የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ''የሰባ ገብዣ'' በሚል ርዕስ ስቅለት ዕለት ያቀረቡትን መልዕክት በተመለከተ እጅግ በርካታ ውግዘትና ፍረጃ ሲሰጥ እየተሰማ ነው። የሊቀ ጳጳሱን ስብዕና እና ማንነት ከማዋረድ ጀምሮ የሚሰጡት ስድብ አዘል “አስተያየቶች” ኢ-መንፈሳዊ፣ ጽንፈኛና አምባገነናዊ ናቸው። ገና ከጅምሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪና ብዙ ተከታይ አለን የሚሉ በሚሰጡ አስተያየት ሊቀ ጳጳሱን ከመዝለፍና ከማዋረድ አልፈው ግለሰባዊ ማንነታቸውን በማጉላት ሲሳደቡ ተሰምተዋል። እነዚህ “መምህራን” ብለው ራሳቸውን የሰየሙ ወይም ጥቂት ጊዜያት በቤተ ክርስቲያኗ የትምህርት ደጃፍ በማለፋቸው ብቻ “መምህር” ተብለው የሚጠሩ፤ በአቡኑ ላይ ለርካሽ የፖለቲካ መጠቀሚያ የሚውልና ከወንጌል አስተምህሮ የለቀቀ እጅግ ጸያፍ ንግግሮች በማሰማት ከሊቃውንቱ … [Read more...] about ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው
የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል”
“ሕገመንግሥቱ ያልፈለገ በሰላም ይሰናበታል” ብለው አለቆች ባስተማሩት መሠረት ትግራይ ከፌዴሬሽኑ መቀጠል አልፈልግም ስትል ይህንኑ ለምን ተግባራዊ አላደረገችም? ለምን ጦርነት ውስጥ ገባች? ምን ተፈልጎ ነው ወደ ጦርነት የተገባው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አለመኖሩ የኬሪያ ኢብራሒም ጥያቄ ነው። አንቀጽ 39 ተጠቅሶ መገላገል እንደሚቻል በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ የነበረ ድርጅት፣ ለዚሁ ህግ ጠበቃና ብቸና ሞግዚት ሆኖ የኖረ ፓርቲ ለምን ይህን ሁሉ ወጣት በነጻነት ሰበብ አስጨረሰ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ለማይፈልጉና ለሚያድበሰብሱ ኬሪያ “አስቡና መልሱን ወዲህ በሉኝ” የሚል እንደምታ ያለው መረጃ ሰንዝረዋል። ጦርነቱን አስመልክቶ የትህነግ ጠበቃና ተከላካይ ሆኖ የዘለቀው ጠያቂያቸው ዝም ብሎ ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይጠይቅ ያለፈው ይህ አንኳር ነጥብ ውሎ አድሮ አጀንዳ እንደሚሆን … [Read more...] about የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል”
ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ
በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ መሪዎች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል። በሥልጠናው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው፣ የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ የዞኑ መካከለኛና ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ወታደራዊ ሥልጠና ወስደዋል። ሥልጠናው በዕውቀት ላይ ተመሥርቶ ሕዝቡን ለማገልገል እና የጸጥታ መዋቅሩን አደራጅቶ ለመደገፍ እና ለመምራት ዓላማ አድርጎ መሰጠቱ ተገልጿል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የተደራጀና የተቀናጀ ሕዝብ ችግሮችን መቋቋምና ፈተናዎችን ማለፍ ይችላል ብለዋል። ለዚህም ከላይ እስከ ታች ያለውን መሪ ወታደራዊ … [Read more...] about ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ
ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው
በትግራይ የተኩስ ማቆም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ያኮረፈው ሻዕቢያ ከግብጽ በወሰደው ውክልና “አንጃ” ከሚባለው የትህነግ ውስን ኃይልና በአማራ ኦሮሚያ ክልል ጠብ መንጃ ካነሱ ኃይሎች ጋር ግንባር ገጥሞ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊከፍት ያሰበውን ውጊያ በአቅም ማነስና ምድር ላይ ባሉ እውነታዎች አስገዳጅነት ለማራዘም መወሰኑ ተሰማ። የኤርትራን የጦርነት ዝግጅት ከውስጥና ከውጭ የሚከታተሉ የኢትዮሪቪው የመረጃ ሰዎች እንዳሉት፣ ከግብጽ በወሰደው ውክልናና ከግል ስጋቱ በመነሳት ከኤርትራ ውጭ በኢትዮጵያ ግዛት ሊጀመር ያሰበውን ጦርነት ለማቆየት የወሰነው ምድር ላይ ባሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሳቢያ ዓቅሙ እንደማይፈቅድ ተረድቶ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት “ጦርነት አንፈልግም። ከነኩን ግን ምላሹ የከፋ ይሆናል” ማለቱ የሚታወስ ነው። እንደ ዜናው ሰዎች ከሆነ የመጀመሪያው ምክንያት በትግራይ … [Read more...] about ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው
“አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ
ሰሞኑን በሸዋ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ባለበት እንደሚቀጥል፣ ሌሎች አደረጃጀቶች ለመቀላቀል ከፈለጉ በራሳቸው ተደራጅተው ወደ አሕፋድ እንዲመጡ ተጠየቀ። ከጥቂት ቀናት በፊት በሸዋ ፋኖ አደረጃጀቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መከሰቱን እና ተዋጊዎችም መሞታቸውን በፋኖ ውስጥ ያሉት አዋጊዎች ገልጸዋል። ጉዳዩ የተከሰተው በደብረሲና አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የራምቦ ክፍለጦርን ወደ ሬማ እንዲሄድ በተደረገው ውሳኔ ነው። ውሳኔው የተላለፈው በወታደራዊ አመራሮች ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ የተፈጸመ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ። ሬማ በሚባለው አካባቢ እንደሚንቀሳቀስ የሚታወቀው በአጼ ፋሲል ክፍለጦር ሥር የሚገኘው … [Read more...] about “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ
መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን!
የመለስ ዜናዊ የግል ጠባቂ/አጃቢ የነበረው ሚኪ ራያ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ቪዲዮ ላይ የቀድሞ ጌታውን ማንነት ባልታወቀ ምክንያት እያዝረከረከው ነው። በትግሪኛ የተናገረውን አስፋው አብርሃ በቴሌግራም ገጹ ተርጉሞ አቅርቦታል፤ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ከኢትዮጵያ በበለጠ ለኤርትራ ያስቡና ይጨነቁ ነበር። ይህ የሁለቱ ሰዎች ስሜትና ባህሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገልጧል - ከ1992ቱ ጦርነት በፊት፣ በጦርነቱ ወቅት እና ከጦርነቱ በኋላ ምንም ያልተቀየረ ስሜት! ከጦርነቱ በፊት .... ሚኪ ራያ "መለስ ዜናዊ መዝናናት ሲፈልግ ወደ አስመራ ይመላለስ ነበር፤ በረራውም Unofficial በረራ ነበር ይለናል - ያው በድብቅ ማለት መሆኑ ነው። “መለስ ዜናዊ ከስራ ውጪ መዝናናት ሲፈልግ አስመራ ነበር የሚሄደው። የራሱን ሰዎች ብዙም … [Read more...] about መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን!
የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የቃብትያ ሁመራ ወረዳና የዞኑ “የተከዜ ዘብ” በባለፉት ሳምንታት ሲሰለጥኑ የቆዩትን ሰልጣኞች በዛሬ ቀን በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ፣ የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ተመርቀዋል። ወልቃይት ጠገዴ የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት መጠበቂያ መሠረት ናት። ከጥንት እስከ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሏል። በተከፈለው መስዋዕትነትም የሀገር ሉዓላዊነት ከነክብሩ ኖሯል። ኢትዮጵያውያን ለነፃነታቸው እና ለሉዓላዊነታቸው በአንድነት እና በኅብረት እየተነሱ ጠላታቸውን ድል ሲመቱ ኖረዋል። ድል ማድረግ የኢትዮጵያውያን የሥነ-ልቦና እና የባህሪ … [Read more...] about የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ
አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ
ሪፖርተር በሌላ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በኃላፊነት ተጠየቀ፤ ይህንን የጠየቀው የአዲስ አበባ አስተዳደር ሲሆን ሪፖርተር መረጃውን ካላስተካከለ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። መግለጫው ከዚህ በታች ይገኛል:- ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፣ የተዛባና ሚዛናዊነት የጎደለው መረጃን ግልፅ ስለማድረግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በመጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም "በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤና ተሳትፎ ማሳደግን" አላማው ያደረገ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ይታወሳል። መድረኩ የታለመለትን አላማ እንዲያሳካም በእለቱ የውይይት መድረኩን እንዲዘግቡ በጽ/ ቤታችን ከተጠሩት ከ15 በላይ የሚሆኑ የመደበኛና የዲጂታል ሚዲያዎች ተገኝተው ዘገባቸውን … [Read more...] about አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ
ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ በጀት ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት አንድም ብር ለመንግሥት በቀጥታ አበድሮ እንደማያውቅ አስታውቋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት አንድም ብር አበድሮ አያውቅም! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ በጀት ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት አንድም ብር ለመንግሥት በቀጥታ አበድሮ አያውቅም። መንግሥት ከሀገር ውስጥ የንግድ ባንኮች (በብሔራዊ ባንክ በኩል ለሽያጭ ከሚቀርበው የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ውጪ) በቀጥታ የመበደር አሠራርም ሆነ ልምድ የለውም። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ በተገባደደው ሳምንት ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስምንት ወራት የስራ አፈጻጸም ማቅረባችንን ተንተርሶ በሪፓርተር … [Read more...] about ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ
“ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ
ትላንት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ "UMD" ለተባለ ሚድያ ዘለግ ያለ ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል። በርካታ ጉዳዮች ባነሱበት ቃለ-መጠይቃቸው "አሁንም ትግራይ መላ ቅጡ በማይታወቅ ሁኔታ ላይ ናት ፤ በርካታ የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ጭንቅና መከራ ውስጥ ይገኛል" ብለዋል። ጥያቄ - በሁለት አመቱ የፕሬዚዳንትነት ቆይታህ ያልጠበቅከውና በጣም መጥፎ ነበር ብለህ የምትገልፀው አጋጣሚ አለ? የጌታቸው ምላሽ - አዎ በጣም ያልጠበቅኩትና መጥፎ ነበር የምለው አለኝ። እኔን እስከማስወገድ ድረስ ፍላጎት እንደነበራቸው አላውቅም ነበር። መጨረሻ ላይ ግን ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ወደ ኤርፖርት ሳመራ እኔን አግቶ ለማስቀረት ሙከራ አደረጉ። ለማገት መሞከራቸው አይደለም እኔን ያበሳጨኝ። እኔ የተበሳጨሁት ሊገድሉኝ አቅደው እንደነበር ያወቅኩኝ ጊዜ … [Read more...] about “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ