• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ!

October 14, 2026 11:04 pm by Editor Leave a Comment

  • በታደሰ ወረደ ተከፋዮች የሚመራው “ዳግም ወደ ሥልጣን የመመለስ” ቅዠትና ሴራ በአስቸኳይ ሊገታ ይገባል!

ከጥቂት ቀናት በፊት በሀገር መከላከያ ልዩ ብቃት ከነበሩበት የቁም እስር ነጻ የወጡት ታደሰ ወረደ እና ሌሎች ሦስት የትህነግ ከፍተኛ መኮንኖች ጉዳይ ለብዙዎች አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል። የታደሰና አብረው የነበሩት ከእስር የወጡበት መንገድ እና ቀጣይ የፖለቲካ እጣ ፈንታቸው በክልሉ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ወገኖች መካከል ከፍተኛ የትርክት ጦርነት አስነስቷል።

ጥቅምት 24 ላይ በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የደረሰውንና በነታደሰ የተመራውን ጥቃት ሳንጠቅስ እንለፈውና፤ “የትግራይ መከላከያ ኃይል” (TDF) በማለት ትህነግ ያቋቋመውን ሕገወጥ ታጣቂ ቡድን ዋና አዛዥ በመሆን የመሩት ታደሰ ወረደ በቀጣይ ደግሞ የጌታቸው ረዳ ምክትል በመሆን ተሹመው እንደ ነበር ይታወሳል። ከትህነግ ሰዎች ጋር በነበራቸው ውግንና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት የተዋቀረውን ጊዜያዊ አስተዳደር በሙሉ አቅሙ እንዳይሠራ ያደረጉት ታደሰ፤ የጸጥታ ኃይሉን በመያዝ መዋቅሩን በመበጣጠስ፤ ጌታቸውን አላሠራም ብለው በመጨረሻም ጌታቸው ከሞት አምልጦ ከክልሉ መውጣቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

በቀጣይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ኃላፊ ሆነው ከተመደቡ ጊዜ ጀምሮ በረቀቀ መልኩ ከትህነግ ጋር በመሥራት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር መሣሪያ በኤርትራ ድንበር በኩል ወደ ትግራይ እንዲገባ የተደረገው በታደሰ የሥልጣን ዘመን መሆኑ አሁን በቁጥጥር ሥር እየዋሉ የሚገኙት ትጥቆች ምስክር ናቸው።

ይህንን ሁሉ ሀገር ያጠፋ የሕዝብ ሕይወት የቀጠፈ ተግባር የፈጸሙ ግለሰብን አሁን ላይ ደግሞ በሚከፈላቸው ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች (ዳዊት ከበደ እና ሚዲያው አውራምባ) አማካኝነት ታደሰን ዳግም ወደ ሥልጣን የመመለስ ዘመቻ ተጀምሯል። ይህ እንቅስቃሴ ለትግራይ ሕዝብ ሰላምና ህልውና ሳይሆን፣ ራሳቸውን ከሕግ ተጠያቂነት ለመከላከል የሚደረግ የመጨረሻ የቁማር ጨዋታ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

መታወቅ የሚገባው ወሳኙ ጉዳይ፤ ታደሰ ወረደ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና የገቡትን 8 መሠረታዊ ቃል ኪዳኖች (ተፈናቃዮችን መመለስ፣ ትጥቅ መፍታት፣ የሕግ የበላይነት ማስፈን፣ እና የመሳሰሉትን) አንዱንም ሳይፈጽሙ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ግለሰብ መሆናቸው ነው። ከዚህ ይልቅ ይባስ ብሎ ለአዲሱ ግጭትና አለመረጋጋት በር በመክፈት፣ እንደ ደብረጽዮን ባሉ ቡድኖች እጅ ክልሉ እንዲወድቅና የጦር መሳሪያ እንዲከማች መንገድ የጠረጉ ሰው ናቸው።

የተዘነጋ ይመስላል እንጂ መታወስና መጠየቅ የሚገባው ጉዳይ ትህነግ ታደሰን ወረደን ከሥልጣን “አስወግዷቸው” (ተስማምተውም ሊሆን ይችላል ድራማውን የሠሩት) እዚያው ትግራይ ያለ አንዳች ችግር በሰላም መቆየት እንዴት ቻሉ የሚለው ነው። ያውም ጠላቴ ነው ከሌሎች ታጣቂ ኃይሎች ጋር ተባብሬ አስወግደዋለሁ በተባለው የዐቢይ መንግሥት የተሾመን ሰው ከሥልጣን ካስወገዱ በኋላ ዝም ብሎ መተው ትህነግ የሚታወቅበት ባህርዩ አይደለም።

በአሁኑ ጊዜ ታደሰ ወረደ አዲስ አበባ ተቀምጠው የትግራይን ሕዝብ እጣ ፈንታ ለመወሰን በሚሞክሩ እንደ ዳዊት ከበደ ባሉ በክፍያ የሚሠሩ “አፈ ቀላጤዎች” አማካኝነት “የሥልጣን ዘመኔ አልተጠናቀቀም” የሚል አጀንዳ እያስፋፉ ይገኛሉ። አዲስ አበባ በመመላለስ በትግራይ ሕዝብ ስም የሚፈቀዱ በጀቶችና ግብዓቶች ለትህነግ እንዲደርሱ ሲያደርጉ የነበሩት ታደሰ፣ ዛሬ በሚዲያ ታጥበው “ከደሙ ንጹህ” ሊሆኑ አይችሉም።

ስለዚህ የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ሕዝብ ሊወስዱት የሚገባ እርምጃዎች አሉ፤

  1. ለፌዴራል መንግሥት፦ በሽግግር ሒደቱ ላይ መንግሥት የሠራውን ስህተት ከመድገም ሊቆጠብና የትግራይን ሕዝብ ሰላም በድጋሚ ሊቀለብሱ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን በትዕግስት ማየት ማቆም አለበት። ታደሰ ወረደ ከሙስና ጀምሮ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት ከከተቱ ቡድኖች ጋር ባላቸው ቀጥተኛ ግንኙነትና የኤርትራ ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ስለገባበት ጉዳይ በሕግ ሊጠየቁ ይገባል።
  2. ለሚዲያዎችና አክቲቪስቶች፦ በጥቅም ተደልለው በትግራይ ሕዝብ ስቃይ ላይ የሚቆምሩና ወንጀለኞችን ለማጠብ የሚሠሩ አካላት ከዚህ የወንጀል ሥራ ሊቆጠቡ ይገባል።
  3. ለታደሰ ወረደ፦ የቀድሞ ታጋዮችና የለውጥ ኃይሎች እንደሚመክሩት፣ ካለፈው ጥፋት በመማር ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸውና ጡረታቸው ማመራቱ ብቸኛው አማራጭ ነው። ከዚህ አልፈው ወደ ሥልጣን ለመመለስ የሚሄዱበት መንገድ ራሳቸውን ወደ ሕግ አቅርቦ “ፍረዱብኝ” እንደማለት ይቆጠራል።
  4. ለትግራይ ሕዝብ፡- በብዙ መስዋዕትነት ያገኘኸውን ሰላም ለመንጠቅ ለሚፈልጉ ኃይሎች ዕድል ፈንታ አትስጣቸው፤ ሰላምህን አጥብቀህ ጠብቅ። ከዚህ በኋላ እንደ ታደሰ ዓይነት ትህነጋዊ መሪ ሳይሆን የሚገባህ በራስህ ሕሊና ወደህና ፈቅደህ፣ በድምፅህ መርጠህ የምታስቀምጠው፤ ሲያፈነግጥ ደግሞ በድምፅህ መልሰህ የምትሽረው መሪ ነው የሚገባህ፤ አበርትተህ እዚህ ላይ ሥራ።  

“የትግራይ ሕዝብ ከእንግዲህ በራሱ ምርጫ መሪዎቹን መምረጥ አለበት! በሴራና በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ የሚደረግ የስልጣን ሽሚያ በቃ ሊባል ይገባል!»

ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Filed Under: Editorial, Middle Column Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tadesse worede, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule