በወንጀል ተከስሰው በእስር ቤት የሚገኙት ጃዋር ሲራጅ መሐመድ፣ በቀለ ገርባ ዳኮ፣ ሐምዛ አዳነ ታዬ እና ሸምሰዲን ጠሃ መሐመድ ከሰኞ መስከረም 25 ቀን ጀምሮ በሚመሠረተው የአደራ መንግሥት ለመሳተፍ ከእስር እንለቀቅ ብለው ተማጽንዖ አቅርበዋል። ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ልቅም ባለ አማርኛ ከሽነው በጻፉት ደብዳቤ መንግሥታዊ አካል ለሆነው “የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች” ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ በግልባጭ “ለፌዴራል ዐቃቤ ሕግ” እና “ለፌዴራል ወንጀል ምርመራ” ጥያቄያቸውን ልከዋል። ተከሳሾቹ መቀሌ ከመሸገው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድብ ህወሓት እና ከሌሎች ራሳቸውን ተቃዋሚ ፓርቲ ብለው ከሚጠሩ ጋር በመሆን ከመስከረም 25 ጀምሮ የአደራ መንግሥት እንመሠርታለን ብለው በተደጋጋሚ ሲናገሩና ሲሠሩ እንደነበር ይታወቃል። ተከሳሾቹ ያቀረቡት ደብዳቤ ከዚህ በታች ይገኛል፤ ጎልጉል የድረገጽ … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነጃዋር “መንግሥት የለም” ብለው የመንግሥት አካል ነጻ እንዲያወጣቸው ተማጸኑ
chilot
የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮች ፍርድ ቤት ውሎ
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን ጨምሮ ለ20 ተጠርጣሪዎች የእስር ፍርድ ቤት በፈቀደው ዋስትና ላይ እና ፖሊስ በጠየቀው የምርመራ ቀናት ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 27/2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ዛሬ በነበረው ችሎት በዋስትናው ጉዳይ እና ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጹሁፍ ያቀረበውን የመልስ መልስ ተቀብሏል። ዛሬ በነበረው ችሎት ማናቸውም ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን የ6ቱ ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ተናግረዋል። በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ከተደረጉ 15 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አስራ 2ቱ በዛሬው ችሎት የተወከሉት፤ በ3 ጠበቆች መሆኑንም ገልጸዋል። ቀሪዎቹ 3 ተጠርጣሪዎች በራሳቸው የሚከራከሩ ናቸው ብለዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ማክሰኞ በነበረው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ … [Read more...] about የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮች ፍርድ ቤት ውሎ
160 ሰዎች የሞቱበት፣ 360 ሰዎች የተጎዱበት፣ ከ4.6 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት የወደመበት የነጃዋር ክስ የወንጀል እንጂ የፖለቲካ እንዳልሆነ ተጠቆመ
ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለውና ክስ ተመሥርቶባቸው የሚገኙ ግለሰቦች ፖለቲከኞች ቢሆኑም፣ የታሰሩት በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው አለመሆኑን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ሚዲያ ኃላፊዋ ቢልለኔ ሥዩም ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት፣ የጉዳዮች መገናኘት ካልሆነ በስተቀር፣ የታሰሩ ግለሰቦች ፖለቲከኞች ቢሆኑም ከፖለቲካ አመለካከትቸና እንቅስቃሴያቸው የታሰሩ እንዳልሆነ አብራርተዋል። ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ገላን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጥይት ተመትቶ የተገደለው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ተከትሎ፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ከተከሰቱ አመፆችና … [Read more...] about 160 ሰዎች የሞቱበት፣ 360 ሰዎች የተጎዱበት፣ ከ4.6 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት የወደመበት የነጃዋር ክስ የወንጀል እንጂ የፖለቲካ እንዳልሆነ ተጠቆመ
ለተከሳሽ ጃዋርና ግብረአበሮቹ “ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው” የሚል ምላሽ ተሰጠ
ባለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. አሥር የተለያዩ ክሶች የተመሠረተባቸው አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 24 ተከሳሾች ክሱ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 ድንጋጌ መሠረት የተሰጣቸው ቢሆንም፣ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 129 ድንጋጌ መሠረት ክሱ ለተከሳሾቹ በችሎት መነበብ ስላለበት፣ በችሎት ለማንበብ ለመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጣቸው። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾን ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ያልቀረቡ ተከሳሾችን የፌዴራል ፖሊስ እንዲያቀርብና ክስ እንዲነበብላቸው የነበረ ቢሆንም ሳያቀርብ ቀርቷል። በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ 14ኛ ተከሳሽና በአሜሪካ አገር ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃነ መስቀል አበበና አውስትራሊያ እንደሚኖሩ የሚነገረው አቶ ፀጋዬ … [Read more...] about ለተከሳሽ ጃዋርና ግብረአበሮቹ “ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው” የሚል ምላሽ ተሰጠ
“በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት፣ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ እንዲሁም የፀና ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች አንዱ ጃዋር መሐመድ፣ እሱን ጨምሮ እስክንድር ነጋና ልደቱ አያሌው የተከሰሱት መንግሥት በምርጫ ያሸንፋሉ የሚል ሥጋት ስላለው እንጂ ወንጀል ፈጽመው አለመሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገረ። ጃዋር ይኼንን የተናገረው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 260215 መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የከፈተውን ክስ፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተከሳሾች ሲሰጣቸው ነው። በሽብርተኝነት ሲከሰስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ የመጀመርያው በኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥ የቀረበበት ክስ ሲሆን፣ ሁለተኛው አሁን የተከሰሰበት መሆኑን ጠቁሞ፣ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው … [Read more...] about “በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው ክስ የሕዝብ ሰላምንና የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል፣ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝና የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል በማለት የዋስትና መብታቸው እንዳይፈቀድላቸው መከራከሩን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡት እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ መንግሥት ወይም ዓቃቤ ሕግ ለሕዝብ ሰላምና ለአገር ደኅንነት የሚያስብ ከሆነ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው፣ በመጪው አገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉ መደረግ እንዳለበት ለፍርድ ቤት ተናገሩ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ዋስትና እንዲከበርላቸው የጠየቁት፣ የተመሠረተባቸውን ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብር ተግባራትና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ካነበበላቸው በኋላ፣ ስለመብት … [Read more...] about የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
በተደጋጋሚ የክስ ቻርጅ እንዳይሰጠው ጥረት ሲያደርግ የነበረው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከግብርአበሮቹ ጋር “ተከሳሽ” የሚለውን መጠሪያ ትላንት ሰኞ መስከረም 11/2013 ተቀብለዋል፤ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በይፋ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በጃዋር መሐመድ እና ሌሎች 23 ተከሳሾች ላይ ክሱን በመሠረተበት ወቅት፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት፤ በውሎው የክስ ሰነዶቹ ለተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲከፋፈል አድርጓል። በመሆኑም እነ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል። ዐቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ ላይ 10 ክሶችን … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
አቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን አርብ መስከረም 8፤ 2013ዓም ነበር። ሆኖም በዚህ ክስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቅበት የመጨረሻው ቀን ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረው ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት ጃዋርና ሲራጅ መሐመድና ግብረአበሮቹ በ10 ተደራራቢ ክሶች ፋይል እንደከፈተባቸውና የክስ ቻርጁም መስከረም 11፤2013ዓም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደሚደርሳቸው አስታውቋል። ዐቃቤ ሕግ ያወጣው ጽሁፍ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድ፤አቶ በቀለ ገርባ፤አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ … [Read more...] about ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ። ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ። “ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል። “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር … [Read more...] about እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በተከሰሱ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ጀመረ። በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በተከሰሱበት በአዋጅ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ሰዎችን በመያዝና በማሰር ስልጣንን ያለ አግባብ መገልግል ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ ማንነታቸው የማይገለፅ ምስክሮችን ዛሬ ማሰማት ጀምሯል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አጠቃላይ 22 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይ እና ሺሻይ ልኡል በሌሉበት ነው ጉዳያቸው የታየው። ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/ 2003 መሰረት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው እና ማንነታቸው የማይገለፅ 29 ምስክሮችን … [Read more...] about ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ