ለዘመናት የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤትን ከኢትዮጵያ ለማንሳት እጅግ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። ይቀርቡ የነበሩት ምክን ያቶች ውሃ የማይቋጥሩ ሆነው በመገኘታቸው ሁሉም ስኬት እንደናፈቃቸው መና ሆነው ቀርተዋል። ሙከራው ግን አላቆመም፤ አሁንም ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የወንበዴ ቡድን ጋር ጦርነት የገጠመች ጊዜ ይኸው አጀንዳ ቀጠለ። ጦርነቱ ከነበረው በርካታ ድብቅ ዓላማዎች በዋነኛነት የሚጥቀሰው ይህ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይመሰክራሉ። በተለይ በኮቪድ ምክን ያት የኅብረቱ ስብሰባ ለሁለት ዓመታት በመስተጓጎሉ በዚያ ከኢትዮጵያ ምድር ተረስቶ እንዲቀር ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም። በተለይ የሰሜኑ ጦርነት በአገሪቱ መረጋጋት የለም ለሚለው እመክንዮ እንደ ማሳያ ተቆጥሮ ስብሰባው እንዳይካሄድ ከፍተኛ ጫና፣ ግፊት ሲደረግ በነበረበት ወቅት … [Read more...] about የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ
Slider
የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
የኮማንዶ ብርጌዱ የተሣካ የተልዕኮ አፈፃፀሙ ታይቶና ተገምግሞ በ1992 ዓ.ም በክፍለጦር ደረጃ ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ከክፍለጦር በላይ ሆኖ መደራጀቱም እንዲሁ፡፡ በሀገራችን ላይ የሚፈፀም ማንኛውንም ትንኮሳ መመከት እና መደምሰስ የሚችል አደረጃጀት ለመፍጠር በማሰብ የልዩ ኃይልና የአየር ወለድ አሃዱዎችን በማሥፋት የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የሚለውን ስያሜ እና አደረጃጀት አሁን ላይም ይዞ ይገኛል፡፡ የሚሠጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በእምነት የሚፈፅምና በከፍተኛ ፅናት ዘብ የሚቆም እንዲሁም በተሰማራበት የውጊያ ውሎ የውጊያው ማርሽ ቀያሪ እና አይበገሬ ሠራዊት በመገንባት ባሳለፍናቸው ዘመቻዎች አኩሪ የጀግንነት ገድል እንደ ዕዝ በመፈፀም የላቀ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ሥር ካሉት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ … [Read more...] about የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ
ከአራት ሰዎች አንድ ሰው የችግሩ ሰለባ እንደሚሆን ተመላክቷል በኢትዮጽያ የዜጎች ከፍተኛ የጤና ጠንቅ ከሆኑ መካከል የአእምሮ ጤና እክል መሆኑ ተመላክቷል። የሕመሙ ተጠቂዎችን በቅርበት የሚረዳቸው በማጣት እና ተገቢ የሆነ የሕክምና ክትትል ባለማግኘት ለከፋ ችግር እንደሚዳረጉ ተጠቁሟል፡፡ በአማኑኤል ስቼሻላይዝድ ሆስፒታል የተመላላሽ ሕክምና ክፍል ኃላፊ እና የተቀናጀ የአዕምሮ ሕመም ሕክምና ከፍተኛ ባለሙያው ሳሙኤል ቶሎሳ፤ በማሕበረሰቡ ዘንድ ለአእምሮ ጤና ያለው አመለካከት ዝቅተኛ መሆኑን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ የሕመሙ ተጠቂዎች እራሳቸውን መቆጣጠር በማይችሉበት ደረጃ የደረሰን የጤና እክል ብቻ ልክ እንደ አእምሮ ሕመም በመቁጠራቸው ሳቢያ በዝቅተኛ የአእምሮ ጤና እክል ውስጥ የሚያልፉ ዜጎች መኖራቸው እንደሚዘነጋም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ 27 … [Read more...] about በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ
የኢትዮጵያ ወርቅ የት ገባ?
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት የወርቅ ምርት “በከፍተኛ መጠን” መቀነሱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናገሩ። የባንኩ ገዢ በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ጥብቅ የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊስ መከተል አለመቻሉን ገልጸዋል። ዶ/ር ይናገር ይህን ያሉት የብሔራዊ ባንክን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት፤ ለፓርላማ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሐሙስ ህዳር 29 ባቀረቡበት ወቅት ነው። የባንኩ ገዢ በዚሁ ሪፖርታቸው፤ በሩብ ዓመቱ የነበረውን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ዳስሰዋል። የሩብ ዓመቱ የወጪ ንግድ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር “መጠነኛ ጭማሪ” ማሳየቱን ያነሱት ዶ/ር ይናገር፤ ገቢው “በተወሰኑ ዘርፎች ላይ” የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገሪቱ ላገኘችው ገቢ “ከፍተኛውን ድርሻ” የያዙት አበባ እና ቡና መሆናቸውን … [Read more...] about የኢትዮጵያ ወርቅ የት ገባ?
ሌባ እንዲይዝ ተሹሞ የነበረው ሌባ ሆኖ ተያዘ
የፖለቲካው መዋቅር ውስጥ ያሉትን ሌቦች የመያዙ ተግባር ይጠናከር የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ። ይህ የተገለፀው በቅርቡ የተቋቋመው የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ስራውን በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ የኮሚቴው አባላት ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። በአዲስ አበባም የአርሶ አደር ልጆች ወይም የልማት ተነሽ ሳይሆኑ የሆኑ በማስመሰል በሐሰት ሙስና የሰሩ ግለሰቦችም ተለይተዋል ብለዋል የብሔራዊ ኮሚቴው አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ። 175 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታና የኮንዶሚኒየም ቤት ምዝበራ የፈፀሙ እንዲሁም በፍትህ ዘርፉ ስልጣናቸውን በመጠቀም ከግለሰቦችና ከንግድ ተቋማት ጋር ለግል ጥቅማቸው ሲሰሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም … [Read more...] about ሌባ እንዲይዝ ተሹሞ የነበረው ሌባ ሆኖ ተያዘ
“ከሩቁ የሚፈራ የመከላከያ ሠራዊት ፈጥረናል”
ሳይዋጋ የሚያሸንፍ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት እየገነባን ነው የመከላከያ ሠራዊት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ "የጥንካሪያችን ምንጭ ሕዝባችን ነው" በሚል መልዕክት የፓናል ውይይት ተካሄደ። በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አብርሐም በላይ (ዶክተር)፣ አሁን በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ከፍተኛ አቅም ተፈጥሯል፤ ከሩቁ የሚፈራ መከላከያ ሠራዊት ፈጥረናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ጠላቶች ሳንቆም ሊጥሉን ሞክረዋል፤ አሁን ቆመን ማንም ሊነቀንቀን የማይችልበት ደረጃ ደርሰናል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በአሁኑ ጊዜ ሳይዋጋ የሚያሸንፍ ሠራዊት መገንባት መቻሉን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የግዛት አንድነቷ በማንም እንደማይሸረፍ በመስዋዕትነት የሚያረጋግጥ ጀግና ወታደር ያላት ሀገር እንደሆነች የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ይህን በተግባር እያረጋገጠ … [Read more...] about “ከሩቁ የሚፈራ የመከላከያ ሠራዊት ፈጥረናል”
ከ፴ ዓመት በኋላ በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንደ ትህነግ
አደራውን ለባለ አደራው ሰጥተው የልማት ሥራዎችን እየተዘዋወሩ የሚመለክቱትና የአረንጓዴ ዘመቻ መመሪያ እየሰጡ ያሉ ዐቢይ አሕመድ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ የወትሮ ጭንቀትና ያለመመቸት ስሜት ፊታቸው ላይ አይታይም። በመንግሥት የዘመኑ ዕቅድ ላይም በተያዘው ዓመት አስተማማኝ ሰላም እንደሚሰፍን ተመልክቷል። ዐቢይ አህመድ ለበዓላት ባስተላለፉት መልዕክቶቻቸውና በፕሮጀክት ምረቃ ላይ “አትጠራጠሩ የሰሜኑ ጦርነት ያበቃል” ብለዋል። “አሁን” ሲሉ መረጃ የሰጡ ወገኖች “አሁን የሰኞው ንግግር ልክ እንደ 1991ዓም (እኤአ) ድርድር ዋጋ የለውም። ምክንያቱም የትህነግ አመራሮች ጊዜ የሚፈጁበት አንዳችም የድርድር ቀብድ የላቸውም”። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቴድሮስ አድሃኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ደውሎ መማጸኑ ተሰምቷል። ምላሽም አግኝቷል። ከመቀሌ ውጪ ቀሪዋ ትልቅ ከተማ አዲግራትና አድዋ … [Read more...] about ከ፴ ዓመት በኋላ በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንደ ትህነግ
“ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
የትህነግ 10 በደሎች - በተለይ በአማራ ሕዝብ! "ትህነግ"... (ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ሕዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ትህነግ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ። የትህነግ መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ትህነግ በተለይ በአማራ ሕዝብ 10 ዐበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ። 1) መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change): ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ … [Read more...] about “ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
“አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”
በአሜሪካ ኦሪጎን ጠቅላይ ግዛት እየተካሄደ ባለው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ኢትዮጵያ እንደገና ስሟ ከፍ ብሏል። በፖለቲካው የሚታየው መከፋፈልና ጥላቻ በስፖርቱ አከርካሪውን ተመትቷል። የዚህ ድል ምንጭ ምንድነው? ብለን ወደ ኋላ እንድናይ ያስገድደናል። ተወዳዳሪ የሌለው ወደፊትም የማይኖረው የጀግኖቹን ጀግና አበበ ቢቂላ ማስታወስ የግድ ይላል። አበበ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሲያሸንፍ የዓድዋ ድል ነው በድጋሚ የተበሰረው። ጣሊያኖቹም ይህንን አልካዱም። የክብር ዘበኛው ወታደር አበበ ሲያሸንፍ “ሮምን የወረረ ኢትዮጵያዊ” ብለው ዘግበውለታል። “ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ግዙፍ ጦር አዝምቶ ነበር፤ ሮምን ለመውረር ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ብቻ በቂ ሆኗል” በማለትም አትተዋል። እነ ማሞ ወልዴና እነባሻዬ ፈለቀ “ኢትዮጵያ” የሚል ቱታ ለብሰው ሲያይ ለአገሩ ተሰልፎ ስሟን ማስጠራት … [Read more...] about “አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”
ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው
በተለይ ምዕራብ ወለጋን ምሽጉ አድርጎ ከትህነግ ጋር በመሆን ንጹሐንን እየጨፈጨፈ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክረው ሸኔ ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ መሆኑ ተነገረ። ሸኔን የማጽዳት ዘመቻው ወደ ፖለቲካውና መንግሥታዊ መዋቅሩም ውስጥ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ተጠየቀ። ጎልጉል ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ጊዜ በተጠናከረ ሁኔታ በሸኔ ላይ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ ኦነግ ሸኔ ጠንካራ የሚላቸውን ይዞታዎቹን ሳይወድ በግዱ እንዲለቅ እየተደረገ ነው። በተለይ በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ በንጹሐን ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂና ለኅሊና የሚሰቀጥጥ ግድያ በፈጸመው ሸኔ ላይ አሁን ዝርዝሩን መናገር የማያስፈልግ ዘመቻ እየተካሄደበት ይገኛል። በቀጣይ ባሉት ቀናት መንግሥት በይፋ ዝርዝሩን የሚያሳውቅ ቢሆንም ዘመቻው በዋንኛነት ትኩረት ያደረገው የሸኔን ጠንካራ ምሽጎችን … [Read more...] about ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው