• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል

March 25, 2026 01:04 pm by Editor Leave a Comment

“ትዕይንተ ሕዝብ አዘጋጅ ግብረ-ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” በሚል ልደቱና ነዓምን በሻዕቢያ ምሪት በመሠረቱት ቡድን ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መሪ ጃልመሮ በአማካሪው በኩል ጃዋር መሀመድን እንደተካ ልደቱ አረጋገጠ።

ይህ ይፋ ይሆነው ከሦስት ቀን በፊት በተደረገው የቡድኑ ስብሰባ ላይ “ጃዋር ስብሰባ የማይገኝበት ምክንያት ምንድን ነው፧” በሚል ከተሰብሳቢዎች ለቀረበ ጥያቄ ልደቱ መልስ ሲሰጥ ነው።

ብረት ያነሳውና አሸባሪው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በስብሰቡ ውስጥ እንዲገባ የተወሰነበትን ውሳኔ ልደቱ በስብሰባው ይፋ አላደረገም። ልደቱ ባያብራራም ውሳኔው ግን ነዓምንና ጃዋር በሻዕቢያና እንደ ግብፅ ያሉ ሌሎች የውጭ ኃይሎች ምሪት እያደራጁት ያለው ስብሰብ ውሳኔ መሆኑ ታውቋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ ግን የጃልመሮ ሠራዊትና ድርጅት በከፍተኛ ደረጃ ክስ ቀርቦበት ነበር። “አብረን መቅመጥ አንችልም” በማለት የተቃወሙ ነበሩ። ሰላማዊ ትግል ወይም ሕዝባዊ እምቢተኛነት በሚል የተሰበሰበ ቡድን ውስጥ የጃልመሮ ዓይነት ቡድን መግባቱ ማነው ይህንን ስብስብ እየመራ ያለው ከሚለው ጀምሮ ብዙ ጥያቄ ጭሯል።

በስብሰባው የተሳተፉ ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ዲሲ ተባባሪ እንዳስታወቁት፣ ጃዋርን ተክቶ የገባው ጅሬኛ ጉደታ በተከታታይ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃትና ዘግናኝ ተግባር እየፈጸመ ነው በሚል የሚከሰሰውና በቅርቡ አምነስቲ አስደንጋጭ ሪፖርት ያወጣበት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል ሆኖ ሳለ እዚህ ስብሰብ ውስጥ መግባቱ አነጋግሯል። ጃዋርን መተካቱ ደግሞ ጃዋር ከጃል መሮ ጋር አብሮ እየሠራ ነው የሚለውን ሃሜት ያጸና ሆኗል ብለዋል።

ጅሬኛ ጉደታ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (OLA) ቃል አቀባይ እና ከፍተኛ አማካሪ ነው። ጅሬኛ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን ታጣቂዎች በተመለከተ በተለያዩ ወቅቶች ማናቸውንም መግለጫዎችን በመስጠት የሚታወቅ ግለሰብ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎችን የሚወክለው ጅሬኛ ጉደታ፤ የኩምሳ ድሪባ ወይም ጃል መሮ አማካሪመ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እምቢተኛነት ወይም ዓመፅ ለማስነሳት በተደራጀው ቡድን ውስጥ ጃዋርን ወክሎ በመግባት ከእነ ልደቱ ጋር “የሰላማዊ ትግል አመቻች” እንዲሆን ተደርጓል።

ልደቱ በተደጋጋሚ “ሰላማዊ ትግል ብቻ” ቢልም አሁን አሁን እየወጣበት ያለው መረጃ እርሱ ከሚናገርው ጋር የሚቃረን ሆኗል። በቅርቡ “ትዕይንተ ሕዝብ አዘጋጅ ግብረ፡ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” ይፋ ባደረገው የጥምር ቡኖች ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በመናበብ እንዲሠራ፣ ለታጣቂ ኃይሎች የአብረን እንሥራ ጥሪ መደረጉን፣ የትጥቅ ትግሉንና ሰላማዊ የሚባለውን ዓመፅ አብሮ ለማስኬድ ዕቅድ ስለማውጣትና ዓመፅ ሲካሄድ ታጣቂ ኃይሎች እንዴት ዓመፁን እንደሚያግዙ ለመምከር በተያዘው ዕቅድ ልደቱ አያሌው ስሙ ቀዳሚ እንደሆነ ተመልክቷል። ልደቱ በፊት ከሚኖርበት አትላንታ ወደ ዋሽንግቶን ዲሲ የተዘዋወረው በነዓምን ዘለቀ በኩል የኑሮ ክፍያ ተደርጎለት እንደሆነ አብረውት የሚሠሩ ይናገራሉ።

አብዛኛውን ጊዜውን በሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ከያሬድ ጋር በአንድ ካፌ የሚያሳልፈው ልደቱ እንዴት ወደ ዲሲ አካባቢ ሊመጣ እንደቻለ ከነገረው ባልደረባው የሰሙ እንዳሉት፣ ክፍያ በነዓምን በኩል ስለሚፈጸምለት ደስተኛ እንዳልሆነም እንዳስታወቀ ነው። ልደቱ ምክንያቱን በግልጽ ባይናገርም ነዓምን ለሻዕቢያ ስለሚሠራ ከዚያ ጋር ይያያዝብኛል ከሚል እንደሆነ ይገመታል።

በተያያዘ የአብሮነት እና ከስምንት የተለያዩ ማህበራትና ሻዕቢያ እንዳደራጃቸው ከሚታወቁ ቡድን መሪዎች እሁድ ለሰኞ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ሌሊት አካባቢ በጋራ እንደሚመክሩ በተነገረው መሠረት ስብሰባውን አካሂደዋል።

በስብሰባው እንዲካፈሉ የተጋበዙ እንዳሉት የስብሰባው ዋና ዓላማ በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ለማካሄድ በታሰበው ስብሰባ ላይ እንዴት በጥምረት እንደሚሠራ ለመምከርና ዕቅድ ለማውጣት፣ በሀገር ቤት ዓመፅ የሚነሳበትን አግባብ አስመልክቶ እንዴት በጋራ መሥራት እንደሚገባ ለመምከር ነበር።

እንደ ታማኝ በየነና አንዳርጋቸው ጽጌ ዓይነቶች በይፋ ቅስቀሳውን እንዲቀላቀሉ በዚህ ስብሰባ ላይ መመሪያ እንደሚሰጥ አጀንዳውን የሰሙ አመልክተዋል የነበረ ቢሆንም ስብሰባው በታቀደው መሠረት ስምምነት ላይ ሳይደረስ ተጠናቅቋል። ሆኖም ለዛሬ ረቡዕ በተጠራው ስብሰባ ምርጫውን ሕገወጥ ለማድረግ ሁሉም እንዴት ተባብረውና ተናብበው እንደሚሠሩ አንድ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ በነዓምን በኩል የተሰጠው የውስጥ መመሪያ ያመለክታል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: lidetu ayalew, Neamin, olf shanee, Shene, wolaitta

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule