
የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢ ስለሆኑት የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶችና የንግድ ተቋማት ሲነሳ ግንኙነታቸው “በሬ ካራጁ” እንደሚሉት ዓይነት መሆኑን መጠቆም ጉዳዩን ምን አልባትም ማሳነስ ካልሆነ በቀር አይበዛም። ምክንያቱም አውሬው ኦሮሚያ ላይ በተቀመጡ የትህነግ ቅምጦች አማካይነት መረጃ እየተቅበለ በተሰጠው የቤት ሥራ መሠረት ኃላፊዎችን እያንገዋለለ ያስጠበጥብ ስለነበር ነው።
በዘመነ ት ህነግ ሪፖርተር ኦሮሚያ ላይ የሠራው ሤራና አሻጥር በዚህ አጭር ጽሑፍ የሚገለጽ አይደለም። ትህነግ ኦሮሚያን የተቆጣጠረው በሪፖርተር አማካኝነት ነበር ቢባል ምንም ማጋነን አይሆንም። በኦሮሚያ ላይ የሚከናወኑ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች መረጃ ይጠባ የነበረው ሪፖርተር ነበር።
ለምሳሌ፤ ኢህአዴግ ሥልጣን ላይ በነበረ ጊዜ፤ በተዋረድ የተቀመጡ የትህነግ ካድሬዎችና ሰላዮች ጥይት በማቀበል ተረኛውን ያስወቅጡታል። ሪፖርተርም ምን ገዶት ተጠንቶ በተዘጋጁ ዓምዶቹ እየበላለተ መረጃዎቹን ይረጫል። ለነገሩ ለዛሬ ኦሮሚያን ተነሳ እንጂ አሠራሩ ሁሉም ጋር ነበር ይቻላል።
ነገሩን በሌላ መልኩ እናስረዳ፤ ለምሳሌ ከኦሮሚያ አንድ ባለሥልጣን ለማስነሳት ወይም በዘመኑ አባባል ገምግሞ ለመገፍተር ሲፈለግ መረጃ ለሪፖርተር ይሰጣል። ሪፖርተር ባለሥልጣኑን አብጠልጥሎ የተሰጠውን መረጃ ያትማል። የሚቀጥለው የሪፖርተር ዕትም ከመውጣቱ በፊት ግለሰቡ ከሥልጣን ይነሳል፤ ወይም ካገር ይወጣል ወይም የደረሰበት ይጠፋል።
ምሳሌውን በማስረጃ እናብራራው፤ አሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከንቲባ/አስተዳዳሪ ይባል እንጂ መሪው፣ አድራጊና ፈጣሪው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንደሆነ ተገልጾ ባንድ ወቅት መረጃ መሰራጨት ሲጀመር፣ ሪፖርተር የአዲስ አበባ አስተዳደር መበስበስን የሚያሳይ መረጃ በጆንያ ተላከለት። ወዲያው አሊ አብዶ በሪፖርተር አዲስ አበባን የገደለ ባለሙሉ ሥልጣን አስተዳዳሪ ተደርጎ በተከታታይ ተቀጠቀጠ። በመጨረሻም የት ህነግ ስውሩ ከንቲባ ስሙ እንዳይነሳ አሊ አብዶ ፊት ለፊት ተደርጎ ከረከሰ በኋላ ፓርላማ ቀርቦ “እኔ አዲስ አበባን ገድያለሁ፣ እኔ ዓቅም የለኝም” ወዘተ በማለት ራሱን በመርገም የደብረጽዮንን መልክ አጸዳ።
እዚህ ላይ አሊ አብዶ የተሳካለት፣ ጎበዝ፣ ብቁና ለአዲስ አበባ ወርድና ስፋት የሚመጥን መሪ ነበር ለማለት ሳይሆን ሪፖርተር የመብያው ጥርስ መሆኑን ለማሳየት ነው፤ በተለይ ኦሮሚያ ላይ። አሊ አብዶ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ኦሮሚያ የቢሮ ኃላፊ ከሆነ በኋላ ይህንኑ ምሥጢርና ደባ ግልጽ ወጥቶ ባይሆንም መስክሯል። ለመቀርጠፍ ብቻም ሳይሆን ለሚፈልጉት አካል፣ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ጥቅም (የኢኮኖሚ ጥቅም ጉዳይን ወደፊት የምንመለስበት ይሆናል) አስፈላጊ ሲሆን የገጽታ ግንባታ ላይ ሪፖርተር ፊት ተሰላፊ እንደሆነ አስታውሶ ማለፉ አይከፋም።
ወደ አሁኑ እንምጣ፤ አሁን ላይ ሪፖርተር ኦሮሚያ ላይ ብዙም ተጽዕኖ የለውም፤ ትህነግ ኦህዴድን ሲያነግሥ እንደነበረው ኦሮሚያ ብልጽግና ውስጥ እጁ ስለሌለ፣ ቢሞክርም ማንነቱን ስለሚረዱት አማረ አረጋዊ ስትራቴጂውን በመቀየር ጨዋ ጨዋ የሚጫወት እየመስለ፣ እንደ ድመት እየታከከ ቀን ቆጣሪ ተስፈኛ ሆኗል። ስለሸለሙት የዘነጉት መስሎት እንደቀድሞ ፕሬስን ሰቅሎ መቦለት ይዳዳዋል። በግል ቢሮው ግለ ታሪኩ በሠራተኞቹ መሳለቂያ፣ ማፈሪያ የሆነው አማረ፣ ስልቱን ከኦህዴድ ወደ ኦነግና ሸኔ ቀይሮ “ሸኔ አዲስ አበባ ዙሪያ ነው፤ ከዱከም ጀምሮ ኢንቨስተር ለቆ እየወጣ ነው” በማለት ያረጠ ፖለቲካ ለመጫወት ይሞክራል። የአውሬው ሪፖርተር አማረ፤ ኦሮሚያን መበጥበጥ ላይ የተቸከለውን ወያኔያዊ ዓላማውን ለማሳካት አሁንም እንደሚንከላወስ መረጃ ጠቅሶ ማሳየት ይቻላል።
ትህነግ ለውጡን አሻፈረኝ ብሎ ወደ መቀሌ ሲሸሽ አዲስ አበባ የተቀመጠው የትህነግ አውራ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመሠረት መታሰቡ በተነገረ ማግስት፣ ዛሬ ከሻዕቢያ ጋር ሽርክና የፈጠሩትን እንደ ደብረጽዮንን ከነሙሉ ካቢኔው በመዘርዘር “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር” ብሎ አስተዋውቆን እንደነበር የሚታወስ ነው። ከላይ እንደተባለው ብልጽግና ውስጥ ይህን መረጃ የሚሰጠው የለምና ፍላጎቱን በ”ታማኝ ምንጮች” አስደግፎ ሰበር አለ።
ከዚያም በኋላ ምኑንም ምኑንም እያተመ፣ (ዝርዝር ማቅረብ ይቻላል) ዛሬ ላይ ደረሰ። ደብረጽዮንም ወደፊት መጣ፤ ሸኔ የተባለ በትህነግ የሚዘወር ደም አፍሳሽ የወንበዴ ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ግድያ ሲፈጽም፣ ሀገር ሲበጠብጥ ሪፖርተር ለሕዝብ ያዘነ ዘጋቢ ሚዲያ መስሎ መረጃዎችን ያወጣል። ዓላማው በገፊና ጎታች ስልት በቅብ ብል ሕዝብን ሆድ ማስባስ ነውና እንዲህ ያለው ዜና አይታለፍም ነበር። ዓላማውን ለማሳየት እንጂ ዜናው እንደዜና ሽፋን አያስፈልግም ለማለት አይደለም።






ጥያቄው የሚነሳው፣ እልቂቱን፣ መፈናቀሉን የሚዘግበው የአማረ ሪፖርተር፣ ይህን ተግባር የሚፈጽመውን ሸኔን አለመንካቱ ነው። ተበዳዮች፣ ሞትን ያመለጡ ዜጎች በገሃድ “ሸኔ ገደለን” እያሉ እየተናገሩ አማረ ሸኔን አይወቅስም። ይባስ ብሎ ለውጪ ሚዲያና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ግብዓት የሚሆን መረጃ በተለይ በእንግሊዝኛው እንደሚመች አድርጎ ሲያቀርብ ነው የኖረው።
ይህ ብቻ አይደለም፤ የሸኔ ታጣቂዎች ወደ ሰላም ሲመለሱ፤ እጅ ሰጥተው ብረት ሲያወርዱ፣ በሰፊ ቁጥር በሰልፍ እየተግተለተሉ “ለሰላም እጅ ሰጥተናል” ሲሉ ይህ ለሪፖርተር ዜና አይሆንም። ከዚህ በታች እንደ ማሳያ የተጠቀሱትን መመልከቱ የሪፖርተርን ማንነት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
የሪፖርተርን አውሬነት ያልተደረዱ ወይም ባልሰማ፣ ባላየ ሆነው ከሪፖርተር ጋር የሚሠሩ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶችና የክልል ቢሮዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ የተስተዋለ አይመስልም። በተለይ የንግድ ተቋማት ለሪፖርተር የሚሰጡት እጅግ ብዙ የማስታወቂያ ገንዘብ ብትችል ኦሮሚያን አፍርስልን ካልሆነ ግን በጥብጥልን ብለው የሚሰጡት መሆናቸውን አውቀውት ይሆን።






ከብዙዎቹ አንዱ የሆነውን ሲንቄ ባንክን እንውሰድ፤ ባንኩ የሪፖርተር የፕላቲኒየም አጋር ነው፤ ከዚህ በፊት ደግሞ ሪፖርተር ላይ ማስታወቂያ ሲያወጣ የኖረ ነው፤ ድረገጹም ላይ የሚታተመው ጋዜጣ ላይ። እንዴት ነው ነገሩ የሲንቄ ባንክ ሰዎች የት ህነግ ወንበዴዎች እነ ደብረጽዮን እነ ፈትለወርቅ ናቸው፧ እንዴት ሆኖ ነው የኦሮሚያ የንግድ ድርጅቶች ንግዳቸውንና ሪፖርተር ላይ የሚያስተዋውቁት፧ በት ህነግ ዘመን ቢሆን ኖሮ ተገድ ደው ነው እንል ነበር።
ከላይ እንዳልነው አውሬው ሪፖርተር ኦሮሚያን በመዳፉ ላይ አድርጎ የትህነግን ዓላማ ሲያስፈጽም የኖረ ነበር። አሁን ስሉሱ ዞሮ ባዶ የቀረ ቢመስልም የወሬ ቋቱ ነው እንጂ የብር ቋቱ በነሲንቄ ባንክና በመሳሰሉት ጢቅ ብሎ እየሞላለት ነው።
አውሬ ምን ቢሆን ለማዳ እንስሳ አይሆንም፤ ዛሬ አንገቱን የደፋ ቢመስልም የሞላለት ዕለት መፍጨትና ማድቀቅ ይጀምራል፤ እስካሁንም ምን ያህል እንደገፋበት፤ ምን ያህሉ እንደተሳካለት፤ ምን ያህሉ እንደከሰረ የሚታወቅ ነው። አሳሳቢው ዝምታ ግን የኦሮሚያ የንግድ ድርጅቶች ያለማቋረጥ አውሬውን መመገብ መቀጠላቸው ነው። የሚመግቡት ሲያጡ ራሳቸው ምግብ ይሆኑታል። ክፋቱ ግን ዳፋው ለኦሮሚያ መትረፉ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


Yes.