የሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ፣ የቀድሞው የአብን ተመራጭና የአሁኑ የኢህአፓ/ትብብር እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ዶ/ር አበባው ደሳለው በሰጡት ቃለ መጠይቅ በምርጫው ማሸነፍ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ብስጭትና ንዴት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ተወዳድረው ከትብብሩ እና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሕዝብ የተመረጡትንም በብልጽግና ችሮታና ድጋፍ የተመረጡ፣ በምርጫ ሳይሆን በቅርጫ ያሸነፉ በማለት ወርፈዋል። ወደ ፓርላማ አለመግባት ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የተከበሩ አቶ አበባው ብሔር ተኮር ከሆነው አብን ወጥተው ወደ ኢህአፓ የገቡበትን ምክንያት አስረድተዋል። “ኢህፓን የመረጥኩበት ምክንያት ደግሞ እንደሚታወቀው ጠንካራ ታጋዮች የወጡበት ፓርቲ ነው። ለተራ ጥቅም ብለው ለተራ ኢኮኖሚ ጉዳይ ብለው ህሊናቸውን የማይሸጡ … [Read more...] about ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ
eprp
እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር
* ሚስጥረ፤ “ወደ ምርጫው የገባኹት አምኜበት አይደለም” የኢህአፓና የትብብሩ ዋና ጸሐፊ የሆነችው ሚስጥረሥላሴ ታምራት ከአዲስ ኢንሳይደር ጋር ባደረገችው ውይይት ወደ ምርጫው የገባችው አምናበት እንዳልሆነ ተናገረች። ትብብሩ የተከፋፈለ መሆኑን ያልካደችው ሚስጥረ የአውሮጳ ኅብረትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ምርጫውን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ “ለእኛ” ከነገሩን ጋር የተለያየ ነው በማለት ኅብረቱ የሐሰት መግለጫ እንዳወጣ እንደምታ የሚሰጥ አስተያየት ሰጥታለች። ከምርጫው በፊት ቅድመ ሁኔታ እንዳስቀመጡና እነዚያ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ወደ ምርጫ መግባታቸውን በተመለከተ ስትመልስ እንዲህ ብላለች፤ “ወደ ሰባት የሚሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሚደረግ ምርጫ አምባገንነትን ነው እንጂ የሚያዋልደው በፍጹም የዲሞክራሲ መገለጫ ሊሆን አይችልም በሚል … [Read more...] about እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር
የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ “ትብብር” የተሰኘው ቡድን ያወጣው መግለጫ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና የእናት ፓርቲ አመራሮች “ትብብር” የተባለውን ስብስብ ወክለው ኢኤምኤስ ለተባለው ዩትዩብ የተናገሩት በሀገር ውስጥና በዲያስፖራው ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ አስነሳ። ሚስጥረሥላሴ ከኢህአፓና ጌትነት ከእናት ፓርቲ ሆነው “ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ያልሆነ የጨረባ ምርጫ ነው” በማለት ውድቅ ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሕዝቡ ግን “ቀድሞውኑ ለገዢው ፓርቲ አጃቢና ድራማ አድማቂ ለመሆን የገባችሁ የፖለቲካ ድንኮችና ሆዳሞች ናችሁ” በማለት በብርቱ እያወገዛቸው ይገኛል። የፖለቲካ ተንታኞችና የውስጥ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ የኢህአፓ እና የ“ትብብር” ጥምረት መሪዎች ቀድሞ የነደፉት … [Read more...] about የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ
“ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል”
ሰኞ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ኢህአፓ እንደሚሰነጠቅ ተነገረ። አሁን ላይ ፓርቲው በተለይ አመራሩ ኹለት ሊባል በሚችል ጎራ ተከፋፍሎ ውስጥ ለውስጥ እየተናቆረ እንደሆነ ተገልጿል። ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ለምርጫ በጥምረት ስም የገባው ኢህአፓ እንደሚሰነጠቅ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ይጠቁማል። በተለይ በአመራር ደረጃ ያለው መለያየትና መከፋፈል ፓርቲውን ለመሰንጠቅ አደጋ እንዳበቃው ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል። የፓርቲው መሪ አቶ አብርሃም ሃይማኖትም የክፍፍሉን ኹኔታ በሚዲያ ቀርበው የተናገሩ ሲሆን በተለይ በአመራሩ መካከል ከምርጫ ጋር በተያያዘ የተከሰተው አለመግባባት የከረረና እርሳቸውንም ከኃላፊነት እንዲወጡ እያስገደዳቸው መኾኑን ተናግረዋል። አንከር ከተባለ ዩትዩብ ጋር የተነጋገሩት አቶ አብርሃም በርካታ የፓርቲውን ምሥጢሮች ይፋ … [Read more...] about “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል”
“አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
በ1980ዎቹ ነበር፤ በዘመኑ ቀልድ የሚያበዛ ታዋቂ ጋዜጠኛ በአንድ የታወቀ ሪዞርት ሽንት ቤት ውስጥ አሳማ ያስቀምጣል። አሳማዋንም የከንፈር ቀለም (ሊፕስቲክ) ቀብቶ እንደ ሰው አስመስሎ። ዓላማው ሌላ ሳይሆን ፕራንክ ነበር። ክስተቱ የሪዞርቱን ባለቤት ፕራንክ አድርጎ ቢያልፍም ከዚያ በኋላ ግን አሳማ የከንፈር ቀለም ቢቀባ እንደ አሳማ መጮኹ (ኦይንክ ማድረጉ)፣ ጭቃ ላይ መንከባለሉ፣ አሰሱንም ገሰሱንም መብላቱ፣ … ባጠቃላይ አሳማነቱ አይቀርም ማለት ነው በሚል አባባል ተተካ። ከዚያም በ90ዎቹ ለቴክሳስ ሀገረግዢነት ይወዳደሩ የነበሩት አን ሪቻርድስ አባባሉን ተጠቀሙበት። ትልቁ ቡሽ በምርጫ ውድድር በነበሩበት ጊዜ የቡሽ አስተዳደር ለውጥ እንደማያመጣ አን ሲናገሩ “ዌል የአሳማዋን ከንፈር ሊፕስቲክ ቀብቶ ሞኒካ ነሽ ሊሏት ይቻላሉ፤ ግን አሳማነቷ ፈጽሞ አይቀየርም” ነበር … [Read more...] about “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ
ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር?
* የተዘነጋው የኢህአፓ ነጭ ሽብርና የወቅቱ ኢህአፓ አካሄድ ነጭ ሽብርም ሆነ ቀይ ሽብር በቀለም መጠሪያቸው ካልተለያዩ በቀር ሁለቱም ሽብር ናቸው። መስከረም 21 ቀን 1969 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሞርጌጅ ህንጻ ውስጥ ትሠራ የነበረችውን ባለቤታቸውን መኪናቸው ውስጥ ሆነው በመጠባበቅ ላይ እያሉ አድብተው ይጠብቁ በነበሩ የኢሕአፓ ነፍሰ ገዳዮች በቅርብ ርቀት በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው ያለውፈው በወቅቱ በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት የጊዜያዊ ጉዳዮች ሰብሳቢ የነበሩት ዶ/ር ፍቅሬ መርዕድ ነጭ ሽብር ከበላቸው ዜጎች አንዱና ነጭ ሽብር ራሱን ያስተዋወቀበት ኦፕሬሽኑ ነው። ሚስታቸውን ጋንዲ ሆስፒታል ጠይቀው ሲወጡ ቀይ መስቀል አካባቢ አድፍጠው ሲጠብቋቸው በነበሩ የኢህአፓ ነፍሰ ገዳዮች የተገደሉት ሌላው ነጭ ሽብር የበላቸው ዜጋ የወቅቱ የኢሰማኮ ሊቀመንበር የነበሩት ተመስገን … [Read more...] about ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር?
ዳኛውማ “ደርግ” ነው
የመጽሐፉ ርዕስ፡ “ዳኛው ማነው?” የብርሃነ መስቀል እና የታደለች ህይወት በኢሕአፓ የትግል ታሪክ 2012 ዓ.ም. እና የብርሃነመስቀል የእሥርቤት ቃል ምርመራ ሰኔ1971 ዓ.ም. ሙሉውን የመጽሐፍ ግምገማ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ዳኛውማ “ደርግ” ነው
ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር
መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ተፈረደባቸው ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም። ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት እንደማትሆን የሆላንድ ፍትህ ሚኒስትር አስታወቁ። አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም። በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየት ሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት … [Read more...] about ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር
“… አንድ ኮማንዶ…”
ጊዜው የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሕመማቸውና ሞታቸው በፈረቃ ተቃዋሚንም ሆነ ደጋፊን ዥዋዥዌ ሲያጫውቱት የነበረ ጊዜ ሲሆን፤ በተቃዋሚ በኩል መለስ ሲሞቱ ቢሯቸው ክፍት ስለሚሆን፤ ስልጣን የሚጠብቃት እረኛ በማጣቷ፤ ከቤተመንግሥስት ወጥታ ስትበር በወጥመድ ለመያዝ ያሰፈሰፈ ይመስል ነበር ቢባል፤ ብዙ የሚያሳማ ግንዛቤ አይመስለኝም። በዚያው ሰሞንም ነበር ጥምረትና ኦነገ (የጄ/ል ከማል ገልቹም) አሊያንስ ፈጠሩ ተብሎ የተወራው፤ ነገር ግን ወሬውን አጣጥመን ሳንጨርስ፤ በነሃሴ 1ቀን 2004 ዓ.ም. የተቋቋመው ስብስብ (ሰንጠረዥ ‹‹ለ››) ውስጥ ሁለቱ የአሊያንስ አባል ድርጅቶች ተነጣጥለው ገብተው እናገኛቸዋለን፤ ከዚያ ወዲህም የአሊያንስ ጉዳይ ኮሽታው ይጠፋል። (ሙሉው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about “… አንድ ኮማንዶ…”









