በጦር መሣሪያ ንግድ፣ በኮንትሮባንድ፣ በዝርፊያ፣ ጦር በማደራጀትና በከፍተኛ ዕዳ የተዘፈቁት አቶ ወርቁ አይተነው ከአምስት ወር በፊት አገር ለቀው የወጡት የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደሆነ የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ገለጹ። “ሚዲያ ጋላቢው” የሚባሉት አቶ ወርቁ አይተነው የኅልውናውን ጦርነት “ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል ነበር” የሚሉ ይኸው “ሠርግና ምላሽ ወደ ሐዘን ተቀይሮባቸው እንዲሰወሩ አድርጓቸዋል" ሲሉ ይገልጻሉ። እነዚህ ለአቶ ወርቁ ቅርብ የሆኑ ወገኖች እንደሚሉት ሪፖርተርን ጨምሮ ዘመኑ ያፈላቸው ሚዲያዎች ሕዝብን ሲያደናግሩና የማይጨበጥ መረጃ ሲረጩ መቆየታቸው ሳያንስ “አቶ ወርቁ አገር ውስጥ መኖር ባለመቻላቸው ተሰደዱ" ሲሉ የከፋይ ጋላቢያቸው አፍ ሆነዋል። “ሲፈልግ አራክሶና አፍንጫ ይዞ የሚሞግተው የዋልታው ስሜነህ ባይፈርስ ከወርቁ አይተነውን ጋር ባደረገው … [Read more...] about ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው
operation dismantle tplf
ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ሊተላለፉ የነበሩ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ጌታሁን አስፋው ጌታሁን የተባለ እና በአማራ ክልል የህዝብ ሰላም እና ጸጥታን ለሚያውኩ ጽንፈኛ ሀይሎች የሎጀስቲክስ አቅራቢ እንደሆነ የተጠረጠረ ግለሰብ በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት የሚገኝ ቤትን በመከራየት የተለያዩ ወታደራዊ ቁሰቁሶችን በማከማቸት ለጽንፈኛ ቡድኖቹ ለማቅረብ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል ሊደረስበት ችሏል፡፡ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የጸጥታ ዘርፍ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ባካሄዱት ኦፕሬሽን ግለሰቡ ከተከራየው ቤት የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች፣ የመካከለኛ እና የረጅም ርቀት ወታደራዊ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ ትጥቆች … [Read more...] about ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው
ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደሌሎች ክልሎች በተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት "በሺዎች የሚቆጠሩ" የትግራይ ተዋጊዎች መሞታቸው፣ ሌሎች በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸዉ የክልሉ ባለስልጣናት ማስታወቃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በጦርነቱ ለሞቱ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት፣ ቤተሰቦቻቸው በቅርቡ በይፋ መርዶ ይነገራቸዋል። ዛሬ በመቐለ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩን በትክክል ባይጠቅሱም "በሺዎች የሚቆጠሩ" ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸውን አረጋግጠዋል። የሟች ቤተሰቦችን ከማርዳት በተጨማሪ መስተዳድራቸዉ ድጋፍ … [Read more...] about በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው
“ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
ዛሬ የትግራይ ክልልን እንዲያስተዳድሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቀመጡት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚታወቁባቸው የሽፍትነት ዘመን ንግግራቸው መካከል “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” የሚለው ነው። ዛሬ ደግሞ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ሆነው አራተኛውን ሙሌት ቦታው ድረስ በመሄድ አክብረዋል። ያኔ ተሸጧል ሲባል አብረው ያመኑና ዜናውን ያራገቡ መልስ ሊሰጡበት የሚገባው ጥያቄ፤ 1ኛ. ግድቡ አልተሸጠም ነበር ወይም 2ኛ. የተሸጠው ተመልሷል ወይም 3ኛ ይህ አሁን ሞልቶ የሚታየው ግድብ ከተሸጠ በኋላ በአዲስ መልክ የተሠራ ነው። መልሱን ለአቶ ጌታቸውና ደጋፊዎቻቸው እንተውና ኢትዮ12 ስለ አራተኛው ሙሌት በተመለከተ የዘገበውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግሥት የመፈረም ፍላጎት … [Read more...] about “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር አሜሪካ ስልክ ደውለው መረጃ አሳልፈው በመስጠታቸው ዋጋ የሚያስከፍል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተሰማ። አፈጉባዔው እንደተቀጣሪ ሪፖርተር በአሜሪካዊ ዜግነት አማራ ክልል ሆኖ ዜና ሲያሰራጭ የነበረው አቶ ተዋቸው ደርሶ የመታሰሩን ዜና ነው በስልክ ያሳበቁት። አቶ ተዋቸው መታሰሩን ዘሃበሻ “ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለሥልጣን ነገሩኝ” ሲል ነው የዘገበው። በዚሁ መነሻ አቶ ተዋቸውን አስመልክቶ መረጃ ለማሰባሰብ የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባደረገው ማጣራት በቀጥታ ለእስር የዳረገው ምክንያት ባይታወቅም፣ የግንኙነት ሰንሰለቱን ተከትሎ በርካታ መረጃ እንደተገኘበት ለማወቅ ተችሏል። ሰላማዊ መንገድን አማራጭ አድርገው ከማይከተሉ ኃይላት አመራሮች ጋር ግንኙነት አለው የሚለው ግን ለመታሰሩ ከተነገሩት ምክንያቶች ገዝፎ የወጣው … [Read more...] about አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ
ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ?
የአባይ ግድብን በተመለከተ ዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ” ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲፈርሙ ተጽዕኖ እየተደረጉና ወደ ፊርማውም እየሄዱ ነው የሚል እንደምታ ያለው ዘገባ ባወጣ ጊዜ አንድ የጎልጉል ተከታታይ የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ የአጸፋ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በወቅቱ የውሃ ሃብት ባለሙያ መሆናቸውን ጠቅሰው February 6, 2020 “ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ” በሚል ርዕስ ምላሻቸውን የጻፉት ግለሰብ ያኔ የጻፉት መጣጥፍ በድጋሚ እንዲወጣላቸውና በወቅቱ ዋዜማ ሬዲዮ አለኝ ያለውን ሰነድ ይፋ እንዲደርግ ጥያቄ አቅርበዋል። ትላንት መከናወኑ ከተነገረለት 4ኛው የውሃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ጥያቄውን ማቅረቡ አሳማኝ ሆኖ ስላገኘነው ለሚዲው የጸሐፊውን መልዕክት እያደረስን መጣጥፉን ከዚህ በታች በድጋሚ … [Read more...] about ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ?
የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት
“ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል ድረስ እሄዳለሁ” በሚለው ሕዝብን የናቀና አገርን ያዋረደ ንግግር የሚታወቁት የአሁኑ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአስተዳዳሪነት የተሾሙባት ትግራይ እየፈረሰች መሆኑን በራሳቸው አንደበት አረጋገጡ። ቀደም ባሉት ዓመታት የትህነግ ሰዎችና አብረዋቸው የሚሠሩ ምሥጢረኞች፣ እንዲሁም የሚታወቁ ባለ ብሮች ብቻ የሚያውቋቸው የግል እስር ቤቶች በአዲስ አበባና በአንዳንድ ክልልሎች እንደነበሩ ይታወሳል። በነዚህ እስር ቤቶች የሚታሰሩ በድርድር ጠቀም ያለ ብር ከፍለው የሚለቀቁ ሲሆን እንደ አሁኑ ሚዲያ ባለመፍላቱ ይፋ አይሆንም ነበር። ይሁን እንጂ በሾርኔ በሚታወቁ ዓምዶች ፍንጭ ይሰጥ ነበር። በወቅቱ ደኅንነቱ የራሱ ልዩ እስር ቤቶች እንዳሉት ቢታወቅም የግል እስር ቤቶቹ ግን በመንግሥት መዋቅር ሥራ ባሉ ወይም በነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የሚተዳደር ኃላፊነቱ … [Read more...] about የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት
ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በሕገ-ወጥ መንገድ በመኪና ሻግ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ። በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመኪና ሻግ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭነው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለጊዜው ባለቤቱ ባልታወቀ ተሽከርካሪ 202 ፍየሎችን ከላይ፣ ከሥር ደግሞ በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ መድሃኒቶችን እና የብር ጌጣጌጦችን በሻግ ጭነው ከያቤሎ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ብርጭቆ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደደረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር … [Read more...] about ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ
ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል
የገፊና ጎታች ሴራ፣ የአማራ ሕዝብ መከራ ክልሉ የፖለቲካ ቧልት እየበላው ነው የአማራ ክልል የራሱን መሪዎች በመብላት ሤራ ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በተለየ መታወቂያው ነው። የአማራ ክልል አሁን ላይ በፖለቲካ አመለካከት ሳቢያ ሰዎች የሚገደሉበት ክልል ሆኗል። አማራ ክልል ላይ በተደጋጋሚ የሚስተዋለው መጠፋፋትና ይህንኑ በማወደስ የሚያራግቡት ክልሉን "ለፖለቲካ ቧልት" ዳርገውታል እየተባለ ነው። "የገፊና ጎታች ፖለቲካ መሃል ሜዳ" የሚባለው የአማራ ክልል መሪዎቹ እንዲገደሉ የሚያቅዱ፣ ግድያውን የሚያቀነባብሩ፣ ግድያውን የሚፈጽሙ፣ ግድያው ሲፈጸም ወደ ሌላ በመጠቆም ሕዝብ እንዲቆጣ የሚያደርጉ ተዋንያኖች የሚተራመሱበት እንደሆነ በርካታ መረጃ በማንሳት የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም። ከሁሉም በላይ በፍረጃና ማጠልሸት ላይ አተኩረው የሚሠሩት ሚዲያዎች "የገፊና ጎታች" ፖለቲካው ፊት … [Read more...] about ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል
ጀብደኛው
አንድ ሽማግሌ የነገሩኝ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሰውዬው ጀግና ነኝ፣ አንበሳ በጡጫ ነብርን በእርግጫ እገላለሁ እያለ ይጎርራል። በኋላ ራሱ ደጋግሞ ያወራውን ጉራ እውነት ነው ብሎ ራሱ አመነው። አምኖም አልቀረ በጉራው የተሳቡ፣ በወሬው የተሰባሰቡ፣ አድናቂዎቹን አስከትሎ በረሃ ወረደ። እሱ ጀብድ ሊሠራ ሌላው ጀብድ ሊያወራ፣ ምን ለምን አብረው አዘገሙ። አድናቂዎቹን ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ አስቀመጠና "ዛሬ ሶምሶንን በዓይናችሁ ታያላችሁ" አላቸው። እነርሱም አድንቀውና አዳምቀው እንዴት እንደሚያወሩት እያሰቡ ወደ አንበሳ መንጋ የሚወርደውን ጀብደኛ በማዶ ይመለከቱ ያዙ። ወረደ ጀብደኛው። አንበሶች ሰብሰብ ብለው ተኝተዋል። በሩቁ ድንጋይ ወረወረባቸው። ሁሉም አንበሶች ቀና ቀና አሉ። አንዱ በድንጋይ የተመታ ደቦል ዘሎ ወጣበትና በቅጽበት ሌሎች ገነጣጠሉት። ታሪኩም ከጄት ፈጥኖ ከውኃ ቀጥኖ … [Read more...] about ጀብደኛው