በሰሜን ኢትዮጵያ ከትህነግ (የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር) ጋር በተደረገው ጦርነት በተወሰነ መልኩ በጦር መሣሪያ በተለይ ግን በሰው ኃይል አብላጫውን ይዞ የነበረው ትህነግ ቢሆንም ጦርነቱ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት እንደገና መጠናከር ብዙ ትምህርት ጥሎ ያለፈ ነበር። ከጦርነቱ በኋላ መከላከያ በሰው ኃይልም ሆነ በመሣሪያ በፍጥነት የሄደበት መንገድ ተጠቃሽ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ስንገዛቸው የነበሩ የጦር መሣሪዎችን ማምረት ጀምረናል ማለታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነውም በየጊዜው በመከላከያ ሚኒስቴር ሥር በተለያዩ ክፍሎች ከተተኳሽ ጀምሮ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችና ተሸከርካሪዎች በአገር ውስጥ በልዩ ሁኔታ እየተመረቱ እንደሆነ የሚወጡ መረጃዎች በመጠቆማቸው ነው። ይህ በአየር ኃይል በኩል እየተደረገ … [Read more...] about አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?!
Politics
የብልፅግና ፓርቲ ሹመኛ ካድሬዎች
የብልፅግና ፓርቲ ሰሞኑን ባደረገው ሁለተኛ ስብሰባው በሥልጣን ላይ ያሉትን ዐቢይ አሕመድ (ፕሬዚዳንት)፣ ተመስገን ጥሩነህ (ምክትል)፣ አደም ፋራህ (ምክትል) የፓርቲውን አመራሮች መልሶ መርጧቸዋል። የብሔርና የክልል አሠራርን በማስቀጠል 45 ካድሬዎች ያሉትና ሦስቱ አመራሮችን ያካተተ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትም ተመርጧል። ከ45ቱ ውስጥ ወንዶች 35 (78%) ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ 10 (22%) ናቸው። በብሔርና ክልል ደረጃ፤ ከኦሮሚያ ክልል 10፤ ከአማራ ክልል: 8፤ ከሶማሌ ክልል: 4፤ ከትግራይ ክልል: 2፤ ከሀረሪ ክልል: 2፤ ከአፋር ክልል: 3፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል: 2፤ ከሲዳማ ክልል: 3፤ ከጋምቤላ ክልል: 2፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል: 2፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል: 3፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል: 4 ናቸው። ቀድሞ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሚባለው ስሙ ተቀይሮ … [Read more...] about የብልፅግና ፓርቲ ሹመኛ ካድሬዎች
ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው!
የመሠረት ሚዲያ ባለቤት አቶ ኤሊያስ መሠረትን በስም ጠቅሶ የመንግሥት ተከፋይ እንደሆነ የፋኖ አንድ ክንፍ መሪ እስክንድር ነጋ በይፋ ተናገረ። እስክንድር “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ” ሲል አመልክቷል። እስክንድር ይህን ያለው ከEMS ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲሆን፣ መነሻው አቶ ኤሊያስ መሠረት በአባቱ ስም እንደሰየመው በሚገልጸው የግሉ ሚዲያ ላይ እስክንድርን ጠቅሶ “ከመንግሥት ጋር ለመደራደር የተዘጋጀው የፋኖ ክንፍ ንግግሩ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ” በማለት ሪፖርት ማድረጉን ተከትሎ ነው። አቶ ኤሊያስ “መሠረት ሚዲያ ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ በሠሩ እና አሁንም እየሠሩ ባሉ ጋዜጠኞች ሚዛናዊ፣ አዳዲስ እና ፈጣን መረጃዎችን ለአንባቢዎች ያደርሳል” በሚል መሪ እሳቤ እንደሚሠራ በማኅበራዊ ገጹ ላይ አስፍረዋል። እስክንድር ነጋ በቃለ ምልልሱ “ኤሊያስ … [Read more...] about ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው!
ደም ጠጥቶ “አልጸጸትም” – የጃዋር አዲስ መጽሐፍ
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ “የአማራ ብሔርተኝነት ማነሳሳታችን ትልቁ ስኬታችን ነው”፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የምርጫውን ቀመር (ካልኩሌሽን ሠርቼዋለሁ)፣ ቁርአን ይዤ ዐቢይን ጅማ ላይ እንዳይመረጥ አደርገዋለሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት ነው ያለው - የዐቢይ እና የቄሮ መንግሥት፣ እኔ ከታሰርሁ ኦሮሚያ ድብልቅልቁ ነው የሚወጣው፣ የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ፣ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ እጅግ በርካቶች በግፍ … [Read more...] about ደም ጠጥቶ “አልጸጸትም” – የጃዋር አዲስ መጽሐፍ
የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን
"ዝምታ ነው መልሴ" ሲሉ ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ድምጻቸውን በቲውተር በኩል በዘፈን ምርጫ አጅበው ብቅ ያሉት ለስንብት ሁለት ቀናት ሲቀራቸው ነው። "የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው" ሲሉ የተቀኙት ፕሬዚዳንቷ "ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" በሚል ሐረግ መልዕክታቸውን አስረውታል። ይህኔ ነው "የኔታ መስፍን ወልደማርያምን ነብሳቸውን ይማረው" ሲሉ ፋይል ያገላበጡ ፕሬዚዳንቷ በኤክስ ይፋዊ ገጻቸው ላይ ላሰፈሩት ቅኔ ምላሽ የሰጡት። አንዳንዶች "ክብርት ሆይ ሕዝብም መንግሥትም መሆን አይቻልም" ሲሉ ቀልደውባቸዋል። ግልጹ፣ ያመኑበትን ለመናገር ወደኋላ የማይሉት፣ የአደባባዩ ምሑር ፕሮፌሰር መስፍን "ለሦስት መንግሥት ያገለገለች" ሲሉ በሎሌነት የመሰሏቸው የሳህለወርቅ ዘውዴን ሹመት በፍጹም እንደማይቀበሉት ተናግረው … [Read more...] about የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን
የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
ከበረሃ ውንብድና አገረ መንግሥትን ወደመምራት ሳያስበው የተቀበለው ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት በነጻ አውጪ ስም አንዲት ሉዓላዊት አገር ጠርንፎ በአናሳዎች በግፍ ሲገዛ የነበረው የወንበዴዎች ቡድን ጎራ ለይቶ በአደባባይ መካሰስ ከጀመረና ውዝግቡም እየተካረረ መጥቶ ትግራይን እንደ አፍጋኒስታን ወይም ኢራቅ በጦር አበጋዞች ከፋፍሎ ወደለየለት ደረጃ እየወሰዳት መሆኑ በቅርቡ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የቡድኑ መሪ የሆነው ደብረጽዮን እነ ጌታቸው የሚከሱኝ በፊትም ጦርነት ውስጥ ያስገባንና ሚሊዮኖችን ያስጨፈጨፈው ትህነግ ነው፤ አሁንም መልሶ ጦርነት ውስጥ ሊከተን ነው፤ ጦርነት ናፋቂ ነው እያሉ ነው፤ ነገር ግን ተጨፈጨፈ የተባለው ሕዝብ ማስረጃ የታለ? ባለተጨበጠና ባልተረጋገጠ፤ ማስረጃ በሌለው እኔን መክሰስ ብቻ ስለፈለጉ ባልሞተ ሕዝብ ይከስሱኛል በማለት … [Read more...] about የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
አሜሪካ ኢሳያስንና ሻዕቢያን የማስወገድ ዓላማዋን ይፋ አድርጋለች
የሻዕቢያና የኢሳያስ አፈወርቂ ማብቂያቸው እየተቃረበ ይመስላል። ይህንኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶች እዚያም እዚህም እየተሰሙ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር የመመለሷን ጉዳይ አጥብቀው በሚፈልጉ ጡነቸኞቹ አገራት ዘንድ አቋም የተያዘ ይመስላል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ፍጹም የማይፍለገውን ትህነግን እንደ ሕጻን አዝላ የኖረችው አሜሪካ አሁን ላይ ሁለቱም እንደ አመጣጣቸው እንዲሰናበቱ አቋም ስለመያዟ ከምልክት በላይ መረጃዎች እየወጡ ነው። ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ኢሳያስን፣ መለስን፣ ሙሴቪኒንና ካጋሜን አንድ ላይ "የአዲሱ ትውልድ መሪዎች" ብለው ለምስራቅ አፍሪቃ ሲያጩ በድጋፍ ስልጣን ላይ የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ካርዳቸው አልቋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ የገነባችው ኃይልና ዘመናዊ የውትድርና ቴክኖሎጂ ሻዕቢያን ለማስወገድ ከትህነግ በላይ አስተማማኝ በመሆኑ አሜሪካ ትህነግን መሽከም … [Read more...] about አሜሪካ ኢሳያስንና ሻዕቢያን የማስወገድ ዓላማዋን ይፋ አድርጋለች
ኢትዮጵያ የሚያልቧት እንደዚህ ነው፤ “ገንዘብ ባለበት ጩኸት አለ”
የአገራችን “ሃብታሞች” ወግ ከፍቶ ውስጡን ላየው ያስደነግጣል። “ገንዘብ ባለበት ሁሉ ጩኸት አለ” የሚለው አባባል በተለይ በኢትዮጵያ እውነት እንደሆነ ማረጋገጫም ነው። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ሲጋልቡ የነበሩ አካላት፣ አሁን ላይ “ይህ ለምን ቀረብን?” ወይም “ገና ለገና ሊቀርብን ነው” በሚል ሥጋት አንድ ላይ አገር እየናጡ ነው። ከዚህ ቀደም “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው” በሚል ርዕስ ስለ አዲሱ ማክሮ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ስንዘግብ ውሳኔው “በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ሳይሆን አዲስ መጽሐፍ ነው፤ ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው፤ ከዚህ አኳያ ፖሊሲው እንከን የማይወጣለት ነው” በሚል አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጠቅሰን እንደነበር ይታወሳል። ይህን ዘገባ ተከትሎ የአዲስ አበባ … [Read more...] about ኢትዮጵያ የሚያልቧት እንደዚህ ነው፤ “ገንዘብ ባለበት ጩኸት አለ”
የትግራይ አበጋዞች ፍልሚያ
የሕወሓትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀመሩትን ንትርካቸውን በመቀጠል፣ አሁን ደግሞ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ መወዛገብ ጀመሩ። የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ፕሪቶሪያ የተላከው ልዑክ ያልተወያዩበትን መስማማቱን ሲገልጹ፣ ልዑኩን የመሩት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ልዑኩ ወደ ፕሪቶሪያ የሄደው ስለመንግሥትነት ጉዳዮች ለመወያየት ሳይሆን ተኩስ ለማስቆም መሆኑንና በዚያው መሠረት ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን አስታውቀዋል። ሕወሓት ስምምነቱን እንዲፈርሙ የመረጣቸው ልዑካን ስህተት መፈጸማቸው የተናገሩት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ በዚህም ምክንያት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት መጀመር የነበረበት ፖለቲካዊ ውይይት እስካሁን አለመጀመሩንና የክልሉም ሉዓላዊነት አለመረጋገጡን አስታውቀዋል። አቶ … [Read more...] about የትግራይ አበጋዞች ፍልሚያ
ገዱ: “የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው እንክሰስው”፤ “ባለውለታ ነው እንጠቀምበት”
ሰሞኑን ለጥገኝነት ማመልከቻቸው ደጋፊ ነው የተባለለትን ዘለግ ያለ ጽሑፍ ያቀረቡት ገዱ አንዳርጋቸው በትግራይ ማኅበረሰብ ዘንድ የተከፋፈለ ዕይታ የፈጠሩ መሆናቸው ተነገረ። ““የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው፤ እጃችን ገብቷል እንክሰሰው” ባዮች በርተተው የታዩ ቢሆንም “ባለውለታችን ነውና አሁንም እንጠቀምበት” የሚሉ በሌላ ወገን ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። በዘመነ ትህነግ የሥርዓቱ ተላላኪና ጉዳይ ፈጻሚ የነበሩት ገዱ አንዳርጋቸው የዚያን ጊዜው አለቆቻቸውን ለማስደሰት ያልታዘዙትን፣ ያልተጠየቁትን እላፊ በመሄድ በመፈጸም አለቆቻቸውን እጅ በመንሳት ይታወቃሉ። ለዚህ ታማኝነታቸው በአማራ ሕዝብ ላይ የመጨረሻውን ሥልጣን እንዲያገኙና ሎሌነታቸውን የበለጠ በደስታ እንዲፈጽሙ አድርጓቸዋል የሚሉ ጥቂት አይደሉም። እንደማሳያም የወልቃይትን ጉዳይ ይጠቅሳሉ። ገዱ አንዳርጋቸው ከዚህ በታች ያለው … [Read more...] about ገዱ: “የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው እንክሰስው”፤ “ባለውለታ ነው እንጠቀምበት”