* ሕዝቡን ሲያሰቃይ የነበረው ጽምዶ እየተበታተነ ነው
እየተካሄደ ባለው ውጊያ ከትህነግ ጎን ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች ከባድ ምት አስተናግደዋል። በውጊያው ወቅት በርካታ የሻቢያ ታጣቂዎች የተደመሰሱ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በቁጥጥር ሥር ውለው ተማርከዋል።
ለጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት፣ የተማረኩትንና የተደመሰሱትን የሻቢያ ታጣቂዎች ሙሉ ማንነትና ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል። በአሁኑ ወቅት የደረሰባቸውን ከባድ ሽንፈት ተከትሎ፣ በርካታ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በድንጋጤ ወደ ኤርትራ እየሸሹ የሚገኙ ሲሆን፣ በድንበር አካባቢ የነበሩ የትህነግ እና የሻዕቢያ ታጣቂዎችም በከፍተኛ ሁኔታ ወደኋላ እያፈገፈጉ ይገኛሉ።
የትግራይን ሕዝብ ለዓመታት ሲጨፈጭፍ፣ ሴቶችን ሲደፍር፣ ንብረትና መሠረተ ልማት ሲያወድም የነበረው የሻዕቢያ ሠራዊት ዛሬ ከትህነግ ጋር በጥቅም ተጋርቶ በድጋሚ ሕዝቡን ለሞትና ለእንግልት ሲዳርግ ማየቱ በስፋት አሳዝኗል። ትህነግ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል ቀደም ሲል የትግራይን ሕዝብ ያስጨፈጨፈውን አካል በጽምዶ የቅርብ አጋር በማድረግ ሕዝቡን ለጥፋት አሳልፎ መስጠቱ የትግራይ ሕዝብ የሚገባው አይደለም።
ይህ በህዝብ ላይ የሚፈጸም በደልና ጭቆና በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በትህነግ እና በሻዕቢያ ግፍና መከራ የመረረው የትግራይ ሕዝብ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል (TPF) ገብተው አካባቢውን በቁጥጥር ሥር እንዲያውሉ እና ሰላም እንዲመልሱ በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Leave a Reply