• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ

October 27, 2026 11:14 pm by Editor Leave a Comment

የሻዕቢያ ቡድን የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በሁሉም አቅጣጫዎች ለማደፍረስና ሀገሪቱን ለማፍረስ ቀንና ሌሊት ሙሉ አቅሙን አሰባስቦ እየሠራ መሆኑን የሚያጋልጥ ሚስጢራዊ መረጃ ለጎልጉል ደርሷል። ለድረ-ገጻችን የደረሰው ይኸው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ የሻዕቢያ መዋቅር በውጭ አገር ከሚገኙ ደጋፊዎቹ ጀምሮ በአገር ውስጥ እስከሚዘረጉ የስለላ መረቦች ድረስ ሰፊ ስምሪት በመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ለጎልጉል የደረሰው መረጃ የሴራውን አደገኛነት በማስመልከት የሚከተሉትን አበይት ነጥቦች በዝርዝር ያጋልጣል፦

የዲያስፖራው ቁልፍ ሚና እና የቴክኖሎጂ ዝግጅት

በዲያስፖራ የሚኖሩ የሻዕቢያ ደጋፊዎች በገንዘብና በቴክኖሎጂ እውቀት የሰለጠኑ ልጆቻቸውን በስፋት እያሰማሩ ይገኛሉ። እነዚህ በዘመናዊ እውቀት የበለጸጉ ወጣቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚደረገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውስጥ በቴክኖሎጂውና በፋይናንስ ረገድ ሙሉ ዝግጅት አድርገው ወደ ተግባር መግባታቸው ተገልጿል። ወደዚህ ያልገቡትም እንዲገቡ ጥሪ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የ“ካሚካዜ” ድሮኖች ግዢ እና የመሠረተ ልማት ስጋት

በጣም አሳሳቢ ከሆኑት ዝግጅቶች መካከል የሻዕቢያ ቡድን “ካሚካዜ” (Kamikaze) የተባሉ አጥፊ ድሮኖችን በስፋት የመግዛቱ ጉዳይ ነው። ቡድኑ እነዚህን የጭፍጨፋና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸውን ድሮኖች በመጠቀም የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስና ሀገሪቱን ለማሽመድመድ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ሊታወቅ ይገባል ሲል መረጃው ያስጠነቅቃል። ከዚህ ሌላ ድሮኖቹን ከኤርትራ ለመላክ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውስጥ ለማድረግና ወደ ሀገር ውስጥ በተለያዩ ዘዴዎች ማስገባት የሴራው አንዱ እቅድ ነው።

በአገር ውስጥ የዘር ግጭት የመቀስቀስ ስትራቴጂ

ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የውስጥ የፖለቲካ ሁኔታ በመጠቀም፣ የዘር ግጭትን በሁሉም አቅጣጫ ለማስነሳት ከውጭ የተደራጀ ልዩ ኃይል አቋቁሟል። ይህ ከውጭ የተቀናጀ ኃይል በአገር ውስጥ ያሉትን ስንጥቆች በማስፋት የእርስ በርስ ግጭት እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተልዕኮ ተሰጥቶታል። ሰሞኑን በአርሲና በሞያሌ የተከሰቱትን ግጭቶች ሰነዱ ለአብነት ያነሳል።

የስለላ መዋቅር መስፋፋት እና ስደተኞችን ለሽፋን መጠቀም

ቡድኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የስለላ መዋቅር በከፍተኛ ደረጃ እያሰፋ ይገኛል። ለዚህ ተግባር ማሳኪያ ይሆን ዘንድ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ኤርትራውያን ዜጎችን (ስደተኞችን) እንደ ሽፋን በመጠቀም ሙሉ የስለላ ጥናት ለማካሄድ ታስቧል። መረጃው እንደሚያረጋግጠው፣ ለእነዚህ ግለሰቦች የተሰጠው ልዩ የስለላና የደህንነት ስልጠና ትምህርት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል።

ይህ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ የሻዕቢያ ቡድን የኢትዮጵያን ሰላም ለማናጋት የያዘው እቅድ ከመቼውም ጊዜ በላይ የረቀቀ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ሁሉንም አቅጣጫዎች ያካተተ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን፣ ጉዳዩ ከሀገራዊ ደህንነት አንጻር ከፍተኛ ጥንቃቄና ክትትል የሚሻ መሆኑን አመላክቷል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Eritrea Prepares Major Offensive Against Ethiopia Using Kamikaze Drones and Ethnic Sabotage

Golgul has obtained leaked intelligence exposing a comprehensive, round-the-clock campaign by the Shabia (Eritrea) regime aimed at destabilizing Ethiopia’s peace and security. According to the document, the plot spans a massive operational network, mobilizing overseas diaspora networks and establishing deep-cover espionage rings directly inside the country.

The leaked briefing highlights several critical vulnerabilities and active threats:

Diaspora Mobilization and Technological Weaponization

The regime is actively leveraging its diaspora community, specifically targeting and deploying tech-savvy, well-funded youth. These individuals have reportedly been weaponized to provide the financial and technological backbone needed to advance the destabilization campaign. A sweeping recruitment drive is currently underway to draw more diaspora youth into active operations.

Acquisition of Kamikaze Drones Threatens Key Infrastructure

Among the most alarming revelations is Shabia’s large-scale acquisition of “Kamikaze” (suicide) drones. Intelligence warns that these lethal assets are slated for high-impact strikes against Ethiopia’s strategic infrastructure, aiming to effectively paralyze the nation. Crucially, the plan does not rely on launching these drones from Eritrean soil; instead, the plot involves smuggling the hardware into Ethiopia through various covert channels to execute strikes from within the borders.

Engineered Ethnic Conflicts as a Core Strategy

Exploiting existing political fault lines, Shabia has established a specialized external task force designed to ignite widespread ethnic violence across Ethiopia. This foreign-coordinated unit is tasked with widening local grievances to trigger full-scale internal clashes. The document specifically points to recent outbreaks of violence in Arsi and Moyale as live examples of this strategy in motion.

Expansion of Spy Rings Using Refugee Cover

The regime is aggressively expanding its intelligence footprint inside Ethiopia. To bypass security screening, the network plans to use incoming Eritrean refugees as operational cover to conduct extensive espionage and reconnaissance. The intelligence confirms that selected individuals have already completed rigorous, specialized espionage and security training and have begun active field deployment.

The leaked document paints a picture of a highly sophisticated, multi-front, and technologically driven campaign to disrupt Ethiopia’s stability—one that demands immediate national security focus and heightened vigilance.

Golgul Amharic Internet Newspaper

Filed Under: Left Column, News Tagged With: eplf, ethiopian terrorists, Isayas Afewerki, kamakazee, operation dismantle tplf, shabiya, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule