• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ?

April 2, 2026 10:52 am by Editor Leave a Comment

ሰዎች ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ናችሁ ተብለው ሲያዙ ይደነግጣሉ፤ ከሁሉ በላይ የሚያስደነግጠው ደግሞ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው የሚነሱት ፎቶ ነው። ሕይወታቸውን ሁሉ የሚያበላሽ፤ ዕድሜ ልካቸውን ሲከተላቸው የሚኖር ፎቶ ነው። ብዙዎች ሲነሱ ይበሳጫሉ፤ ሌላ ሰው ለመምሰል ይሞክራሉ፤ ንዴትና ቁጭር ይታይባቸዋል፤ ዓይነቱ እጅግ ብዙ ነው።

ዱሮ ላይ ፎቶ ቤት ሄዶ መነሳት ብርቅ ነበር። ፎቶ አንሺ ማለት ከሐኪም በላይ ነው የሚከበረው፤ ሁኑ ያለውን ሁሉ ሆኖ መነሳት የግድ ነው። የማይሆኑ ትዕዛዞችን ሊሰጥ ይችላል፤ “የተናደደ ሳቅ ፊትህ ላይ አሳይ”፤ “ተመስጠህ ተበሳጭ”፤ ወዘተ የሚሉ።

ፊንቴክን በተመለከተ ተጠርጥረው የተያዙት የተነሱት ፎቶ ትንሽ ለየት ያለ ነው። ዱሮ “ፎቶ ቤት ሄደህ ፎቶ ትነሳለህ” እንደተባለ ልጅ ፍልቅልቅ ብለው መነሳታቸው ግራ ያጋባል። አንድ ሰው ለብቻው በሺዎች የሚቆጠር ፎቶ በስልኩና በመሰል መሣሪያዎች እንደፈለገ በሚያነሳበት ዘመን “ፎቶ ተነሳሁ” በሚል ስሜት “ተጽዕኖ ፈጣሪዎቻችን” መነሳታቸው ከኛ ተማሩ ለማለት ይሆን?

አጭበርብራችኋል ተብለው የተከሰሱበት ወንጀል ምንም አልመሰላቸውም ወይስ ፖሊስ ጣቢያው መዝናኛ እና ደስ ሲል ደግሞ ፎቶ መነሻ ፓርክ መስሏቸዋል? እንዴት ነው 1400 ያህል ሰው ብሬን ተጭበረበርሁ ብሎ እያለቀሰ እያለ እነሱ በዚህ ደስታ የሚነሱት? የሩብ ዓመት በጀት የሚመስል ብር አጭበርብራችኋል ሲባሉ ምኑ ነው ያሳቃቸው? ፖሊስ ይህንንም አብሮ ቢመረምር ጥሩ ሳይሆን አይቀርም።

ለማንኛውም የደረሰው ጉዳት ባጭር ይህንን ይመስላል፤

  • በፊንቴክ መኪና አቀርባለሁ ባይነት 1,430 ሰው የጉዳት ሰለባ ሆኗል
  • ፊንቴክ 1.7 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል
  • ገዢዎችን በተለይ ያማለለው ጉዳይ በሦስት ወር መኪና እንደሚያገኙ፤ ለዚህም 950 ሺህ ብር ቀብድ እንደሚከፍሉ፤ በአምስት ዓመት ክፍያ ብቻ እንደሚጠበቅባቸው ቃል መገባቱ ነው
  • ዐቃቤ ሕግ የታዋቂ ሰዎች አስተዋዋቂነት፤ የማኅበራዊ ሚዲያ ሽፋን ለመጭበርበሩ የወንጀሉ ዋነኛ አካል ነው ብሏል
  • የመጀመሪያ አካባቢ መኪና በተባለው ጊዜ መሰጠቱ እና ይህም ባደባባይ መታየቱ ለወንጀሉ ጥሩ ድጋፍ የሰጠ መሆኑን መርማሪዎች ጠቁመዋል
  • ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች እየታደኑ ነው፤ ጉዳዩ ከፊንቴክም በላይ እየሆነ ነው፤ 19 ክስ ተመሥርቷል

ፌዴራል ፖሊስ ያወጣው መረጃ ከዚህ በታች ይገኛል፤

በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩት የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መስራችና ባለቤቶች ላይ ምርመራ ተጠናቆ ክስ መመሥረቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፊንቴክ ኢንቨስትመንት የግል ድርጅት መስራችና ባለቤቶች የሆኑት ዳንኤል ዮሃንስ ኢየሱስ እና ግርማይ ገብረሚካኤል ይህደጎ የተባሉ ተጠርጣሪዎች፣ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በመጠቀም ከ1,200 በላይ ዜጎችን በማጭበርበር የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት በማድረሳቸው ፖሊስ በ19 ዓይነት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራውን አጣርቶ ለዓቃቤ ሕግ በመላክ ክስ እንዲመሰረትባቸው ማድረጉን ገልጿል።

መጀመሪያ ላይ ክሱ የቀረበው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የነበረ ቢሆንም፣ ወንጀሉ ውስብስብ፣ ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቅና ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ ምርመራው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በኩል በሰፊው ሲጣራ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪ ዳንኤል ዮሃንስ ክስ ተመስርቶበት በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል የተደረገ ሲሆን፣ ሌላኛው ተጠርጣሪ ግርማይ ገብረሚካኤልን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

ግርማይ ገብረሚካኤል በአውሮፓውያኑ 2010 የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ወቅትም “አስካሉካን” በተባለ ድርጅት ስም ዜጎችን በማጭበርበር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ይዞ ከሀገር ቢሰወርም፣ በወቅቱ በኢንተርፖል አማካኝነት ተይዞ ለሕግ መቅረቡን የወንጀል ሪከርዱ ያመላክታል።

ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎችን በ90 ቀናት ውስጥ የመኪና ባለቤት እናደርጋችኋለን በማለት የ950 ሺህ ብር (50%) ቅድመ ክፍያ እንዲፈጽሙና ቀሪውን ገንዘብ ያለወለድ በ5 ዓመት በባንክ ብድር እንደሚጨርሱ በማሳመን ነው ወንጀሉን የፈጸሙት።

ሕዝብን ለማሳመን ሲሉ 148 መኪኖችን ከጅቡቲ በማስገባት 100ዎቹን ለተወሰኑ ሰዎች ማከፋፈላቸውንና ቀሪዎቹን 48 ዘመናዊ መኪኖች በድብቅ መሸጣቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።

በተጨማሪም 350 መኪኖች ወደ ሀገር መግባታቸውንና 400 መኪኖች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የሚገልጽ የሐሰት መረጃ ለተጎጂዎች ሲሰጡ እንደነበር በምርመራው ተደርሶበታል።

ተጠርጣሪዎቹ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ከሆነው የቻይናው BYD ካምፓኒ ጋር ምንም ዓይነት ውል ሳይኖራቸው ውል እንዳላቸው በማስመስልና በመስቀል አደባባይ ከተለያዩ ቦታዎች በትውስት ያሰባሰቧቸውን መኪኖች ድርጅቱ ያስገባቸው በማስመሰል የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

በጅቡቲ “አልፋቲዞ” የተባለ ድርጅት በማቋቋም መኪኖቹን በ10% ቅድመ ክፍያ ተረክበው፣ ቀሪውን 90% ክፍያ ሳይፈጽሙ ጅቡቲ ላይ መልሰው መሸጣቸውም በምርመራው ተረጋግጧል።

ፖሊስ እንዳረጋገጠው ተጠርጣሪዎቹ ከእያንዳንዱ ተጎጂ ለቅድመ ክፍያ፣ ለመንግሥት ታክስና ለቻርጀር ማሰሪያ በሚል በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን 365 ሺህ ብር ተቀብለዋል።

የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅትን ባልተገባና በተጋነነ መልኩ በማስተዋወቅ፣ በሕገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ተጋሪ በመሆን የተጠረጠሩት አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ሰለሞን ቦጋለ፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ አብርሃም ግዛው፣ ይገረም ደጀኔ፣ መንሱር ጀማል እና ካሊድ ናስር በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱም በእነዚህ ግለሰቦች ላይ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። እነዚህ ግለሰቦች ዕውቅናቸውን በመጠቀም የሐሰት መረጃዎችን በማሰራጨትና እያንዳንዳቸው 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የ”BYD Song Plus” መኪና በስጦታ በመቀበል ወንጀሉን በማሳለጥ ተጠርጥረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማጭበርበር፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ (Money laundering) እና በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ይህ ውስብስብ ወንጀል ተጣርቶ ክስ እንዲመሰረት ከፖሊስ ጋር በትብብር ለሠራው የፍትሕ ሚኒስቴር እና መረጃ ሲሰጥ ለነበረው ማኅበረሰብ ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረቡን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: Abraham, BYD cars, daniel, Girmay, Khalid, Ponzi Scheme, Serawit, Yigerem

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule