• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ

June 28, 2022 01:07 pm by Editor Leave a Comment

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ)ን ማንነት የማያውቅ አንድም በሟቾች ይሸቅጣል፤ በደማቸው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይጣጣራል፤ ወይም ያወቀ መስሎት ይለፈልፋል፣ ይዘልፋል፣ ይዘፍናል።

ትህነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምህረት የማያውቅ እንደሆነ “ነጻ አወጣሃለው” ባለው ሕዝብ ላይ ለዓመታት የፈጸመውን መመልከት በቂ ነበር። ስለምንረሳና እንደምረሳ ስለሚያውቅ ገድሎ ሙሾ አውራጅ ሆኖ ይመጣል። ጨፍጭፎን ስለ ሰላም ልደራደር ይላል።

በወለጋ የተከሰተውንና መቼም የማይረሳውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በትህነግ ልክ ያለ አካል እና እርሱ አቡክቶ ጋግሮ የሠራው ኦነህ ሸኔ ካልሆነ ማንም ሊያደርገው እንደማይችል መገመት የማይችል ገና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልገባው የፖለቲካ ሕጻን ነውና አርፎ ተቀምጦ ይማር። ሌሎች ግን አሉ አዛኝ መስለው አጀንዳ የሚፈጽሙ። ባደባባይ ከሰቆቃው ሰለባ በላይ ያለቅሳሉ፤ ከዚያ መልስ “አባላናቸው” እያሉ ከጣሪያ በላይ ይስቁብናል፣ በጅልነታችን ይሳለቁብናል።

እጅግ ልብ የሚሰብረውን የአቶ መሐመድን ሰቆቃ አል-ዐይን አስነብቦናል፤ ለታሪክ እናሰቀምጠው።

አቶ መሀመድ የሱፍ ሙሄ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ ዕድሜያቸውን በትክክል እንደማያውቁት ይናገራሉ፡፡ 

የቶሌ ቀበሌ ነዋሪው አቶ መሐመድ 22 ቤተሰብ በአንድ ቀን እንደተገደለባቸው ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ከተገደሉባቸው ቤተሰቦቻቸው መካከል ከወለደች አራት ቀን የሆናት እመጫት ልጃቸው አንዷ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

አቶ መሐመድ የሱፍ የአራት ቀን እመጫት ልጃቸው ከእነ ልጇ በጥይት መገደሏን ያነሱ ሲሆን፤ ገዳዮቹ ህጻኗን እንኳን አለመተዋቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡ 

አቶ መሐመድ ልጆቻቸው ከነልጅ ልጆቻቸው መገደላቸውን የገለጹ ሲሆን የመጀመሪያና ሶስተኛ ልጆቻቸው እስከ ልጅ ልጆቻቸው አምስት፤ አምስት ሆነው መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡ 

ሁለተኛዋ ልጃቸው ከሶስት ልጆቿ ጋር፤ እመጫቷ ልጃቸው ከሁለት ልጆቿ ጋር፤ ሌላኛዋ ልጃቸው ከአንድ ልጇ ጋር እንደተገደሉባቸው አቶ መሐመድ ለአል ዐይን አማርኛ በስልክ ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ የተዳረችው የአቶ መሐመድ ልጅ እንዲሁም አንድ ወንድ ልጅም እንደተገደሉባቸው ነው የገለጹት፡፡

አቶ መሐመድ በአጠቃላይ ስድስት ልጆቻቸው እና 16 የልጅ ልጆቻቸው መገደላቸውን የገለጹ ሲሆን የቀበሯቸውም እራሳቸው እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ አዛውንቱ እናታቸውም አባታቸውም የተገደሉባቸውን ሰባት ልጆች ይዘው እዛው ቶሌ ቀበሌ መቀመጣቸውንና መሸሽ አለመቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ 

አቶ መሐመድ በታጣቂዎች እንደተገደሉባቸው የጠቀሷቸውን ሁሉንም እራሳቸው እንደቀበሩ ገልጸዋል፡፡ ሃዘንተኛው አዛውንት የራሳቸውን ቤተሰቦችን ጨምሮ በአጠቃላይ 60 ሰዎችን መቅበራቸውን ይናገራሉ፡፡ 

“የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች የቀበርኩት እኔ ነኝ፤ በእኔ እጅ ነው የተቀበሩት ማንም አልቀበረልኝም፤ እኔ እራሴ ነኝ የቀበርኳቸው” ሲሉም ይናገራሉ አቶ መሐመድ፡፡ ከሟቾች ባለፈም የቆሰሉ ስድስት ልጆች እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ አንደኛዋ ልጃቸው አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደሄደች ገልጸዋል፡፡ አዲስ አበባ የሄደችው ልጃቸውእግሯ ይቆረጥ አይቆረጥ እየተባለ እንደሆነ ያነሱት አዛውንቱ የሟቾችን ስም ዝርዝር መናገር እንደሚችሉም ነው የገለጹት፡፡ 

የአቶ መሐመድ የሱፍ ሙሄ 22 የቤተሰብ አባላትን ካሳጣቸው ግድያ የተረፉት በቆሎ ማሳ ውስጥ ገብተው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እርሳቸው በቆሎ ማሳ ውስጥ ገብተው የተደበቁት ገዳዮቹ ሴት እና ልጅ “አይገድሉም” በሚል ግምት እንደሆነ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል፡፡

የአቶ መሐመድ የሱፍ ሙሄ ጓደኛዬ መሐመድ አሊ በበኩላቸው የልጃቸው ሚስት ከነልጇ እንደተገደለች ያነሱ ሲሆን ጓደኛቸው አቶ መሐመድ የሱፍ ግን 22 ቤተሰቦቻቸውን ማጣታቸውን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ጥቃት አድራሾቹን ያውቋቸው እንደሆነ የጠየቅናቸው አቶ መሐመድ ከግድያው በፊት ወደ ደምቢዶሎ በቶሌ ቀበሌ ማለፋቸውንና ምግብም ጠይቀው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጥቃቱ ሲፈጸም ወንዶች በብዛት ወደ ስራ ሄደው እንደነበርአቶ መሀመድ ገልጸዋል፡፡ 

አሁን ላይ እናታቸውና አባታቸው የተገደሉባቸውን ሰባትት ፤ አባታቸው የተገደለባቸው አምስት በድምሩ 12 የልጅ ልጆች ይዘው ግራ በመጋባት መቀመጣቸውን የገለጹት አቶ መሐመድ የፌዴራልም የክልል ባለስልጣናት መጥተው እንዳልጠየቋቸው ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቶሌ ቀበሌ በተፈጸመ ጭፍጨፋ የሟቾች ቁጥር 2 ሺ እንደሚደርስ አቶ መሐመድ ገልጸዋል፡፡ 

በምዕራብ ወለጋው ግድያ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ለኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም ማግኘት ባለመቻላችን ሃሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ 

የፈዴራል መንግስት ግድያ በተደረገበት አካባቢ የሕግ ማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች “አሸባሪዎችን ለማጥፋት በጋራ እንሠራለን” ብለዋል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Right Column Tagged With: ethiopian terrorists, olf shanee, olf shine, operation dismantle tplf, rapist tplf, tplf terrorist, wollega

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule