በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በተከሰሱ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ጀመረ።
በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በተከሰሱበት በአዋጅ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ሰዎችን በመያዝና በማሰር ስልጣንን ያለ አግባብ መገልግል ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ ማንነታቸው የማይገለፅ ምስክሮችን ዛሬ ማሰማት ጀምሯል።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አጠቃላይ 22 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይ እና ሺሻይ ልኡል በሌሉበት ነው ጉዳያቸው የታየው።
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/ 2003 መሰረት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው እና ማንነታቸው የማይገለፅ 29 ምስክሮችን ያዘጋጀ ሲሆን፥ በዛሬው እለት ሶስቱን አቅርቧል።
በዚህም አንድ ምስክር መሰማት ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ ሲሆን፥ በሚታየው የቪዲዮ ማስረጃ ጥራት ጉድለት ምክንያት ቀሪ ምስክሮቸን ከመጋረጃ ጀርባ ለመስማት ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ©ፋና
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
yuya Jemal says
PP- EPRADF #2. PP also part crimine against humanities during TPLF regime