በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ ሰው ህይወት ክቡር ነው። ከዚያም አልፎ ህይወት ያለውን ነገር ሁሉ በከንቱ አለማጥፋት በተፈጥሮ ህሊናችን ውስጥ ህግ ሆኖ ስለተቀመጠም ነው የሰው ብቻ ሳይሆን የሌላም ፍጥረት ህይወቱ አለአግባብ በጭካኔ ሲቀጠፍ የሚዘገንነን። የሰውን ህይወት ለማጥፋት መጀመርያ የራስን ህሊና ፍርድ መጣስና ማቆሸሽን ይጠይቃል። ዛሬ በኢትዮጵያ በየቀኑ በጭካኔ የሚቀጠፉ ለጋ ወጣቶች፣ ማምለጥ የማይችሉ ህፃናት፣ አዛውንት አባቶችና እናቶችን ለሚመመለከት፣ ብሎም ለሚያስብ ንፁህ ህሊና ላለው እረፍት የሚነሳ ነው። በተለይ ባለፉት አምሳ ዓመታት በግፍ የጠፋው ኢትዮጵያውያን ህይወት እጅግ የሚዘገንን ነው። አዎ አባቶቻችን የውጭ ወራሪን ለመከላከልና በነፃነት ለመኖር ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል። አምባገነን የሆኑ የየአካባቢው መሳፍንት ግዛታቸውንና ሃብታቸውን ለማስፋት በሚያደርጉት … [Read more...] about የኢትዮጵያውያን ህይወት ዋጋ ምን ያህል ወርዷል?
alemu
ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር
መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ እድሜልክ እስራት ተፈረደባቸው ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም። ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት እንደማትሆን የሆላንድ ፍትህ ሚኒስትር አስታወቁ። አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም። በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየት ሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት … [Read more...] about ሆላንድ ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች መደበቂያ ገነት አትሆንም – ፍትህ ሚኒስትር