* የመከላከያ ሠራዊት አባላት አጽድተው ነው ለፎቶ ያበቁት
* ስለ ጆን መዲድ መማረክ ከግንባር የተገኘ መረጃ
ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ ወይም በበረሃ የቅንጦት ስሙ ጆን መዲድ፣ ሲማረክ በድንጋጤ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” እንደነበር ጎልጉል ከግንባር የደረሰው መረጃ ያስረዳል። በዚህ የተበላሸ ሁኔታ ለሰው እንዲታይ ያልፈቀደው በጽኑ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት ለፎቶ ከመቅረቡ በፊት ልብስ እንዳስቀየረው የትግራይ የሰላም ኃይሎች ከፍተኛ አመራር ለጎልጉል ተናግረዋል።
ከፍተኛ አመራሩ እንደገለጹት፣ ጆን መዲድ በሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በተደረገበት ጥብቅ ከበባ ውስጥ በገባበት ወቅት መጀመሪያ “እጅህን ስጥ” ተብሎ ተጠይቆ ነበር። ሆኖም ጥያቄውን ውድቅ ጥቂት ለመታኮስ ሲሞክር የመጣበትን የመከላከያ ኃይል ፍጹም መቋቋም እንደማይችል በመረዳቱ በመጨረሻ ለመማረክ ተገድዷል።
የጎልጉል ምንጭ እንደገለጹት፣ ጆን መዲድ በተማረከበት ወቅት በከፍተኛ ፍርሃትና ድንጋጤ ውስጥ ስለነበር “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነበር። የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ግን እጅግ ከፍተኛ በሆነ ወታደራዊ ዲሲፒሊንና ስነ ምግባር የታነጹ በመሆናቸው፣ ታጋዩ ለፎቶ ከመቅረቡና በሕዝብ ፊት ሲወጣ መልኩና ሰብዕናው ተበላሽቶ እንዳይታይ በማሰብ ልብሱን እንዲቀይር አድርገዋል።
“መከላከያ በጣም በዲሲፒሊን የታነጸ ስለሆነ ይህንን የማዋረድ ተግባር ማድረግ አልፈለገም” ያሉት የትግራይ ሰላም ኃይል አመራር፤ ስለ መማረኩ ሁኔታም ሆነ ስለነበረበት ገጽታ እስካሁን መከላከያ ምንም የተናገረው ነገር የለም ብለዋል። ይህ በራሱ የሆነው የሠራዊቱ የላቀ ስነ ምግባርና ዲሲፒሊኑ የገደበው በመሆኑ እንጂ፣ እንደ እነሱ (እንደ ትህነግ) አሠራርና ባህርይ ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ ሌላ መልክ ይይዝ እንደነበር አመራሩ አስረድተዋል።
በትህነግ ደጋፊ የዲጂታል ወያኔ ሠራዊት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይም ከአውራምባ ታይምስ ዳዊት ከበደ የተባለ “ጆን መዲድ ሲማረክ ምንም ዓይነት ሠራዊት አልነበረውም” በማለት ያሰራጨውን ወሬ የትግራይ የሰላም ኃይሎች ከፍተኛ አመራሩ ሙሉ በሙሉ አጣጥለውታል።
አመራሩ ለሰጡት ምላሽ፤ “እኛ እንደነሱ ስላልሆንን ምንም አንላቸውም፤ የፈለጉትን የፈጠራ ወሬ ማውራት ይችላሉ። ነገር ግን ድንጋይ እንወርውር (የጦርነት ቅስቀሳ እና ጥፋት ውስጥ እንግባ) ካሉ ጉዳዩ ሌላ ይሆናል” በማለት የሚዲያውን ወሬ ውድቅ አድርገውታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Leave a Reply