• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል”

May 29, 2026 07:07 pm by Editor Leave a Comment

ሰኞ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ኢህአፓ እንደሚሰነጠቅ ተነገረ። አሁን ላይ ፓርቲው በተለይ አመራሩ ኹለት ሊባል በሚችል ጎራ ተከፋፍሎ ውስጥ ለውስጥ እየተናቆረ እንደሆነ ተገልጿል።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ለምርጫ በጥምረት ስም የገባው ኢህአፓ እንደሚሰነጠቅ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። በተለይ በአመራር ደረጃ ያለው መለያየትና መከፋፈል ፓርቲውን ለመሰንጠቅ አደጋ እንዳበቃው ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል።

የፓርቲው መሪ አቶ አብርሃም ሃይማኖትም የክፍፍሉን ኹኔታ በሚዲያ ቀርበው የተናገሩ ሲሆን በተለይ በአመራሩ መካከል ከምርጫ ጋር በተያያዘ የተከሰተው አለመግባባት የከረረና እርሳቸውንም ከኃላፊነት እንዲወጡ እያስገደዳቸው መኾኑን ተናግረዋል።

አንከር ከተባለ ዩትዩብ ጋር የተነጋገሩት አቶ አብርሃም በርካታ የፓርቲውን ምሥጢሮች ይፋ አድርገዋል። ጠያቂ ሆኖ የቀረበው መሳይ መኮንን እጅግ የሚያሸማቅቅና ክብር የሚነካ ቃላትን ለፓርቲውም ሆነ ለመሪው እያነሳ በመወረፉ አቶ አብርሃም መረጃዎችን ለማውጣት የተገደዱ ይመስላል።

የኢህአፓ አካሄድ በተለይ በድጋፍ ሰጪ ስም ከተዋቀረውና በውጪ ከሚገኘው ቡድን በቀጥታ የሚቀዳ ነው። መሪውን የተቆጣጠሩትና የፓርቲውን አቅጣጫ የሚዘውሩት ከፖለቲካ ጡረታ ሞት ይለየኝ ያሉት የቀድሞዎቹ ኢህአፓዎች ናቸው።

ከወራት በፊት፤ ምርጫውን በተመለከተ ለኢህአፓ የተሰጠው የፕሮጀክት አካሄድ መመሪያ፤ እንወዳደራለን ብላችኹ ግቡ፤ ለምርጫው ቅድመ ኁኔታዎችን አቅርቡ፤ አስቻይ ኹኔታዎች እንደሌሉ አስቀድማችኹ በተደጋጋሚ ተናገሩ፤ የተወሰነ እንቅስቃሴ አድርጉ፤ ምርጫው ሲቃረብ ለቅቃችኹ ውጡ፤ ይህንንም በማድረግ በመንግሥት ላይ የፖለቲካ ጫና ብቻ ሳይሆን ምርጫውን ሕገወጥ ወይም ዲሌጂቲማይዝ (delegitimize) በማድረግ ሥራ ትሠራላችኹ የሚል ነበር።

የሻዕቢያ ወኪልና የኤርትራን ጉዳይ አስፈጻሚ እንደሆን በግልጽ በተለያዩ ስብሰባዎች የሚናገረው ነዓምን ዘለቀ፤ ከወራት በፊት በተካሄደ የዙምና WhatsApp ስብሰባ የተለያዩ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶችን ሰብስቦ ምርጫውን ሕገወጥ ወይም ዲሌጂትማይዝ ስለማድረግ በግልጽ ሲናገር ተደምጧል። የሻዕቢያም ዓላማም ይኸው እንደሆነ ነዓምን በተደጋጋሚ ሲናገር የተሰማ ጉዳይ ነው።

ኢህአፓ ግን በጀት ተመድቦ የወጣለትን ዕቅድ እና የተሰጠውን ተግባር ሳይፈጽም በመቅረት እንዲያውም በምርጫው እወዳደራለኹ በማለቱ ቁጣ አስነስቶበታል።

የምርጫ ቦርድ አሠራርና ሕግ፤ ከምርጫ የሚወጣ ፓርቲ ከምርጫው አንድ ወር በፊት ውሳኔውን ማሳወቅ አለበት ይላል። ስለዚህ ሚያዚያ ላይ ኢህአፓዎች በውስጥም በውጪም ያሉት ተሰበሰቡና ምን እናድርገ በሚለው መከሩ፤ አቶ አብርሃም እንደተናገሩት። ውይይቱ ኢህአፓን ለኹለት ከፈለው።

አንደኛው፤ ከወዲሁ እጅ መስጠት የለብንም፤ በምርጫው መሳተፍና ከዚያ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን መምራት የሚሉ ሲኾን፤ በሌላው ደግሞ በምርጫው መቀጠል የለብንም፤ አስቻይ ኹኔታዎች የሉም፤ በቅድመ ኹኔታነት ያስቀመጥናቸው አልተሟሉም፤ ስለዚህ ምርጫውን አንወዳደርም ብለን መውጣት አለብን የሚሉ በሌላ ወገን ሆኑ።

አቶ አብርሃም እንደተናገሩት፤ ሰባት የሚያኽሉ የማዕከላዊና የሥራ አስፈጻሚ አባላት ሚስጥረሥላሴን ጨምሮ በምርጫው መቀጠል የለብንም የሚሉ ነበሩ። ሦስት ደምፀ ተዓቅቦ፤ በልዩ ሁኔታ ለምሳሌ ምርጫው ሁለት ቀን ሲቀረው እንውጣ የሚሉ ደግሞ ሁለት ነበሩ ይላሉ። በአጠቃላይ አስራ ኹለት ሰዎች ተመሳሳይ የሚባል ዓቋም ያዙ። የተቀሩት ደግሞ መቀጠል አለብን፤ ለሚቀጥለው መራራ ትግል መዘጋጀት አለብን የሚሉ በሌላ ቡድን ሆኑ። አብላጫው በምርጫው እንቀጥል የሚል ኾነና ተወሰነ።

የኢህአፓው መሪ እንደሚሉት ሚያዚያ ፳፬ ቀን የታተመው የፓርቲው በምርጫ መቀጠል ውሳኔ እነ ክርስቲያን ታደለንም ጭምር አማክረን ያደረግነው ነበር ይላሉ። እነርሱም ያሉን ድርጅታችሁን ጠብቁ ለአብላጫው ውሳኔ ተገዙ ነው ያሉን በማለት አቶ አብርሃም ተናግረዋል። ኾኖም ግን በአብን ስም ፓርላማ የገቡት ክርስቲያን ታደለ በምን አግባብ የኢህአፓ አማካሪ እንደኾኑ አቶ አብርሃም አልተናገሩም።

ስለዚህ አሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መምሕር (መጋቤ ብሉይ) እና የኢህአፓ መሪ የኾኑት አቶ አብርሃም፤ “ኢህአፓ እንደ ድርጅት ከምርጫው አንወጣም ብሎ ወስኗል፤ ትብብሩም በዚሁ ቀጥሏል፤ ከወጣንም እንደ ትብብር ነው እንጂ ከዚህ በኋላ በግል አንወጣም”።

ከዚህ በኋላ ንዴቱን መደበቅ የተሳነው መሳይ መኮንን ዕንግዳውን አቶም ይኹን መጋቤ ብሉ ማለቱን በመተው “አብርሃም”፣ “አንተ” እያለ በመጥራት ጸያፍ የሚባል ቃላትን በመጠቀም አቶ አብርሃምን ማዋረዱን እና ማስፈራራቱን ተያያዘው። የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ተከፍሏል፤ ግማሾቻችኹ የብልጽግና ተከፋዮች መሆናችኹን መረጃው አለኝ፤ እናንተ ለዓቅመ ፖለቲካ ያልበቃ አመራር ናችኹ፤ በግልጽ እንነጋገር ከተባለ ለራሳቸው ጥቅም የሚታገሉ፤ የፖለቲካ ጡጦ ያልጠቡ ናቸው በናንተ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ያሉት በማለት መሳይ ያለገደብ ተናገረ።

የሚናገሩት ትንሽ የተደናገራቸው አቶ አብርሃምም መስተካከል የሚገባው ነገር አለ፤ ከምርጫው በኋላ ሕዝባዊ ትግል ይቀጣጠላል፤ አዲስ አበባን እንኳን ብናሸንፍ ሌሎቹን አስተባብረን ድርድር እናደርጋለን ብለው ሳይጨርሱ መሳይ አቋረጣቸውና አስገራሚ ነው፤ እንደዚህ ብላችኹና ምርጫውን ከማሸነፍ ባለፈ አዲስ አበባን ጭምር እንቆጣጠራለን ብላችኹ ማሰባችኹ በውስጣችኹ ያለው የፖለቲካ አመራር ከእውነተኛ ዓለም የተጣላ፤ ምንም ዕውቀት ዓይነት የነባራዊው ኹኔታ ዕውቀት የሌለው ነው በማለት ጥያቄ የማይባል አስተያየት ተናገረ።

ሌላ ማስተካከያ ለመናገር የሞከሩት አቶ አብርሃም ሲቀጥሉ እኛ በምርጫው ለመሳተፍ የወሰነው አንዳንዶች መንግሥት እኛን በአሸባሪነት ለመመደብና ከግብጽ ጋር ትሠራላችኹ ብሎ ለመኮነን እየተዘጋጀ ስለኾነ ለምን የተዘጋጀልን ወጥመድ ውስጥ እንገባለን፤ ስለዚህ በምርጫው መሳተፍ ከዚህ ያድነናል ብለው የወሰኑም አሉ በማለት ሌላ ያልተጠየቁትን ድርጅታዊ ምሥጢር ይፋ አደረጉ ።

በአቶ አብርሃም ምላሽ ይበልጥ ስሜቱ የተነካው መሳይ በፊት የተናገረውን በመድገም ሚዲያ ላይ መኾኑን በመዘንጋት የቃላት ናዳውን ቀጠለ፤ “ከዚህ በፊት ቅደም ሁኔታ አስቀምጣችኹ አንዱም እንኳን ምንም ሳትሉ ወደ ምርጫ መግባታችኹ ወደፊት እንዴት ሕዝቡ ያምነናል ብላችኹ ነው ትግሉን እናቀጣጥላለን የምትሉት፤ ግማሽ ያህሉን የማዕከላዊ ፓርቲ አባልኮ ብልጽግና ተቆጣጥሮታል፤ ማስረጃው አለን፤ ይህንን ደግሞ በቅርቡ ይፋ እናደርገዋለን” በማለት ማስፈራሪውን ሰነዘረ።

እቶ አብርሃም ስሜታቸው የተነካ በሚመስል ኹኔታ የሰጡት ምላስ ያሉበት የፖለቲካ ውዝግብ እጅግ በጣም የሚያሰለችና የሚያደክም መሆኑን በመጥቀስ፤ የሀገር ጉዳይ ባይሆን ኖሮ ከፖለቲካ ብወጣ እመርጣለኹ፤ በሃሳብ መለያየት እንደ ወንጀል የሚቆጠርበትና ብዙ መከዳዳት፣ ሤራ፣ ወዘተ ያለበት ኹኔታ እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ ሃሳቤን አልተቀበልህም ብሎ መፈረጅ እና መጠላለፍ ነው ያለው በማለት የኢህአፓን ውስጣዊ መከፋፈል ይፋ አድርገዋል።

ለዚሕ ምላሻቸው ምንም ሐዘኔታ ያልተሰማው መሳይ ቅድም የረሳኹት ብሎ አዲስ አበባ ላይ ቅስቀሳ አደረግን ያላችኹት መስተካከል ያለበትና ሕዝቡን ያልመጠነ እንዲያውም የናቀ አባባል ነው፤ እናንተ ያደረጋችኹት ቅስቀሳ ሳይኾን በየቦታው ዘፈን (ዳስ ጣልን) እያሰማችኹ ባንዲራ ማውለብለብ ነው፤ ሕዝቡ ከናንተ የጠበቀው ይህንን አይደለም በማለት አቶ አብርሃም ቀጣይ ይካኼዳል ያሉት ቆራጥ ትግል ውሃ ቸልሶበታል።

አቶ አብርሃም ከመሳይ ጋር ያደረጉትን ወሬ ሲጨርሱ ግን መሳይ በአጽዕኖት ሲቃወመው የነበረውን ምርጫ እንዲያሸንፉ መልካም ዕድል እመኛለኹ በማለት ዕንግዳውን ሸኝቷል።

የኢህአፓ የውጪ ድጋፍ ኮሚቴ ውስጥ ያሉ ለጎልጉል የሰጡት አስተያየት ፓርቲው በከፍተኛ ኹኔታ የተከፋፈለ መኾኑን የሚገልጽ ነው። በውጪ ያለው የጠበቀውና ያቀደውን ሀገር ቤት ያለው አመራር ባለማስፈጸሙ ከፍተኛ ንዴትና ቁጭ አለ የሚሉት መረጃ አቀባይ በተለይ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ ገንዘብ እየተዋጣ የተላከው መና መቅረቱ በውጪ ያለውን እጅግ ያሳዘነ ተግባር ኾኗል ብልዋል።

ከምርጫው በኋላ የተወሰኑ የኢህአፓ ተወዳዳሪዎች በክልል ምክርቤትም ኾነ በፓርላማ ወንበር የሚያገኙ ሲኾን ከሚገኘው ጥቅማጥቅም አኳያ ወንበራቸውን ማስጠበቃቸው የማይቀር ይሆናል። የማይገቡት ደግሞ ከብልጽግና ጋር አዳማቂ ሆናችኹ መሥራት የለባችኹም በማለት ያሸነፉትን አባላት አትግቡ የሚሉ ሲኾን ይህም አባላቱንና አመራሩን ለኹለት የሚሰነጥቀው ይሆናል።

በዘመነ ትህነግ በውጪ የሚገኘው ኢህአፓ ለኹለት ተሰንጥቆ ኢህአፓ እና ዲ-ኢህአፓ የሚባል ተመሥርቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: eprp, EPRP-D

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule