አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ተፈተው አሜሪካ እስከገቡ፣ ከአሜሪካም ሜኖሶታ ከጃዋር ጋር ጫጉል ቆይተው እስኪወጡ የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን የሚያውቁ፣ የሚያመልኩትን አምላክ ተግሳጽ መስማት የሚችሉ፣ በዙሪያቸውም ሆነ በሩቅ ባሉ ክብር ያላቸው ፖለቲከኛ እንደነበሩ ስምምነት አለ። ይህ ስምምነት ነበር አቶ በቀለን በኢትዮጵያ ለውጥ ቢፈጠር ሁሉንም አቻችለው ወደ በጎ መንገድ እንዲመሩ ከሚታሰቡት መካከል ቀዳሚው አድርጓቸው የነበረው። የዲሲ ነዋሪው ገመቹ በቀለ ከሜኖሶታ "ተሃድሶ" ይለዋል ተመርቀው ሲወጡ "የአንጎል ቀዶ ጥገና ተድርጎላቸዋል" ባይ ነው። የዘወትር የጎልጉል አስተያየት ሰጪ ገመቹ እንዳብራራው አቶ በቀለ ጃዋር በዝግ ቤት ከሰው ለይቶ ቀዶ ጥገና ካደረጋቸው በኋላ ሙሉ በሙሉ ሌላ የማይታወቁ ሰው ሆኑ። "በቀለ ይፈታ" እያሉ ሲጮሁ የነበሩ ወገኖችን ከነ ባንዲራቸው … [Read more...] about የጃዋር ቅዠትና የበቀለ የተላላኪነት ፖለቲካ – የለማ ሃዲድ መሳት
getachew assefa
“ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ስዩም፣ አባይና አስመላሽ ተደመሰሱ፤ ደብረጽዮን 24 ሰዓት ተሰጥቶታል መከላከያ ሠራዊት ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ። ደብረጽዮን በ24 ሰዓት ውስጥ እጁን ካልሰጠ እንደሚደመሰስ ተነግሮታል። የመከላከያ ሠራዊት ሀይል ሥምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል። አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል። የህወሐት ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ … [Read more...] about “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ለትምህርት እንዲሆነን
ታላቁ መጽሐፍ የተጻፈበትን ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” ተጻፈ ይላል። በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ጊዜያት አሳልፈናል። በሥልጣን የተቀመጠ የሚወርድ እስከማይመስለውና ሰብዓዊነቱን እስኪዘነጋ ድረስ ሕዝብን ሲበድል ይኖራል። የሕይወቱ መጽሐፍ ሲጠናቀቅ ይሰናበታል። ስንብቱ ግን በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ሲሆን መመልከቱ በየዘመናቱ የመሰከርነው ሐቅ ነው። ንጉሡ በደርግ ሲተኩ፤ ደርግ “ለለውጥ ባጎፈረው” ህወሓት ሲተካ፤ አሁን ደግሞ አይደረስብንም፣ አንበገርም፣ እንደ ደርግ አንሆንም፣ ዓቅምም፣ ገንዘብም፣ ሁሉም ነገር አለን ሲል የነበረው በረኸኛው የወንበዴ ጥርቅም ከየጉድጓዱና ሰርጡ እንደ አውሬ … [Read more...] about ለትምህርት እንዲሆነን
“ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
አባይ ወልዱ እና አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል፤ አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበረ አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ ዕቁባይ በርሄ የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች ንጋቱ አንገሶም አምደማርያም ተሰማ እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ … [Read more...] about “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 4 የቡድኑ አባላት ደግሞ እርምጃም ተወስዶባቸዋል። የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ብሎ የገለፀውን የጁንታው አፈቀላጤ ጨምሮ 4 ከፍተኛ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ በርካቶች ሲደመሰሱ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህም መሰረት፣ ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) 1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ 2. ዘርአይ አስገዶም … [Read more...] about የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል። በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት … [Read more...] about ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል
ወንጀለኛው የህወሓት ጁንታ የንግድ ድርጅቶች በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳታቸውን ምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ አዲሱ እጥፉ አስታወቁ። የሀገሪቱን ሀብት ከመበዝበር ወደ ውጭ ለማሸሽ መሳሪያ እንደነበሩም ጠቆሙ። አቶ አዲሱ እጥፉ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገ ለጹት፦ የህወሓት ጁንታው የንግድ ድርጅቶች በሀገ ሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተፅዕኖ እጅግ የከበደ ነው።ተቋማቱ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት በመቆጣጠርና በህገወጥ መንገድ በመዝረፍ የአገሪቱን ሀብት ወደውጭ ሲያሸሹ ነበር። የንግድ ተቋማት አሰራራቸው ብቻ ሳይሆን አጀማ መራቸውም ህገ ወጥ እንደነበሩ የገለፁት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ላለፉት በርካታ ዓመታት በማናለብኝነት ሀገሪቱን ሲመዘብሩ መቆየታቸውና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አስታውቀዋል። ጁንታው … [Read more...] about ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል
“ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” በቢሊዮን የሚቆጠር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች አስመጪና አከፋፋይ!
አቶ ፍፁም አባዲ በኢትዮጵያ አየርመንገድ የካርጎ ክፍል ሃላፊ፣ ምክትሉ አቶ ናትናኤል ጎበና እና የጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆነው አቶ ዮሃንስ አረጋይ በአየርመንገዱ የካርጎ ክፍል የሚሰሩ “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲግ” ሰራተኞች ናቸው። በዱባይና ቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የጭነት ወኪሎች፣ የቦሌ ጉሙሩክ ሃላፊ ከነበረው ከአቶ ገብረማርያም እስከ ጥበቃ ክፍል ሰራተኞች የሚደርሰው ሰንሰለት የጌታቸው አሰፋ የኮንትሮባንድ ንግድ ሰንሰለት ነው። እነ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን የተወገዱበትን ሚስጥር፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በህወሓቶች ስለሚፈፀመው ዘረፋና የኮንትሮባንድ ንግድ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ይፋ ወጥቷል። “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” ከሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ800 ሚሊዮን ብር ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በአየርመንገድ በኩል ግብር ሆነ ታሪፍ … [Read more...] about “ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” በቢሊዮን የሚቆጠር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች አስመጪና አከፋፋይ!
ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በተከሰሱ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ጀመረ። በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በተከሰሱበት በአዋጅ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ሰዎችን በመያዝና በማሰር ስልጣንን ያለ አግባብ መገልግል ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ ማንነታቸው የማይገለፅ ምስክሮችን ዛሬ ማሰማት ጀምሯል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አጠቃላይ 22 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይ እና ሺሻይ ልኡል በሌሉበት ነው ጉዳያቸው የታየው። ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/ 2003 መሰረት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው እና ማንነታቸው የማይገለፅ 29 ምስክሮችን … [Read more...] about ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
የህወሓት ነባር ታጋይ የሆነው ጌታቸው አሰፋ የመረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመው 1993 ዓ.ም ላይ ነበር። ክንፈ ገ/መድህንን የተካው ጌታቸው አሰፋ ከቀደመው የመረጃና የደኅንነት ሰው ፍጹም የተለየ ባህሪ እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ። ከሸራተን ሆቴል ውጭ እምብዛም የማይዝናናው ጥንቁቁ የመረጃ ሰው ሲበዛ ተጠራጣሪና ደመቀዝቃዛ እንደሆነ ይነገርለታል። በኤምባሲዎች ራት ግብዣ ላይ እንኳን ለመገኘት ከኤምባሲ ኤምባሲ፣ ከአምባሳደርም አምባሳደር የሚያማርጠው የደህንነቱ ቁንጮ፣ በህይወት እያለ ምሽት ላይ ከቦሌ ወሎ ሰፈር ግሮሰሪዎች በአንዱ ከማይታጣው ክንፈ ገ/መድህን አኳያ የተለየ ባህርይ ብቻ ሳይሆን የረቀቀ የአፈና መዋቅር በአገር ውስጥም ሆነ በቀጠናው ላይ መዘርጋት የሚችል ሰው መሆኑ ከቀደመው የመረጃ ሰው እንደሚለየው ይነገርለታል። ሰውየው ራሱን እንደመንፈስ … [Read more...] about የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!