ላለፉት 50 ዓመታት በትግራይ ሕዝብ በማስጨነቅና በማሸበር በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ሲሸማቅቁ የኖሩት የትህነግ የሚዲያ ተቋማት ስም ባስቸኳይ መቀየር ይገባል። እነዚህ በትግራይ ክልል የሚገኙና የሕዝብ ሀብት የሆኑ የሚዲያ ተቋማት አሁንም ድረስ የሕዝቡን ስነ-ልቦና በነጻነት ለመገንባትና ገለልተኛ ሆነው ለማገልገል የተሸከሙት ስምና ማንነት ከፍተኛ ማነቆ ሆኖ እንደሚቆይባቸው ምንም ጥርጥር የለም። በተለይ እንደ ድምፂ ወያነ እና የትግራይ ቴሌቪዥን ያሉ ተቋማት ከደርግ ሥርዓት በኋላ ላለፉት ሦስት አስርተ ዓመታት ያህል የትህነግ (ሕወኃት) የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ማሽን ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል። እነዚህ የሚዲያ ተቋማት በ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ወቅትም ሆነ ከዚያ በኋላ ባሉት ሠላሳ ዓመታት፣ አገር ወዳዱን የትግራይ ሕዝብ አእምሮ ለመቆጣጠርና የቡድን አስተሳሰብን ለመርጨት እንደ ዋና … [Read more...] about በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል!
Editorials
ርዕሰ አንቀጽ
በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ!
በታደሰ ወረደ ተከፋዮች የሚመራው “ዳግም ወደ ሥልጣን የመመለስ” ቅዠትና ሴራ በአስቸኳይ ሊገታ ይገባል! ከጥቂት ቀናት በፊት በሀገር መከላከያ ልዩ ብቃት ከነበሩበት የቁም እስር ነጻ የወጡት ታደሰ ወረደ እና ሌሎች ሦስት የትህነግ ከፍተኛ መኮንኖች ጉዳይ ለብዙዎች አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል። የታደሰና አብረው የነበሩት ከእስር የወጡበት መንገድ እና ቀጣይ የፖለቲካ እጣ ፈንታቸው በክልሉ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ወገኖች መካከል ከፍተኛ የትርክት ጦርነት አስነስቷል። ጥቅምት 24 ላይ በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የደረሰውንና በነታደሰ የተመራውን ጥቃት ሳንጠቅስ እንለፈውና፤ “የትግራይ መከላከያ ኃይል” (TDF) በማለት ትህነግ ያቋቋመውን ሕገወጥ ታጣቂ ቡድን ዋና አዛዥ በመሆን የመሩት ታደሰ ወረደ በቀጣይ ደግሞ የጌታቸው ረዳ ምክትል በመሆን ተሹመው እንደ ነበር ይታወሳል። ከትህነግ … [Read more...] about በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ!
ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው?
ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) በማለት የሚጠራው ሕገወጥ የወንበዴዎች ቡድን ተክሎብን እና ጥሎብን የኼደው መርዝ እስካኹን አልፋታ ብሎን የመከራ ዘመናችንን አርዝሞታል። ሀገርን በዘር ከፋፍሎ፤ ሕዝብን እንደ ከብት በክልል ወስኖ፤ ኢትዮጵያዊነትን በሰፈርና በወንዝ ወስኖ፤ ለዘመናት አብሮ የኖረን ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያይ አድርጓል። እንዳሰበው ባይሳካለትም ሀገራችን ከመፍረስ ድና አኹን ያለችበት ቁመና ላይ ትገኛለች። ትህነግ ግን ነጻ አወጣዋለኹ ብሎ ሲነግድበት የነበረውን ሕዝብ የምድር ሲዖል ውስጥ ጨምሮ እያሰቃየው ይገኛል። ወደ ጉዳያችን ስንመለስ፤ ትህነግ መርዙን ተፍቶብን ወደ ትግራይ ኼዶ ቢመሽግም አሁንም ግን ግድያ፣ ደም ማፍሰስ፣ ማፈናቀል፣ አልቆመም። በሀገሪቱ ላይ የሚፈጽመው ዕልቂት የገፊና ጎታች ሤራ እንደሆነ በተደጋጋሚ ያነሳነው ጉዳይ ነው። ጎልጉል በዚህ … [Read more...] about ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው?
ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው
ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን፤ በ4 ወራት ይጠናቀቃል የተባለውን እና 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በዓመት ማምረት ይችላል ተብሎ የተነገረለትን የማዳበሪያ (የዩሪያ) ፋብሪካ ለመገንባት ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ስምምነት ሲፈረም በሰጡት አጭር መግለጫ ፋብሪካው እንደ ዓባይ ግድብ እንደማይሆን ተናግረው ነበር። ይህ ፕሮጀክት “በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚመራ ስራቴጂክ ፕሮጀክት ነው፤ በከፍተኛ ዲሲፒሊንና ቁጥጥር የሚደረግ ነው፤ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሜጋ ፕሮጀክት ነው፤ ሕዳሴ ላይ የነበረው ስህተት እዚህ አይደገምም፤ በጥንቃቄና በጥናት የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፤ በዕውቀትና በጥንቃቄ ብቻ ነው የሚመራው፤ ምክንያቱም አንድ ፕሮጀክት መጀመራችን ሳይሆን በጥንቃቄ ካልመራነው ተጨማሪ ኃብትና ጊዜ ስለሚያባክን እንደዚህ ዓይነት ስህተት … [Read more...] about ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው
እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ!
በክህደት የሚታወቀው ትሕነግ “ዝረፉ፣ ጨፍጭፉ፣ አውድሙ” ብሎ ልኮ ላስጨረሳቸው ሁሉ በጅምላ “የሰማዕትነት ማዕረግ” አከናንቦ ሐዘን አውጇል። ይህ የትሕነግ የሰማዕትነት ማዕረግ የመንዙን መብረቅ እሸቴን፣ ኮሎኔል ማራኪዋ ምክትል ዐሥር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄን፣ የክምር ድንጋዩ ትንታግ ጌጤ መኳንንት አባ ረፍርፍ፣ በስልኩ ብቻ 15 የጁንታ ታጣቂዎችን ማርኮ፤ 40ዎቹን እንዲደመሰሱ ያደረገው የጋይንቱ ጀግና ሰፊው በቀለ ናደው፣ የምድር ድሮኖች (አፋር) - የዕቶን ውስጥ ነበልባሎችን፣ አገር ብለው ከየአቅጣጫው የተመሙ የኢትዮጵያን ልጆች “አሸባሪ” አድርጎ መፈረጅ መሆኑን ስንቶች ተረዳን? ሸዋ ደብረብርሃን አፍንጫ ሥር፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ አፋርን አካልሎ ደጋግሞ የወረረ፣ የዘረፈ፣ መነኩሴ የደፈረ፣ ንጹሐንን የጨፈጨፈና ንብረት ያወደመ፣ እንስሳት ሳይቀር የረሸነ፣ … [Read more...] about እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ!
ይቅርታ ያደረገን ሕዝብ ማታለል አይገባም
ተሃድሶ ጥሩና መጥፎ ጎኖች አሉት። በተለይ ሥርነቀል አቢዮት በተለመደባት አገራችን ተሃድሶ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ያንን መዘርዘር ግን አሁን አስፈላጊ አይደለም። የዚህ ርዕሰ አንቀጽ ዓላማ በተሃድሶ ምክንያት እየደረሰ ያለውና መረን የለቀቀ ተግባር እርምጃ እንዲወሰድበት ለመጠቆም ነው። ትህነግ ያላሰበውን ሥልጣን ተቆጣጦሮ አዲስ አበባ ሲገባና ካድሬዎቹ የዲዛይነር ልብስ መልበስ ሲጀምሩ የተበላሸው ጭንቅላታቸው ያው በበረሃው እሳቤ ነበር የቀጠለው። ከዓመታት በኋላ የድርጅቱን መበስበስ እንደማያውቅ ሆኖ ያስደነቀው ሊቀጳጳስ መለስ ዜናዊ “እስከ እንጥላችን ገምተናል” ነበር ያለው። የዘራውን እንደሚያጭድ አለማሰቡ ዕውቀት ጸዴ በረኸኛ መሆኑን በራሱ አስመስክሮበታል። ያገኙትን ሁሉ መዝረፍ ሙያቸው አድርገው የተካኑት ትህነጋውያንና ኢህአዴጋውያን ሊቀ ደናቁርት ካድሬዎች በለውጥ ስም ልክ … [Read more...] about ይቅርታ ያደረገን ሕዝብ ማታለል አይገባም
ጥቅምት 24 “የክህደት ቀን” ተብሎ በግንቦት 20 መቃብር ላይ ይተከልልን!
በራሳቸው ሕዝብ ላይ ሲደርስ ሰማይ የሚደፋባቸውና ዓለም ሁሉ አብሯቸው እንዲያለቅስ የሚፈልጉት ምዕራባውያን በሌሎች ላይ ለሚደርሰው ሰቆቃ ቅንጣት ታህል ግድ አይላቸውም። አንድ ማሳያ እንጥቀስ፤ የዛሬ 80 ዓመት አካባቢ ጃፓን የአሜሪካንን ድንበር ጥሳ ከሐዋይ ደሴቶች አንደኛዋ ላይ የሚገኘውን ወታደራዊውን የፐርል ወደብ ገና በጠዋቱ በድንገት አጠቃች፤ በወደቡ ላይ የነበሩት 8 መርከቦች ጉዳት ደረሰባቸው፤ አራቱ ሰጠሙ፤ በአጠቃላይ ወደ 20 የሚደርሱ መርከቦችና ጀልባዎች ከጥቅም ውጪ ሆኑ፤ ከ300 በላይ የሚሆኑ አውሮፕላኖች፣ ጀቶችና ሔሊኮፕተሮች ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፤ ከሁሉ በላይ ከ2,400 በላይ የሚሆኑ ባሕረኞች፣ ወታደሮችና ሰላማዊ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆሰሉ። በቀጣዩ ቀን ዲሴምበር 8፣ 1941 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት … [Read more...] about ጥቅምት 24 “የክህደት ቀን” ተብሎ በግንቦት 20 መቃብር ላይ ይተከልልን!
“ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ
ቴዲ አፍሮን የሚወዱት ሰዎች እጅግ በርካታ የመሆናቸውን ያህል ጥቂት የማይባሉ ደግሞ አምርረው ይጠሉታል። ደጋፊዎቹ በተለይ በዘመነ ትህነግ በድፍረት የሚያዜማቸውን እያነሱ “የአንድ ሰው ሠራዊት” ይሉታል። የሚጠሉት ደግሞ ቴዲ “ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?” ቢል እንኳን “ይሄ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ፣ …” በማለት የስድብ ናዳ ያወርዱበታል። ቴዲ በትህነግ ዘመን ግልጽ ግፎች ደርሰውበታል። የሙዚቃ ኮንሰርቶቹ ያለ ምንም ካሣና ቅድመ ማስታወቂያ ቲኬት ከተሸጠ በኋላ በተደጋጋሚ ተሰርዘውበታል። የጎዳና ተዳዳሪ ገድለሃል በሚል ክስ ለእስር በተዳረገበት ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበ ቁጥር ያለማቋረጥ እያለቀሰ ንጹሕ መሆኑን ለማሳመን ሞክሯል። ከእስር የተለቀቀበት አግባብም በራሱ ብዙ ሊያስብል የሚችል ነው። በአገራችን የለውጥ መዓበል በተነሳበት ወቅት ጃዋርን ጨምሮ አክራሪና ጽንፈኛ ኦሮሞዎች … [Read more...] about “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ
የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ብሎ በመጥራት ለበርካታ ዓመታት አገራችንን ሲያሸብር የኖረው እና በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት በአሸባሪነት የተዘመገበው፤ በቅርቡም በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተመዘገበውን ትህነግ “አሸባሪ” ብሎ ለመጥራት ሲጨንቃቸው የሚታዩ የአገር ውስጥና የውጪ (እንደ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ጀርመን ድምፅ) ሚዲያ ተቋማት መኖራቸው በግልጽ እየታየ የመጣ ክስተት ሆኗል። በቅርቡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀም የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንን አለማከበር ነው” ካለ በኋላ “እነዚህን ስያሜዎች በሚጠቀሙ ሚዲያዎች ላይ ባለስልጣኑ ፈቃድ እስከመሰረዝ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል። በአገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን ሕግ እና … [Read more...] about የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ምርጫ በዝረራ ማሸነፍ
በኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዷል። ተቃዋሚ ወይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ተሳትፈዋል። የምርጫው ሒደት ባብዛኛው ከተጽዕኖ የራቀ ነው ሊባል ይችላል። ተቃዋሚዎች በቂ የአየር ጊዜ ተሰጥቷው ፕሮግራማቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ ተደርገዋል። በርካታ ክርክሮች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ተካሂዷል። ለገዢው ፓርቲ እንደ በፊቱ ጊዜያት ፕሮፓጋንዳውን እንዲያሰራጭ እጥፍ ጊዜ አልተሰጠውም። ከተቃዋሚዎቹ እኩል በሚባል መልኩ ሃሳቡን እንዲያቀርብ ነው የተደረገው። ከሁሉ በላይ በደኅንነቱ መሥሪያ በጀት ተበጅቶለት ኮሮጆ ለመገልበጥ የሚሠራ ኃይል የለም። ምርጫ ቦርድም ነጻና ተዓማኒነቱን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። በምርጫው ቀን መራጩ ሕዝብ ነጸ በሚባል መልኩ ሲመርጥ ውሏል። በተለይ በከተሞች አካባቢ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚያስብል ተግባር እንዳልተፈጸመ ታይቷል። … [Read more...] about ምርጫ በዝረራ ማሸነፍ










