• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ

April 2, 2026 10:16 am by Editor Leave a Comment

የውጭ የደህንነት ተቋማት በአንድ ሀገር ውስጥ ወደፊት ስልጣን ወይም ተፅዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ ወጣቶችን ገና በለጋ እድሜያቸው የመመልመልና የራሳቸውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ግብ በሚያሳካ መልኩ ኮትኩቶ የማሳደግ ስልትን በስፋት ይተገብራሉ። ይህ ተግባር በዘርፉ “የልሂቃን ቀረጻ” (Elite Capture or Cultivation) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የተመረጡ ወጣቶችን የዓለም እይታ (Worldview) ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ የውጭ ሃገር ፍላጎትና ጥቅምን በሚያሳካ መልኩ አድርጎ መቅረጽ ነው። እነዚህ ተቋማት የአንድን ወጣት የወደፊት የመሪነት ዝንባሌ ቀድመው በመረዳት፣ በትምህርት እና በተለያዩ ስልጠናዎች ስም ከሀገሩ በማውጣት የአስተሳሰብ አድማሱን በእነሱ የፍላጎት ልክ ይቀርፁታል።

ይህ “Formative age” ወይም የማንነት ቀረጻ ምቹ እድሜ የአንድ ሰው ስብዕና እና መሰረታዊ እምነት የሚገነባበት ወሳኝ ወቅት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፤ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” እንደሚለው ሁሉ፣ በዚህ የእድሜ ክልል የሚሰጡ ስልጠናዎችና የሚፈጠሩ ግንኙነቶች ግለሰቡ ለቀሪው ዘመኑ የሚከተለውን የፖለቲካ መስመር ይወስኑታል። በመሆኑም፣ ምንም እንኳ ግለሰቡ “እኔ በራሴ ነፃ ፈቃድና እውቀት ነው የምንቀሳቀሰው” ብሎ ቢያስብም፣ የልቦና ውቅሩና የውሳኔ አሰጣጡ አስቀድሞ በሰለጠነበት “የአስተሳሰብ ማዕቀፍ” (Frame of Reference) የታጠረ እንዲሆን ይደረጋል። በዚህም ምክንያት፣ የውጭ ኃይሎች አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት ግለሰቡን እንደ ስትራቴጂያዊ መሳሪያ ይጠቀሙበታል።

የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ጉዞ የዚህ ውስብስብ ኦፕሬሽን ውጤት መሆኑን ለመረዳት የግድ የመረጃና ደህንነት ባለሙያ መሆን አይጠበቅብንም። እርሱ ራሱ “አልፀፀትም” በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቃውን የትግል ህይወት ታሪክ መጽሐፍ በጥሞና ማንበብና “ለምን?” ብሎ መጠየቅ ብቻ በቂ ነው። ጀዋር በዚህ መጽሐፉ፣ በጉልምስናው ወራት ወደ ሲንጋፑር ተወስዶ በወጣት አመራር ስልጠና ስም የህዝባዊ እምቢተኝነት የፖለቲካ ስልቶችን ከሀ እስከ ፐ እንዳስተማሩት በግልጽ ይተርካል። ይህም ለጀዋር ለወደፊቱ የፖለቲካ ስራው የሚያስፈልገውን ቴክኒካዊ እውቀትና ክህሎት እንዲገበይ ያደረጉበት ነበር። ጋዜጣ ላይ የሚወጡ የፓለቲካ ቅስቀሳ ጽሁፎችን እንዴት እንደሚፃፉ፣ ሚድያ እንዴት እንደሚመራ፣ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አመራር፣ ስትራቴጂና እቅድ ዝግጅት ስልጠና እንደታሰጠው ጀዋር ያለምንም ሃፍረት ሳይደብቅ በመፅሀፉ ላይ ይገልፃል።

በሲንጋፑር ቆይታው ወቅትም የባዕድነትና የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማው በሚል ሰበብ የስድሳዎቹን ትውልድ የፖለቲካ አመለካከትና ስልት ተሞክሮ እንዲቀስም ታቅዶ ከተዘጋጀ ግለሰብ ጋር እንዲገናኝ ተደርጓል። የቀድሞ የመኢሶን አባል ከነበረ ሰው ጋር የቅርብ ቤተሰባዊ ዝምድና እንዲፈጥር በማድረግ፣ ስለ “ያ ትውልድ” የአብዮት ትግልና የርዕዮተ-ዓለም ፍጭት እንዲጠመቅ ተደርጓል። ይህ ስልታዊ ግንኙነት ጀዋር ገና በወጣትነቱ የ60ዎቹን የፖለቲካ መንፈስ፣ ጥላቻና ግትርነት ላይ የተመሰረተ ስብዕና እንዲላበስ በማድረግ፣ ለወደፊት የፖለቲካ ጉዞው መሰረታዊ የሆነውንና ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነውን የልቦና ውቅር የገነባበት አጋጣሚ ሆኗል።

ይህ የልቦና ውቅር የመቅረጽ ስራ በአሜሪካ ቆይታውም በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል። ጀዋር እዚያም በነበረው ቆይታ ከቀድሞ የኢሕአፓ አባላትና እንደ ያሬድ ጥበቡና ነአመን ዘለቀ ካሉ የግራ ዘመም ፖለቲካ አራማጆች ጋር እንዲቀራረብ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረውለታል። ምንም እንኳን ጀዋር በዕድሜ የአዲሱ ትውልድ አባል ቢሆንም፣ በውስጡ የሰረጸው የፖለቲካ አስተሳሰብ ግን የዚያኛው ትውልድ ቅጂ ነው። ይህም የልቦና ውቅሩ ከአሁኑ ዘመን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ይልቅ፣ ተሸንፎ በወደቀው የባለፈው ክፍለ ዘመን የርዕዮተ-ዓለም ትግልና የሴራ ፖለቲካ ላይ ብቻ ተቸንክሮ እንዲቀር አድርጎታል።

በዚህም ምክንያት፣ የጀዋር የፖለቲካ ትግል ከህዝባዊ እምቢተኝነትና ከአመፅ ውጪ ሌላ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ አማራጭ መንገድን ለማሰብ ተቸግሮ ይታያል። አሁን ዓለም ያለችበትን ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር፣ የኃያላን ሀገራትን ፍላጎትና ቀጣናዊ ስጋቶችን ተረድቶ የሀገሩን ህልውና ለማስቀጠል የሚያስችል የትግል ስልት መቀየር ሲገባው፣ እርሱ ግን በአሮጌው መንገድ ላይ ብቻ ተቸንክሮ ቀርቷል። ልዩነቶችን አጥብቦ፣ በአንድ ሀገር ልጅነት መንፈስ ተባብሮ ሀገራዊ ህልውናን ከማስጠበቅ ይልቅ፣ ሁልጊዜም የታሪካዊ ጠላቶቻችንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ግብ የሚያሳካውን የግጭት አዙሪት ይመርጣል።

ይህ ዓይነቱ የግጭትና የህዝባዊ አመጽ ትግል ስልት፣ ኢትዮጵያ ከውስጥ በራሷ ዜጎች እንድትዳከም በማድረግ የብልፅግና እና የዲሞክራሲ ሀገረ መንግስት ግንባታዋን ለዘመናት ወደ ኋላ ሲጎትት የኖረ አጥፊ መንገድ ነው።

ጀዋር ልክ እንደ ጋሪ ፈረስ ግራና ቀኝ መመልከት እንደተሳነውና በአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲጓዝ እንደተገደደ መረዳት አይከብድም። የውጭ ኃይሎች ሆን ብለው የቀረጹትን የፖለቲካ የልቦና ውቅር ሀገራዊ ችግሮችን በሰከነ፣ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት እንዳይችል ትልቅ እንቅፋት ሆኖበታል።

ጀዋር ይህ ማንነቱ፣ ሃገራችን ዛሬ ከምትፈልገው የትብብርና የሰጥቶ መቀበል ውይይትና ድርደር ፖለቲካ ይልቅ፣ በጠባብና በአንድ አቅጣጫ በሚነዳ የትግል ስልት ውስጥ ታስሮ እንዲቀር አድርጎታል። ጀዋር ለሀገር የሚያስብ ቢመስልም፣ በተግባር ግን እየተከተለ ያለው መንገድ የውጭ ኃይሎችን ስትራቴጂያዊ ፍላጎት የሚያገለግልና የሃገርን አንድነት የሚሸረሽር ነው። ይህን የሕሊና ትብታብ ተረድቶ ከባዕዳን የአስተሳሰብ እስር ቤት መውጣት ካልተቻለ፣ የፖለቲካ ትግሉ ምንጊዜም ለሃገር ግንባታ ሳይሆን ለሀገር መፍረስ መሳሪያ መሆኑ አይቀሬ ነው።

አለባቸው ጉብሳ

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: ethiopian terrorists, jawar massacre, Jawar Mohammad, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule