• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው!

November 17, 2026 11:54 pm by Editor Leave a Comment

በበርካታ ጉዳዮች መጨመላለቅ፣ ቧልት መጫወት፣ መደለል፣ በማህበራዊ ሚዲያ እንጭጭ አሳቢዎች አማካይነት ድራማ መስራት፣ ተቧድኖ ማሴር፣ እዛም እዚህም ሹመኛ ላይ እየተንጠላጠሉ፣ የተለያዩ ህጋዊ ተቋማት ውስጥ እየተወሸቁ ወዘተ እያስፈራሩም ጭምር ውንብድና መፈጸም እና የቴሌኮም ኔትዎርኮችና የዳታ መጋዘኖች ዙሪያ የሚደረግ ቁማር ተመሳሳይ እንደሆኑ አድርገን የምናስብ ካለን አልገባንም። ገብቶንም ዝምታን የመረጥን ካለን “ኢትዮጵያዊ” ልንባል አንችልም። ተቆጣጣሪ አካል ሆነን ቸል የምንል ካለን ጣጣው “በዘመቻ/ኦፐሬሽን” የሚታፈስ አይደለም። ይህን አስተያየት ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከላይ በርዕሱ እንደጠቆምኩት፣ ጉዳዩ ከንትርክም፣ ከመካሰስም፣ ከቲፎዞ ጩኸትና ከችሎት ጀርባ ባለ ማመቻመች፣ እንዲሁም ሴራ የሚዘጋ አጀንዳ በመሆኑ ነው።

እንደ መግቢያ

የአንድ ሀገር የቴሌኮም መሠረተ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ጌትዌይ፣ የዳታ ማዕከላትና የዲጂታል መረጃ ሥርዓቶች በቀላሉ የንግድ ሀብቶች ተብለው እንደ ማናቸውን የንግድ አይነቶች በቀላሉ ሊታዩ አይችሉም። ይህ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ዓለም የሚያውቀው የዘመኑ የደህንነት ጉዳይ ሀ፣ ሁ፣ … ነው።

አገልግሎቶቹ የባንክና የፋይናንስ ሥርዓት፣ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የጤናና የትምህርት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃንና የሀገር ደህንነት የሚመሠረቱባቸው ወሳኝ የብሔራዊ መሠረተ ልማቶች ናቸውና የቁጥጥሩ ቁልፍ በተሳሳቱ አካላት እጅ ከገባ የሚያስከትለው ጉዳት ከንግድ ኪሳራ በላይ ሊሆን ይችላል፤ ነውም!

የዓለም ሳይበር ደህንነት ታሪክ “Scattered Spider” እና “Silence” ያሉ የወንጀል ቡድኖች የዲጂታል ሥርዓቶችንና የፋይናንስ መሠረተ ልማቶችን በመጠቀም ምን ያህል ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ዓለም በየቀኑ ብዙ ጉድ እያስኮመኮመችን ነው። እኛም ደሴት አይደለንም እና ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ካልተደረገ ይህ አደጋ ለኢትዮጵያም ስጋት የማይሆንበት ምክንያት የለም። በኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር የሚመለከታቸው የአገራችን የደህንነት ተቋማት “አከሸፍን” እያሉ የሚነግሩን መረጃዎች በወጉ ለሚከታተል፣ ይህንን ዘርፍ ማንም ይሁን ማን “ቀበኞች” ከተቆጣጠሩት ምን ሊከተል እንደሚችል ለመገመት ጠቢብ መሆን የሚጠይቅ አይመስለኝም። ይህን ካልኩ ወደ ዋናው ጉዳዬ ላምራ።

ዌብስፕሪክስ ማን ነው?

ዌብስፕሪክስ (WebSprix) በ2013 ዓ.ም. የተመሰረተ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ያደረገ በኢትዮጵያ የግል የኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ ነው። ኩባንያው በመሥራቹና በዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ዳዊት ብርሃኑ አመራር የተለያዩ የዲጂታል መሠረተ ልማትና የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን እያቀረበ ይገኛል። ዌብስፕሪክስ ለመኖሪያ ቤቶችና ለንግድ ተቋማት የፋይበር ኢንተርኔት፣ የክላውድ ኮምፒውቲንግና የዳታ ሆስቲንግ፣ የኢንተርኔት ቴሌቪዥን (IPTV)፣ የድርጅት ኔትወርክና ቪፒኤን (VPN) እንዲሁም የድምፅና የአጭር ጽሑፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ያቀርባል።

በተለይም መረጃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከማቹና እንዲስተናገዱ የሚያስችል የሀገር ውስጥ የክላውድ መሠረተ ልማት በማቋቋም ረገድ እየሠራ ይገኛል። ይህም በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት፣ የመረጃ ሉዓላዊነትና የግል ዘርፉ በቴሌኮም መሠረተ ልማት ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ እርምጃ ነው። ዝርዝር ጉዳዩን እና የአክሲዮን ድርሻውን ለጽሁፌ መነሻ ያደረኩትን “ጎልጉል” — “ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት” ሲል ያተመውን መረጃ ይመልከቱ።

ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት

ተራ ጸብና የሽርክና ጉዳይ አይታየኝም

እንደገባኝ ባለአክሲዮኖቹ ባለሙያውን፣ የሃሳቡን ባለቤትና መስራቹን “ይባረሩልን” በማለት በውልና ማስረጃ አዲስ ቃለ ጉባኤ አጸድቀው የሄዱት ዌብስፕሪክስን ለኢትዮጵያ አማራጭ የጌትዌይ ግንባታ መገንባት እንዲችል ፈቃድ አግኝቶ ወይም በሌላ መልኩ ሌላ ራሱን የቻለ፣ የኢትዮቴሌኮምን ጌትዌይ የማይጠቀም ሌላ “ቴሌኮም” ለመሆን እየተንደርደረ ባለበት ወቅት ላይ ነው። እኔንም ያነቃኝና እንደ ዜጋ ጊዜ ወስጄ ጉዳዩን እንድመረምረው ያደረገኝ ይኸው ጉዳይ ነው።

በዌብስፕሪክስ ውስጥ የባለቤትነትና የአመራር “ማፈናቀል” (ቃሉን ተውሼ ነው) አስመልክቶ የተነሳው ክርክር ተራ የንግድ አለመግባባት ተብሎ ሊታለፍ አይገባም ያልኩት ከላይ በጠቋቆምኩት አግባብ ነው። በተለይም በተወሰኑ ባለድርሻዎች ላይ የቀረቡ የጀርባ ታሪካቸው፣ የወንጀል ተሳትፎ፣ የፋይናንስ ምንጮችና በተለያዩ “እጆች” የሚመሯቸው ተቋሞች ጉዳይ፣ በሕግና በማስረጃ መጣራት የሚጠይቁ ቢሆኑም በዘርፉ ዙሪያ መጠነኛ እውቀቱ ላላቸው ክርክሩ እንቅልፍ የሚነሳ ሀገራዊ አጀንዳ ነው። “አይደለም” የሚለኝ ካለ እስከ ጥግ ልሟገት ዝግጁ ነኝ።

“የኢትዮጵያን የዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የባንኮችን ምሥጢራዊ መረጃ፣ የመንግሥትን ወሳኝ ሲስተሞችና የኢንተርኔት ግንኙነት ቁጥጥር ማን ይይዛል?” የሚሉትን ሀገራዊ ጉዳዮች የተሸከመ፣ ከግለሰቦች የንግድ ፍላጎት በላይ የሀገር ደህንነትን የሚመለከት በመሆኑ የዌብስፕሪክስን የባለቤትነትና የአመራር ክርክር ከሸፍጥና ከተራ የሌብነት መረብ በራቀ በገለልተኛነት፣ በማስረጃና በብሔራዊ ደህንነት መነጽር መመርመር ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ሉዓላዊነት በአንድ ኩባንያ የውስጥ ክርክር ወይም ከጀርባው ሌላ አጀንዳ ባዘለ የባለቤትነት ዝውውር ሊከናወን አይገባም የሚል አቋም አለኝ።

የዌብስፕሪክስ ጌትዌይ፣ የዳታ ቁጥጥርና የብሔራዊ ደህንነት ስጋት

የመንግሥትን የዲጂታል መሠረተ ልማት የሚያገናኝ፣ የባንኮችን የገንዘብ ሥርዓት፣ የጤናና የትምህርት ተቋማትን መረጃ እና የሚዲያ ኔትወርኮችን አጣምሮ እየሰራ ያለ ድርጅትን (ወይም መስራት የሚፈልግ ድርጅትን) በስመ ፕራይቬታይዜሽን ግልጽነት ሳይኖር “እንካችሁ” ማለት፣ የሀገሪቱን ወሳኝ ዲጂታል መሠረተ ልማት እንዲያስተዳድር መፍቀድ ከንግድ ፖሊሲ በላይ የሆነ የብሔራዊ ደህንነት ጥያቄ እንደሆነ ከቴክኖሎጂው ጎን ለጎን የሚሰበክ የዕለት ተዕለት “የቴክኖሎጂ ደህንነት ጥበብ መጀመሪያ” ነው።

በዘመናዊው ዓለም የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት በድንበር፣ በወታደራዊ ኃይልና በተፈጥሮ ሀብት ቁጥጥር ብቻ አይለካም፤ የመረጃ ሉዓላዊነት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት ቁጥጥርና የብሔራዊ ዳታ ደህንነትም የሀገር ሉዓላዊነት ወሳኝ አካላት ሆነዋል። ለዚህም ማረጋገጫው ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ በጀት መድበው ዘብ የሚያቆሙበት ቁልፉ ጉዳያቸው በመሆኑ ነው።

በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እየተስፋፋ በመጣበት፣ ባንኮች የገንዘብ አገልግሎታቸውን በዲጂታል መድረኮች እያካሄዱ፣ የመንግሥት ተቋማት የዜጎችን መረጃ ወደ ዳታ ማዕከላት እያስገቡ፣ የጤናና የትምህርት ሥርዓቶች በኔትወርክ እየተገናኙ ባሉበት ሁኔታ የቴሌኮም ጌትዌይና የክላውድ መሠረተ ልማት ቁጥጥር ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እየጎላ በመምጣቱ “ወርቅ ከመሬት ይወጣል፤ የወደፊቱ ሀብት ግን ከዳታ ይፈጠራል” የሚለውን የ21ኛውን ዘመን ብሂል እየሰማን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ያስገነቡትን የዳታ ማዕከል ሲያስመርቁ “ከተሰሩት ስራዎች ሁሉ እጅጉን የረካሁበት” ያሉትም ለዚሁ ይመስለኛል።

በዚህ ወሳኝ የብሔራዊ ደህንነት ዘርፍ የዌብስፕሪክስ (WebSprix) የቴክኖሎጂ አገልግሎት፣ የጌትዌይ ግንባታ ዕቅድ፣ የክላውድ ዳታ ማዕከልና ባለቤትነት ምንም እንኳ በህግ በተደነገገ አግባብ ፈቃድ የተሰጠው ቢሆንም አሁን ከተነሳው ክርክር አንጻር በጥልቀት መመርመር የሚገባው ጉዳይ እንደሆነ ጠቅሶ መጻፍም ሆነ መከራከር የየትኛውም ቡድን ወይም ግለሰቦች ደጋፊና ተቃዋሚ አድርጎ አያስፈርጅም። ይህን የሚያስቡ ካሉ 50 ዶላር እየተከፈላቸው ያገኙትን ጉዳይ ተገተው የሚያፈሱት በስም እንኳን ለመጥራት የማይመቹት እንቶኔዎች ናቸው።

ጉዳዩ ላይ አስረግጦ ለመውጣት ዌብስፕሪክስ የግል ድርጅት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጥያቄው ይህ ድርጅት በሀገሪቱ የዲጂታል መሠረተ ልማት ውስጥ የያዘው ሚና፣ ወደፊት የሚኖረው ተሳትፎ፣ አሁን ላይ የሚያስተዳድረው የመረጃ ወሰን፣ የባለቤትነት መዋቅሩና ከባለድርሻዎቹ ማንነትና ጀርባ አንጻር የብሔራዊ ደህንነታችን ጉዳይ በወጉ ተጠንቶ የሚሰላ እንጂ፣ “እገሌ ይባረር” ከሚለው የተለመደ የባለድርሻዎች ክርክር ተርታ የሚመደብ አይሆንም። የ”እገሌ ይባረርልን” ጥያቄው የተነሳበት ወቅትና ሀገሪቱ ያለችበት አሁናዊ ሁኔታም ከላይ ከተዘረዘረው ጉዳይ አንጻር ሊጤን የሚገባው ይሆናል. እስኪ አንዳንድ ጉዳዮችን እንይ፦

1. ጌትዌይ፡ የሀገር ዲጂታል መግቢያና መውጫ

የኢንተርኔት ጌትዌይ ማለት ከሀገር ውስጥ ኔትወርኮች ወደ ዓለም አቀፍ ኢንተርኔት የሚደረግን ግንኙነት የሚያስተሳስር ወሳኝ መሠረተ ልማት ነው። የዚህ ሥርዓት አስተዳደር ከቴክኒካዊ አገልግሎት በላይ የሆነ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል።

የጌትዌይ አስተዳዳሪ የኔትወርክ ትራፊክን የማስተላለፍ፣ የመንገድ ምርጫን የማስተዳደር፣ የአገልግሎት ቀጣይነትን የመወሰንና የኔትወርክ መረጃዎችን የማየት ቴክኒካዊ አቅም ሊኖረው ይችላል። ይህ ግን ሁሉንም የዜጎች መረጃ ማንበብ ወይም ማግኘት ይችላል ማለት አይደለም፤ የሚኖረው ትክክለኛ የመዳረሻ ወሰን በኔትወርክ አወቃቀር፣ በምስጠራ፣ በፈቃድና በቁጥጥር ሥርዓት ይወሰናል።

ነገር ግን የጌትዌይ ቁጥጥር በአንድ አካል እጅ ከተከማቸ የሚፈጠረው የተጠራቀመ አደጋ ከባድ ነው። በተለይ የብሔራዊ ደህንነት፣ የባንክ ሥርዓት፣ የመንግሥት ግንኙነትና የሕዝብ መረጃ በዚያው መሠረተ ልማት ላይ ከተመሠረተ የቁጥጥር አለመኖር በሀገር ደረጃ የሚታይ ተጋላጭነት ይፈጥራል።

2. ዌብስፕሪክስ፡ ከኢንተርኔት አቅራቢነት ወደ ወሳኝ ዲጂታል መሠረተ ልማት

ዌብስፕሪክስ በኢትዮጵያ የግል የቴክኖሎጂ አገልግሎት ዘርፍ የተሳተፈ ድርጅት ሲሆን፣ በኢንተርኔት አገልግሎት፣ በፋይበር ኔትወርክ፣ በክላውድ ኮምፒውቲንግና በዳታ ማዕከል አገልግሎት ዘርፎች እየሰፋ መጥቷል።

የ“ሸጋ” የጥር 22 ቀን 2026 ዘገባ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ሰፊ የክላውድ መሠረተ ልማት ማስጀመሩን ገልጿል። አገልግሎቱ VMware እና OpenStack የተባሉ የቴክኖሎጂ ሥርዓቶችን የሚጠቀም ሲሆን፣ በአይሲቲ ፓርክ ከWingu Africa ጋር በColocation ሥርዓት እንደሚሰራ ዘገባው ያመለክታል።

ይህ ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እድገት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ የአካባቢያዊ ክላውድ አገልግሎት የዳታ ማከማቻን ወደ ሀገር ውስጥ ለማምጣት፣ የመረጃ ፍጥነትን ለማሻሻልና የውጭ ቴክኖሎጂ ጥገኝነትን ለመቀነስ ያግዛል።

ሆኖም ይህ የቴክኖሎጂ እድገት ከብሔራዊ ደህንነት ቁጥጥር ጋር መመጣጠን አለበት። የክላውድ መሠረተ ልማት የሚያስተዳድር ድርጅት የተለያዩ ተቋማትን የማከማቻ፣ የማቀናበሪያ፣ የባክአፕ (Backup) እና የአደጋ ማገገሚያ (Disaster Recovery) ሥርዓቶችን ሊያስተናግድ ይችላል። ይህ ደግሞ የቴክኖሎጂ አቅራቢውን በተቋማት የሥራ ቀጣይነት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ከፍ ያደርገዋል። ስለዚህም ከቁጥጥር ባለፈ ተቋሙን ማን ይመራዋል፣ የሚመሩት አካላት ማንነትና ሀገራዊ እይታ በጥልቀት እንዲመረመር ግድ ያደርጋል።

በዚህ ጉዳይ የሚጠየቀው ወሳኝ ጥያቄ አንድ የግል ድርጅት የሀገሪቱን የተለያዩ ወሳኝ ተቋማት የቴክኖሎጂ አገልግሎት ሲያቀርብ የሚፈጠረው የተጠራቀመ ስጋት ምንድን ነው የሚለው ነው።

በተለይ የግል ባንኮች፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንና ፋና ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የቴክኖሎጂ አገልግሎት ከዌብስፕሪክስ ጋር የተያያዘ መሆኑ በውልና በተቋማቱ ማረጋገጫ ከተረጋገጠ፣ ጉዳዩ ከተራ የንግድ ውል በላይ የሆነ የብሔራዊ ደህንነት ጥናት ይጠይቃል፤ ምክንያቱም እነዚህ ተቋማት የሚያስተዳድሯቸው መረጃዎች እጅግ ስሱ ናቸው፦

  • ባንኮች፡ የደንበኞች የገንዘብ ሂሳብ፣ የግብይት ታሪክ፣ የብድር መረጃና የክፍያ ሥርዓቶች።
  • የጤና ሚኒስቴር፡ የዜጎች የጤና ታሪክ፣ የሕክምና መረጃ፣ የሕዝብ ጤና ስታቲስቲክስና ሌሎች ስሱ መረጃዎች።
  • የትምህርት ሚኒስቴር፡ የተማሪዎች መረጃ፣ የፈተና ውጤት፣ የትምህርት ተቋማት ዳታና የሰው ኃይል መረጃ።
  • የመንግሥት ሚዲያ፡ የዜና ምርት ሥርዓት፣ የስርጭት መረብ፣ የሚዲያ አርካይቭና የመገናኛ መሠረተ ልማት መረጃዎች አስተማማኝ እጅ መኖር ስላለባቸው።

በመነሻዬ እንዳልኩት “እገሌ ይባረር” የሚለው ጉዳይ የህግ ጥያቄውን ባላጠናውም ከነዚህ ዝርዝር ጉዳዮች አንጻር ብሄራዊ ጉዳይ ተደርገው መታየት አለባቸው።

የባለቤትነት ግልጽነት፡ የብሔራዊ ደህንነት መነሻ ጥያቄ

በወሳኝ የቴሌኮምና የዳታ መሠረተ ልማት ዘርፍ የሚሳተፍ ድርጅት ማን እንደያዘው፣ የአክሲዮን ባለቤቶቹ እነማን እንደሆኑ፣ የመጨረሻ ተጠቃሚ ባለቤቶቹ እነማን እንደሆኑና የካፒታሉ ምንጭ ምን እንደሆነ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል። ቀደም ሲል በተጠና ማንነት ብቻ ሳይሆን ክትትሉ ተቋሙ በሥራ ላይ እስካለ ድረስ መቀጠል አለበት። በዚህ መነሻ እያንዳንዱ ባለአክሲዮን በሀገሪቱ የመረጃ መነጽር ሥር ቢሆን አያስገርምም፤ ትክክልም ነው።

ይህ የግል ኩባንያን የመጠራጠር ጉዳይ አይደለም፤ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሠረተ ልማት ላይ የሚደረግ መደበኛ የስጋት ግምገማ እንጂ! እንዲህ ያለውን የዓለም ታላላቅ ሀገሮች ሳይቀር በትኩረት የሚያዩትን ጉዳይ በፖለቲካ አጣፍቶ መንግሥትን “ተኛና ታረድ” ማለት ከጅልነት የዘለለ ትርጉም አያሰጥም።

በዚህ ረገድ ስለ ዌብስፕሪክስ አንዳንድ የአክሲዮን ባለቤቶች ከፋኖ ታጣቂዎች የፋይናንስ ድጋፍ ጋር የተያያዘ ተግባር እንዳላቸው፣ ከሀገር ወጥተው እንደሚገኙና በሀገር ውስጥ ባሉ ወገኖቻቸው በኩል የባለቤትነት ለውጥ ለማምጣት የሕግ ሂደት እንደጀመሩ የሚነሱ ክሶች መኖራቸውን ሰምተናል። ነገሩ በህግ የተያዘ በመሆኑ ብዙ ማለት ባይቻልም፣ እነዚህ ክሶች በፍርድ ቤት ሰነዶች፣ በባንክ ማስረጃዎች፣ በተገቢ የምርመራ ሪፖርቶችና በኩባንያው የአክሲዮን መዝገብ መረጋገጥ አለባቸው። በተለይ የተደራጁ ታጣቂ ኃይሎችን የሚደግፍ የፋይናንስ ምንጭ በሀገሪቱ ወሳኝ ዲጂታል መሠረተ ልማት ላይ የባለቤትነት ወይም የቁጥጥር ተፅዕኖ ለማግኘት እየሞከረ መሆኑ በማስረጃ ከተረጋገጠ፣ ይህ ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ነው። በተለይም አሁን ላይ ነገሩ ከኤርትራ፣ ሱዳን፣ ግብጽና ወዘተ ጋር የተቆራኘ መሆኑ ይፋ በሆነበት ወቅት!

በዚህ ሁኔታ የሚነሳው ጥያቄ አንድ ወገን በአክሲዮን ድርሻ ብቻ ኩባንያውን የሚቆጣጠር አቅም ማግኘቱ አይደለም፤ የድርጅቱ የውሳኔ ሰጪነት፣ የኔትወርክ አስተዳደር፣ የዳታ መዳረሻና የአገልግሎት ቀጣይነት በማን እጅ ይሆናል? ከዛስ ምን ይከተላል? የሚለው ነው።

የባለቤትነት ክርክር ወደ ብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ሲያድግ

የአንድ የግል ኩባንያ ባለቤቶች በመካከላቸው የንግድ ወይም የአክሲዮን ክርክር ሊኖራቸው ይችላል። ይህ በመደበኛ ሁኔታ በፍርድ ቤት መፍትሔ የሚያገኝ የንግድ ሕግ ጉዳይ ነው። ነገር ግን የሚከራከሩት አክሲዮኖች የሀገሪቱን የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ማዕከልና የወሳኝ ተቋማት የቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚያስተዳድር ድርጅት ባለቤትነት ላይ ከሆነ፣ የክርክሩ ተፅዕኖ ከንግድ ሕግ ወሰን በላይ ይሄዳል።

በተለይ የአክሲዮን ባለቤትነት ለውጥ በተደራጁ ታጣቂ ኃይሎች የገንዘብ ምንጭ ጋር የተያያዙ ወገኖች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል የሚል ተጨባጭ ማስረጃ ካለ፣ የባለቤትነት ለውጡ ከመፈጸሙ በፊት የብሔራዊ ደህንነት ግምገማ ማድረግ ተገቢ ነው። እዚህ ላይ የፍርድ ቤት ነፃነት መጠበቅ አለበት የሚል መከራከሪያ ሊነሳ ይችላል። እኔም በግል ማንኛውም የባለቤትነት ጥያቄ በሕግ መሠረት መታየት አለበት የሚለውን አቋም እደግፋለሁ፤ ይሁንና የንግድ ክርክር የብሔራዊ ደህንነት ጥቅምን እንዳይጎዳ ተገቢው ተቆጣጣሪ ተቋም የባለቤትነት ምንጭንና የመጨረሻ ተጠቃሚ ባለቤትነትን መመርመር እንዳለበት ለአፍታም ሳላንገራግር የምመክርበት ጉዳይ ነው። አግባብ ያለው መርህም ይመስለኛል።

የሳይበር ጥቃት፡ አንድ ድርጅት ሲጎዳ ብዙ ተቋማት የሚጎዱበት ሁኔታ

በዘመናዊው የሳይበር ጦርነት አንድ ሀገርን ለማዳከም ወታደራዊ ጥቃት ብቻ አያስፈልግም፤ የሀገሪቱን የገንዘብ ሥርዓት፣ የመገናኛ መሠረተ ልማት፣ የጤና ሥርዓትና የመንግሥት የዳታ ማዕከላት ማወክ ብቻ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ከባድ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል።

የአንድ የግል ኩባንያ ክላውድ ሥርዓት የበርካታ ወሳኝ ተቋማትን ዳታ እያስተናገደ ከሆነ፣ በዚያ ሥርዓት ላይ የሚደርስ የሳይበር ጥቃት ከአንድ ድርጅት በላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

የድርጅቱ አስተዳደር በተገቢው ሁኔታ ካልተጠበቀ፣ የኔትወርክ መዳረሻ መብቶች በጥንቃቄ ካልተደራጁና የዳታ መለያየት ሥርዓት ከሌለ የአንድ ደንበኛ የደህንነት ችግር ወደ ሌሎች ደንበኞች ሊስፋፋ ይችላል።

ይህ በተለይ ለኢትዮጵያ አሳሳቢ ነው፤ ምክንያቱም የባንክ፣ የጤና፣ የትምህርትና የመንግሥት ዳታ ሥርዓቶች የሀገሪቱ የማይተኩ ስትራቴጂካዊ ሀብቶች እየሆኑና በርካታ አገልግሎቶች ወደዚሁ ማዕቀፍ እየተዛወሩ በመሆኑ ነው።

የሕግ መሠረቱ አለ፤ የቁጥጥር ትግበራው የት ደረሰ?

ኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2024ን አውጥታለች። አዋጁ የግል መረጃ በሕጋዊ፣ በደህንነቱ በተጠበቀና የመረጃ ሉዓላዊነትን በሚያስጠብቅ መንገድ መቀናበር እንዳለበት ያስቀምጣል። አዋጁ የአካባቢያዊ የግል መረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ ሰርቨር ወይም ዳታ ማዕከል እንዲከማች ይደነግጋል። እንዲሁም የዳታ ተቆጣጣሪና የዳታ አቀናባሪ ተቋማት የመረጃ ጥበቃ ግዴታዎችን እንዲወጡ ያስገድዳል። ከዚህ በተጨማሪ የወሳኝ መሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2026 የወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ የሕግ መሠረት አስቀምጧል።

ስለዚህ ጥያቄው “ሕግ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ብቻ አይደለም። እነዚህ ሕጎች በወሳኝ የዲጂታል መሠረተ ልማት ላይ እንዴት እየተተገበሩ ናቸው? የባለቤትነት ለውጥ ምን ዓይነት የደህንነት ማጣሪያ ያልፋል? የመንግሥት ተቋማት የዳታ ደህንነት ኦዲት በማን እየተደረገ ነው? የሚሉት ናቸው።

የመጨረሻ ጥያቄ፡ የሀገር ዲጂታል ቁልፍ በማን እጅ መሆን አለበት?

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚዋን ማሳደግ፣ የግል ኢንቨስትመንትን መሳብና የቴክኖሎጂ ውድድርን ማበረታታት አለባት። ነገር ግን የዲጂታል እድገት የብሔራዊ ደህንነትን በሚያዳክም መንገድ መካሄድ የለበትም።

የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ማዕከል፣ የባንክ መረጃና የመንግሥት የዲጂታል ሥርዓቶች የሀገር ስትራቴጂካዊ ሀብቶች ናቸው። እነዚህን የሚያስተዳድሩ ድርጅቶች የባለቤትነት ግልጽነት፣ ጠንካራ የደህንነት ቁጥጥርና በሕግ የተወሰነ ተጠያቂነት ሊኖራቸው ይገባል።

ስለዚህ የዌብስፕሪክስ ጉዳይ በአንድ የግል ድርጅት የንግድ ስኬት ወይም ውዝግብ ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም። የሀገሪቱ የዲጂታል መሠረተ ልማት ማን እንደሚቆጣጠረው፣ የዜጎች መረጃ በምን ደረጃ እንደሚጠበቅና በብሔራዊ ደህንነት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር የባለቤትነት ለውጥ ሲኖር መንግሥት ምን ዓይነት የጥበቃ ሥርዓት እንዳለው የሚያነሳ ብሔራዊ ጥያቄ ነው።

የሀገር ዲጂታል ቁልፍ በማን እጅ ነው? የሀገሪቱን የመረጃ ሉዓላዊነት የሚጠብቀውስ ማን ነው? እነዚህ ጥያቄዎች ከአሁኑ በላይ መመለስ የሚጠይቁ ናቸው። ይህን መሰል ቁልፍ ጥያቄዎች እንዲሁ በችሎት መዶሻ የሚደመደሙ አይደሉምና ፍርድ ቤቶችም ሆኑ ዳኝነት ላይ የተቀመጡ አካላት ነገሩን በኃላፊነት ሊያዩት ይገባል። ጨዋታው “እገሌ ሄደ፣ እገሌ መጣ” የሚለው የሸማኔው መወርወሪያ ዓይነት ጨዋታ አይደለምና ጠንቀቅ!

ማጠቃለያ፤ መንግሥት ምን ማድረግ አለበት?

ኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ እንዲሳተፍ መፍቀዷ በራሱ ችግር አይደለም። ውድድር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ኢንቨስትመንትና የአገልግሎት ጥራት ለማሳደግ የግል ዘርፍ ተሳትፎ ያስፈልጋል። ነገር ግን የሀገሪቱ ወሳኝ ዲጂታል መሠረተ ልማት በባለቤትነት ወይም በአስተዳደር ሥልጣን ለማንኛውም አካል ሲሰጥ የብሔራዊ ደህንነት ግምገማ መደረግ አለበት። ሲሰጥ ብቻ ሳይሆን ከተሰጠም በኋላ ክትትል ግድ ነው። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥትና ተቆጣጣሪ ተቋማት ብሄራዊ ስጋትን ዜሮ ከማድረግ አኳያ ይበጃል የሚሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይገባቸዋል።

ኢንሳ (INSA)፣ የብሔራዊ ደህንነት ተቋማት እና ፈቅስድ ስትሰጥ ያስቀመጥከውን አስገዳጅ ህግ የምታውቀው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒከሽን ባለስልጣን  ለምን ዝም አላችሁ?! 

ኤፍሬም ጓንጉል

Filed Under: Opinions, Politics, Slider Tagged With: Abebaw Desta, abraham minwuyelet, Dawit Berhanu, Mekdes aklilu, Scattered Spider, Silence, WebSprix, WebSprix Sovereign Cloud

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule