖርት፣ ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ለፓርላማው የቀረበው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ ስድስት ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ፣ 19 ተቋማት ደግሞ የጎላ ችግር ያላባቸው ሆነው በመገኘታቸው ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ሒሳባቸው የጎላ ችግር ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት … [Read more...] about ሌቦቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይፋ ሆኑ፤ 4 ቢሊዮን ብር ያህል ባክኗል
ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው
በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ተላላኪነትና ባንዳነት የፈረሰው ገናናው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ ዳግም እያንሠራራ ነው። አዳዲስ ባሕረኞችን በውጭ አገር እያሠለጠነ ሲሆን አዳዲሶችን ደግሞ በአገር ውስጥ እያስመረቀ ነው። ትላንት በመሠረታዊ ባሕረኞችን አስመርቋል። ከመከላከያ ማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘነው ዜና ከዚህ በታች ቀርቧል። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አካዳሚ አዛዥ ኮማንደር ከበደ ሚካኤል በባሕረኞች የምረቃ ፕሮግራም ላይ እንደገለፁት አካዳሚው ባሕረኞች ከባህረኝነት ሙያ ጋር በቀጥታ ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሳይንሳዊ መርሆችን እንዲረዱ ስልጠና ወስደዋል። ባሕረኞች በባሕር ላይ የሚያጋጥማቸውን ዋና ዋና የሚባሉ መሠረታዊ የባሕር ላይ ደህንነት ትምህርቶች እና ሌሎች ጠቅላላ እውቀት ማግኘታቸውንም ገልፀዋል። ኮማንደር ከበደ … [Read more...] about ከ፴ ዓመት ውርደት በኋላ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የውሃ አካል ላይ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ነው
“በደብረ ኤሊያስ ወረዳ ሥላሴ ገዳም የታጠቀ ፅንፈኛ ኃይል መሽጎ ነበር” ጄኔራል አዘዘው መኮንን
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ በተወሰደ እርምጃ የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል እየተሠራ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። መንግሥት በወሰደው የሕግ ማስከበር እርምጃ በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ሰላም ተመልሶ የግብርና ሥራቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን የአካባቢው አርሶ አደሮች መግለጻቸው ይታወሳል። በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 403ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዘዘው መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት በደብረ ኤሊያስ ወረዳ በስላሴ ገዳም አካባቢ የታጠቀ ፅንፈኛ ኃይል መሽጎ ነበር። በገዳሙ የመሸገው ኃይል ችግር ለመፍጠር በማለም ተጨማሪ ኃይል በማሰልጠንና በማደራጀት ሲሰራ መቆየቱን በተገኘው መረጃ ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። የአካባቢውን ህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት አንቅስቃሴዎችን ከማስተጓጎሉም በላይ የጸረ ሰላም … [Read more...] about “በደብረ ኤሊያስ ወረዳ ሥላሴ ገዳም የታጠቀ ፅንፈኛ ኃይል መሽጎ ነበር” ጄኔራል አዘዘው መኮንን
በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰላም መደፍረስ እና የጸጥታ ሥጋቶችን ለመቀልበስ ትኩረት እያደረገ በነበረበት ወቅት በሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ዝውውር የተሰማሩ አካላት በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኢኮኖሚው መስክ አስተዋፅዖ ባላቸው የማዕድን ምርቶች በተለይም በወርቅ ላይ ያተኮረ ዝርፊያ ሲፈጽሙ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡ የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ … [Read more...] about በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
ነብርን ያላመዱ እናት
ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ ይባላሉ፤ በቦረና ዞን የዲሎ ወረዳ ቃዲም ኦላ ጫጩ ገልገሎ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ የዱር እንስሳት የሆነውን ነብርን በማላመድ አብራቸው እየኖረ ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ ጂሎ በዞኑ ድርቅ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ለከብቶች ሳር ለመፈለግ ወደ ዱር ባቀኑበት ጊዜ የነብር ግልገል ማግኘታቸውን ይናገራል። ወይዘሮዋ ግልገሏን እነርሱ የሚመገቡትን ምግብ በመመገብ እንዳሰደጉትና አሁን ላይ ተላምዶ ከፍየሎችና ህፃናት ጋር እያደገ ነው ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ነብርን ያላመዱ እናት
የወልቃይ ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የወሰንና የማንነት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ህዝቡ ሰልፍ ባደረገባቸው በሁሉም ቦታዎች የተላለፈው የዞኑ አስተዳደር መልዕክትየተከበርከው ጀግናው፣ አይበገሬው የወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብክቡራት እና ክቡራን የአማራ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሃገረ-መንግሥት ከመሠረቱና ካፀኑ አንጋፋ የአገሪቱ ሕዝቦች ውስጥ አንድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሦስት ሺሕ ዘመናት በዘለቀ ሃገረ መንግሥትነትና የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ከሳባዊት አክሱም ሥልጣኔ እስከ ዘመናዊት ኢትዮጵያ አመሠራረት ሂደት ውስጥ አማራ የራሱ የሆኑ አንጸባራቂና በጎ ሚናዎችን ተጫውቷሌ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የአማራ ሕዝብ ምንጩ ከወዴት ነው ተብሎ የታሪክ መዝገቦች ሲፈተሹ የአማራ መነሻው ከወልቃይት-ጠገዴ ነው፡፡ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ነገዶች ታሪክ ፀሃፊያን እንደሚያስረዱት፣ እኛም ከአያት ቅድመ አያቶቻችን እንደተማርነው፣ ወልቃይት-ጠገዴ የከለው ሌጅ፤ … [Read more...] about የወልቃይ ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የወሰንና የማንነት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ
ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የሠራ ወጣት
በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ሥራዎች የሚታወቅ ወጣት ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰራ። በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ስራዎች የሚታወቅ ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያ 360° ዞር መምታት የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰርቶ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ እና የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በተገኙበት ለእይታ አቅርቧል። ሮኬቱ ከስድስት እስከ 10 ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል መሆኑን ወጣት ዘካሪያ በመገለጽ በአንዴ አራት ቀላዮችን የሚይዝና መወንጨፍ የሚችል ሮኬት መሰራቱን ገልጸዋል። ያለሰው ንክኪ በራሱ ማዘዣ 360° ዲግሪ በመዞር በአየር ክልል የሚንቀሳቀስና ጥሶ የሚገባ የጠላት ዒላማን መምታት የሚችል ሮኬት መሆኑንም አስታውቆ ቦታው ከተመቻቸ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የተሳካ … [Read more...] about ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የሠራ ወጣት
በኢትዮጵያ ካሉ 47 ሺህ ት/ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራት ብቻ ናቸው
በኢትዮጵያ ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “ከፍተኛ” የሚባለውን ደረጃ ያሟሉ፤ አራት ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ካሉ 47 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራቱ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ወላጆች፣ የቀድሞ ተማሪዎች እና መምህራንን የሚያሳትፍ፤ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ሀገር አቀፍ የትምህርት ዘመቻ በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 15፤ 2015 በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው። ሪፖርቱን ለፓርላማ አባላት ያቀረቡት … [Read more...] about በኢትዮጵያ ካሉ 47 ሺህ ት/ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራት ብቻ ናቸው