የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ)ን ማንነት የማያውቅ አንድም በሟቾች ይሸቅጣል፤ በደማቸው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይጣጣራል፤ ወይም ያወቀ መስሎት ይለፈልፋል፣ ይዘልፋል፣ ይዘፍናል። ትህነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምህረት የማያውቅ እንደሆነ "ነጻ አወጣሃለው" ባለው ሕዝብ ላይ ለዓመታት የፈጸመውን መመልከት በቂ ነበር። ስለምንረሳና እንደምረሳ ስለሚያውቅ ገድሎ ሙሾ አውራጅ ሆኖ ይመጣል። ጨፍጭፎን ስለ ሰላም ልደራደር ይላል። በወለጋ የተከሰተውንና መቼም የማይረሳውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በትህነግ ልክ ያለ አካል እና እርሱ አቡክቶ ጋግሮ የሠራው ኦነህ ሸኔ ካልሆነ ማንም ሊያደርገው እንደማይችል መገመት የማይችል ገና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልገባው የፖለቲካ ሕጻን ነውና አርፎ ተቀምጦ ይማር። ሌሎች ግን አሉ አዛኝ መስለው አጀንዳ የሚፈጽሙ። ባደባባይ ከሰቆቃው ሰለባ በላይ … [Read more...] about “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ
rapist tplf
ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ትህነግ ለሌላ አውዳሚ ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀይል እየመለመለ መሆኑን አንድ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ አጋለጠ። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በሚገባ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበትም ገልጿል። በአሸባሪው ትህነግ ጠብ አጫሪነት በተቀሰቀሰው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ጉብኝት ያደረገው "የስኩፕ ኢንዲፔንደንት ዜና" ዋና ኤዲተር አላስቴየር ቶምሶን፤ የአሸባሪው ትህነግ ዋነኛ ፍላጎት ዳግም ጦርነት መቀስቀስ መሆኑን ከኢዜአ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል። የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደም በርካቶችን በጦርነት በመማገድ ለሞት መዳረጉን አስታውሶ፤ ቡድኑ አሁንም ተመሳሳይ ተግባር ለመድገም እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ነው የተናገረው። ለዚህ ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተዋጊዎች እየመለመለና እያሰለጠነ መሆኑን በአስረጂነት … [Read more...] about ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ዘላቂ ወዳጅ የሌላት አሜሪካ ፊቷን በትህነግ ላይ እያዞረች ነው
ትህነግ ብዙ ወጪ ያደረገበት የሎቢ ሥራ ኪሣራ እየገጠመው ነው አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለስ ፍንጭ አሳየች የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሜሪካ የንግድ ልዑክ የተነሱበትን ቅሬታዎች በተመለከተ ተጨማሪ “አዎንታዊና ገንቢ” ዕርምጃዎችን የሚወስድ ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ከተጠቃሚነት የተሰረዘችበትን የአሜሪካ መንግሥት ከቀረጥ ነፃ የንግድ ዕድል (አጎአ) በተመለከተ የንግግር ሒደት ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጋዜጠኞች ጋር በስልክ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ ኢትዮጵያ ከአውሮፓውያኑ ጥር ወር 2022 ጀምሮ ከአጎአ ተጠቃሚነት የታገደችው የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ከሰብዓዊ መብትና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቷ መሆኑን መናገራቸውን ኋይት ሀውስ … [Read more...] about ዘላቂ ወዳጅ የሌላት አሜሪካ ፊቷን በትህነግ ላይ እያዞረች ነው
የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን (Diaspora Cyber Team) ትላንት (Sep 5) ስብሰባ ነበራቸው።የእኛ ሰዎችም የሳይበር ውይይታቸውን ሰብረው በመግባት ታድመው ወጥተዋል። አጀንዳዎቹ:- 1- አለም አቀፍ ጫናዎችን በድጋሜ በአዲስ መልክ እንዴት እንፍጠር? 2- ትግራይ ውስጥ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው። ለዚህስ መፍትሄው ምንድነው? 3- ህወሓት/የትግራይ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የሚሉ ናቸው። የተስማሙባቸው ነጥቦች:- 1ኛ) ጦርነቱ ትግራይ መሬት ላይ በነበረበት ወቅት ተዘረፍን ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ በጅምላ ተገደልን ... ብለን የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና እንዲፈጥሩ አድርገናል። አሁን ያንን መንገድ መከተል አዋጭ ስላልሆነ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እየተጎዳና እየሞተ እንደሆነ ፣ ወደ ትግራይ እየገባ ያለው የእርዳታ እህልም እጅግ … [Read more...] about የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ብሎ በመጥራት ለበርካታ ዓመታት አገራችንን ሲያሸብር የኖረው እና በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት በአሸባሪነት የተዘመገበው፤ በቅርቡም በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተመዘገበውን ትህነግ “አሸባሪ” ብሎ ለመጥራት ሲጨንቃቸው የሚታዩ የአገር ውስጥና የውጪ (እንደ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ጀርመን ድምፅ) ሚዲያ ተቋማት መኖራቸው በግልጽ እየታየ የመጣ ክስተት ሆኗል። በቅርቡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀም የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንን አለማከበር ነው” ካለ በኋላ “እነዚህን ስያሜዎች በሚጠቀሙ ሚዲያዎች ላይ ባለስልጣኑ ፈቃድ እስከመሰረዝ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል። በአገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን ሕግ እና … [Read more...] about የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ከ 170 በላይ ሴት የጁንታው አባላት በራሱ የጁንታው ታጣቂዎች ተደፍረዋል
በማይካድራ ንጹሃንን ጨፍጭፎ የሸሸው የአሸባሪው የህወሓት ወንጀለኛ ታጣቂ ቡድን በሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሴቶችን መድፈሩን በመከላከያ ሰራዊት የተማረኩት የህክምና ባለሙያና ወታደራዊ አመራር የሆኑት ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ማጋለጣቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። በሱዳን የስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙ ከ170 በላይ የሚሆኑት የጁንታው አባላት ሴቶች ላልተፈለገ እርግዝናና ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጣቸውንም ምረኮኛው ገልጸዋል። ወንጀል ፈፅመው ወደ ሱዳን የሸሹ የትህነግ ታጣቂዎች በስደተኞቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈፀሙና በዚህም ያልተፈለገ እርግዝናና የአባላዘር በሽታዎች መስፋፋታቸውን ሲታዘቡ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ተክለወይኒ ታረቀ ሻምበል ተክለወይኒ ታረቀ ትውልዳቸውና ዕድገታቸው በሰሜን ምስራቅ ትግራይ ታህታይ አዲያቦ በባድመ አካባቢ ሲሆን ከሰራዊቱ … [Read more...] about ከ 170 በላይ ሴት የጁንታው አባላት በራሱ የጁንታው ታጣቂዎች ተደፍረዋል