ሰዎች ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ናችሁ ተብለው ሲያዙ ይደነግጣሉ፤ ከሁሉ በላይ የሚያስደነግጠው ደግሞ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው የሚነሱት ፎቶ ነው። ሕይወታቸውን ሁሉ የሚያበላሽ፤ ዕድሜ ልካቸውን ሲከተላቸው የሚኖር ፎቶ ነው። ብዙዎች ሲነሱ ይበሳጫሉ፤ ሌላ ሰው ለመምሰል ይሞክራሉ፤ ንዴትና ቁጭር ይታይባቸዋል፤ ዓይነቱ እጅግ ብዙ ነው። ዱሮ ላይ ፎቶ ቤት ሄዶ መነሳት ብርቅ ነበር። ፎቶ አንሺ ማለት ከሐኪም በላይ ነው የሚከበረው፤ ሁኑ ያለውን ሁሉ ሆኖ መነሳት የግድ ነው። የማይሆኑ ትዕዛዞችን ሊሰጥ ይችላል፤ "የተናደደ ሳቅ ፊትህ ላይ አሳይ"፤ "ተመስጠህ ተበሳጭ"፤ ወዘተ የሚሉ። ፊንቴክን በተመለከተ ተጠርጥረው የተያዙት የተነሱት ፎቶ ትንሽ ለየት ያለ ነው። ዱሮ "ፎቶ ቤት ሄደህ ፎቶ ትነሳለህ" እንደተባለ ልጅ ፍልቅልቅ ብለው መነሳታቸው ግራ ያጋባል። አንድ ሰው ለብቻው በሺዎች የሚቆጠር ፎቶ … [Read more...] about ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ?

