ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ምንም ጊዜ የማይቀየር፣ ሊስተባበል የማይችልና ልዩ የሆነ መለያ አላቸው። ይህም ለክህደትና ለመሸጥ፣ በኢትዮጵያውያን አገላለጽ ለባንዳነት የተጋለጡ ወይም መደምደሚያቸው ባንዳነት ነው። ሌሎቹን እንተዋቸውና በአገራችን ዋና ምስክር የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግን) ማንሳት ይበቃል። ጥሩም መከራከሪያ የሚቀርብበት የዘመኑ አፍላ ታሪክ ነው። ቃለ ምልልሱ ከተካሄደ ቆይቷል። ሰሞኑን ግን የሩሲያ መንግሥት ቲቪ በድጋሚ ሲያሳየው ነበር። ጋዜጠኛው ቭላዲሚር ፑቲንን ይጠይቃል። ይህን የቆየ ቃለ መጠይቅ ማስተላለፍ የተፈለገው በቀድሞ ወጥ ቀቃይ የሚመራውና አሁን ቫግነር የተባለው ኢመደበኛ አደረጃጀት ከሩስያ መከላከያ ጋር የገባበትን መፈታተን ተከትሎ ነው። ጥያቄ - ይቅርታ ታደርጋለህ?ፑቲን - አዎ፤ ግን ለሁሉም አይደለም፤ጥያቄ - ይቅር ለማለት የማይቻለው … [Read more...] about ኢመደበኛነት – አገር አፍራሽ የዘመኑ ባንዳነት
wolaitta
የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮች ፍርድ ቤት ውሎ
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን ጨምሮ ለ20 ተጠርጣሪዎች የእስር ፍርድ ቤት በፈቀደው ዋስትና ላይ እና ፖሊስ በጠየቀው የምርመራ ቀናት ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 27/2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ዛሬ በነበረው ችሎት በዋስትናው ጉዳይ እና ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጹሁፍ ያቀረበውን የመልስ መልስ ተቀብሏል። ዛሬ በነበረው ችሎት ማናቸውም ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን የ6ቱ ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ተናግረዋል። በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ከተደረጉ 15 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አስራ 2ቱ በዛሬው ችሎት የተወከሉት፤ በ3 ጠበቆች መሆኑንም ገልጸዋል። ቀሪዎቹ 3 ተጠርጣሪዎች በራሳቸው የሚከራከሩ ናቸው ብለዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ማክሰኞ በነበረው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ … [Read more...] about የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮች ፍርድ ቤት ውሎ
የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች በወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ፤ ለተጠርጣሪዎች ተፈቅዶ በነበረው ዋስትና ላይ ፖሊስ የመልስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ለመጪው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 19 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የተጠርጣሪዎችን አቆያየት በተመለከተ በትላንትናው ዕለት ከሰዓት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም በጠዋት ችሎት ቀርበው የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች አልተገኙም በሚል ብይኑን ለዛሬ ማሳደሩን ጠበቃው ገልጸዋል። እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሲጠብቁ የቆዩ ሰባት ተጠርጣሪዎችም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሐዋሳ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ … [Read more...] about የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ