• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ

April 29, 2026 02:27 pm by Editor Leave a Comment

* ዳያስፖራው ራሱን ከትግሉ እያገለለ ነው 

ከሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ በተደረገ ተከታታይ ስምሪት የፋኖ ኃይል እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ። በተለይ በራያ ቆቦ ወረዳ የተደረገው ሥምሪት ባካባቢው በሚገኘው የፋኖ ኃይል የደረሰው ጉዳት መጠነ ሰፊ እንደሆነ ተመልክቷል። በፋኖ ተስፋ የቆረጠው ዳያስፖራ ከሚኖርበት ሀገር የገጠመው ችግር ተጨምሮ ለፋኖ የሚሰጠውን ድጋፍ እየቀነሰ ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ በራያ ቆቦ ወረዳ በአማያ፣ በባይባዋ፣ በፀበለት እና አካባቢው በተደረገው ተከታታይ ስምሪት የመከላከያ ሠራዊት በፋኖ ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ምት ንብረቱን፣ ትጥቁን እና ተተኳሹን በመተው ከአካባቢው ሲለቅቅ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ኮር አካል የሆነው 48ኛ ክፍለ ጦር በተጠቀሱት ቦታዎች እና ልዩ ሥፍራው “አካምባ” በሚባል ቦታ ፈጥኖ በመድረስ የፋኖው ኃይል ጥሎት እና አንጠባጥቦት የሸሸውን ንብረት በቁጥጥር ሥር አውሏዋል።  

በዚህም መሠረት፦

የ82 ሚ/ሜ ሞርተር ጥይት – 515

የ82 ሚ/ሜ ሞርተር ፊውዝ – 520

የ82 ሚ/ሜ ሞርተር ካምሱር – 43

የ12.7 ሚ/ሜ ዶሽቃ ጥይት – 818

የመትረዬስ/ብሬን ጥይት – 47080

ቆመህ ጠብቀኝ መሣሪያ – 48

የተተካይ ክላሽ ብሬን – 1

የኤኬኤም ክላሽ ማፅጃ – 137 የተገኘ መሆኑን መረጃው ይጠቁማል።

ከውስጥም ከውጪም ከፍተኛ የመበታተን አደጋ የተጋረጠበት የፋኖ ኃይል እየደረሰበት ያለውን ጫና መቋቋም እያቃተው እንደሆነ ይሰማል። በፊት ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላርና ዩሮ በቀላሉ ለመሰብሰብ ይችል የነበረው የውጪው ደጋፊ በተለያዩ ምክንያቶች እጁን ወደ ኪስ ማስገባት እየቸገረው መጥቷል። ከፋኖ እየከዳ ለመንግሥት እጁን የሚሰጠው ሠራዊትና አመራር ጉዳይም ሌላው ተስፋ አስቆራጭ ሆኗል።

በተለይ በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የታየና ለፋኖ የገቢ ማሰባሰቢያ ተብሎ የተጠራ ስብሰባ “በቂ ሰው ስላልተገኘ” በሚል መበተኑ ተበትኗል። በሥፍራው የነበሩና በሁኔታው እጅግ የተናደዱ ሰዎች በስብሰባ ጠሪዎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደሞከሩና ይህንን የተመለከቱትም ወዲያውኑ ጸጥታ አስከባሪ በመጥራት ሁኔታውን ለመቆጣጠር ችለዋል።

ሰለሞን ቦጋለ የተባለ ግለሰብ የፋኖ ደጋፊ መሆኑ ተጠቅሶ ወደ ኢትዮጵያ ከተጠረዘና በተለይ በዚሁ ዜና ላይ ፋኖ ሦስተኛ ደረጃ አሸባሪ ተብሎ ከተጠቀሰ በኋላ የፋኖ ደጋፊ ደብቁኝ እያለ መምጣቱ በገሃድ የሚታይ ሐቅ ሆኗል። የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ጭምር ዜግነታቸውን እየገፈፈ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ መጀመሩ በማንኛውም ቡድን የዳያስፖራ ደጋፊ ዘንድ ከፍተኛ ሽብር ፈጥሯል።

በተለይ ዱሮ ሶማሌያዊ ነኝ፣ የመናዊ ነኝ፣ ሱዳናዊ ነኝ እያሉ አሜሪካ ጥገኝነት የጠየቁና ዜግነት ያገኙ በርካታዎች ሊመለሱ የሚችሉበትን ሀገር ሲያስቡት የፈጠረባቸው ጭንቀት እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይፋ ያልሆኑ በየአካባቢው በሚደረጉ ኢመደበኛ ስብሰባዎች ላይ የሚሰማ ትርክት ሆኗል። የገቢ ማሰባሰቢያ ስብሰባዎች መሰረዛቸውና በአካል የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ወደ ድረገጽ ትዕይንት መቀየራቸው ከዚሁ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በስፋት ይሰማል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ      

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, Fano, North Wollo Fano, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule