• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ

May 6, 2026 11:55 pm by Editor Leave a Comment

 የፌዴራል ፖሊስ በሪፖርተር ላይ ያወጣው መግለጫ የሪፖርተርንና የባለቤቱን ማንነት እንዲሁም ስሑት ሥራውን ያጋለጠ ነው። እንደ ፌዴራል ፖሊስ መግለጫ ሪፖርተር “ስውር ተልዕኮ የተንፀባረቀበት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ፈፅሟል”። የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሪፖርተር ጋዜጣ “ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ አርቲስቶች ከ98 ቢሊየን ብር በላይ መዝረፋቸው በኦዲት ምርመራ መረጋገጡ ተነገረ” በሚል የዘገበው መረጃ የተዛባ መሆኑን አስታወቀ

ሪፖርተር ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለተከበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና የፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ሪፖርቱን ለማስረዳት በማስታወሻነት የተጠቀመበትን ጥቅል መረጃ መነሻ በማድረግ፣ ጠቅላላ ይዘቱን በአግባቡ ሳይረዳ እና በተቋሙ ስትራቴጂክ አመራሮች የቀረበውን  ዝርዝር ማብራሪያ መጠቀም እየቻለ እውነታውን ወደ ጎን በመተው ሕዝብን በሚያሳስት መልኩ የተዛባ መረጃ በጋዜጣው የፊት ገፅ ላይ ይዞ ወጥቷል።  

ሪፖርተር ጋዜጣ ከአንድ ቁንፅል ሀሳብ በመነሳት በማይገባ የሒሳብ ስሌት ውስጥ በመግባት 133 ሚሊየን 903 ሺህ 384 ዶላር ወደ ብር በመቀየር እና ከ78 ቢሊየን ብር ጋር በመደመር ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ አርቲስቶች ከ98 ቢሊየን ብር በላይ ዘርፈዋል በማለት ያሰራጨው ዘገባ ፍፁም የተሳሳተ ነው። 

እውነታው ግን 78 ቢሊየን ብር በየወንጀሉ ዓይነት ሲተነተን፦ 7 ቢሊየን ብር በሙስና ወንጀሎች (ከመዳበሪያ ግዥ እና ከባንክ ማጭበርበር ጋር የተያያዘውን ጨምሮ)፣ 6.4 ቢሊየን ብር በጉምሩክና ታክስ ወንጀሎች (ታክስ ስወራንና የኮንትሮባንድ ወንጀሎችን ጨምሮ)፣ 13.7 ቢሊየን ብር በተደራጁና ልዩ ልዩ ወንጀሎች (ሕገ-ወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም የማዕድን ዝውውርን ጨምሮ)፣ 44.9 ቢሊየን ብር በፋይናንስ እና ንግድ ነክ ወንጀሎች (ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች የተሳተፉበት ሕገ-ወጥ ሐዋላ፣ የሳይበር ወንጀል፣ የንግድ ነክ ወንጀል በተለይም ከፊንቴክ ድርጅት እና ከአርቲስቶች ጋር በተያያዘ በ1,400 ሰዎች ላይ የደረሰውን 1.7 ቢሊየን ብር ጉዳትን ጨምሮ) እንዲሁም 6 ቢሊየን ብር የሚገመት በሽብርና በሌሎች የተለያዩ ወንጀሎች ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ማዳን የተቻለ እና አልፎም በደረሰ ጉዳት ላይም ምርመራ ማጣራቱን በዝርዝር ሪፖርቱ ተመላክቷል።

በተመሳሳይ ለተከበረው ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርት ላይ 133 ሚሊየን 903 ሺህ 384 ዶላር ላይ ምርመራ ተጣርቶ ጉዳቱን ማዳን መቻሉ በዝርዝር ተገልጾ እያለ፤ ሪፖርተር ጋዜጣ ግን እንደተዘረፈ አድርጎ ለሕዝብ ያሰራጨው ዘገባ ከእውነታው የራቀና የተዛባ ነው።

ከላይ ከተዘረዘሩት ወንጀሎች ጋር በተያያዘ በ9 ወር ውስጥ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ 1,518 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ተጣርቶባቸውና ክስ ተመስረቶባቸው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ተደርጓል።

እነዚህ ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱት ወንጀሎችን በተመለከተ ፖሊስ በየጊዜው የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ለሕዝብ ሲያሳውቅ እንደነበር ይታወቃል።

እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ የሪፖርተር ጋዜጣ መረጃውን በትክክል ለህዝብ ማድረስ ሲገባው አዲስ ነገር እንደተፈጠረ እና ኀብረተሰቡ እንደ ተዘረፈ አድርጎ ከጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ያፈነገጠና የጋዜጣው ስውር ተልዕኮ የተንፀባረቀበት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ፈፅሟል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሐሰተኛና የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር የፈጸመውን ሪፖርተር ጋዜጣን በሕግ አግባብ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውቋል።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፥ ‎አዲስ አበባ፥ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: Amare Aregawi, ethiopian terrorists, federal police, operation dismantle tplf, Reporter, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule