
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።


በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን ‘የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው’ ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት በሙሉ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የቴሌኮም እንዲሁም የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረታዊ አገልግሎቶች ከጥገና ሥራ በኋላ ተመልሰው እየቀጠሉ ነው ብለዋል።
በአካባቢው ለሕዝቡ የተጀመረው ሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀጥልና መንግስት በሕግ ማስከበሩ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በተለይም ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚሰሩ ስራዎች ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች
- ጠላት በርከት ያሉ የእኛን መኮንኖች ይዞ ስለቆየ እነሱን ይዞ ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ ስለሆነም ማታ ማታ በምናደርገው ኦፕሬሸን በርከት ያለ ሰው በሚኖርበት ሰአት ይህ ሀይል የእኛ ሃይል ሊሆን ይችላል በሚል ያቆየናቸው ሚሳየሎችና ቦንቦች ዛሬ ያኮሩኛል። ያንን ተጠቅመን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመካከላችን ያሉትን መኮንኖች አናያቸውም ነበር፤
- ይህ ኢትዮጵያን የመታደግ ኢትዮጵያን የማኩራት ብቃት፤ ተልዕኮን በአጭር ጊዜ የመፈጸም ብቃት የተቋማችን የሁልጊዜ አርማ መሆን አለበት፤
- በተደጋጋሚ እንዳልኩት የመከላከያ ሰራዊት የብልጽግና ሰራዊት አይደለም፤ የአብይ ሰራዊት አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መከታና ኩራት የሆነ ወታደር ነው፤
- እኛ የምንፈልገው ፕሮፌሽናል ጠንካራ አርሚ እንድትሆኑ እንጂ ለአንድ ፓርቲ የሚገዛ እንድትሆኑ አንፈልግም፤
- ኢትዮጵያ ከብልጽግናም ከፓርቲም በላይ ናት፤ ትልቋን አገር የመታደግ ሃላፊነት ተጥሎባችኋል፤
- ፖለቲካው የተበላሸ ነው፤ የማያውቀውን የደም ስር እና ሀረግ እየፈለገ የሚቧደን ነው፤ እናንተ ግን ጀግኖች ብቻ ሳትሆኑ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፤
- ጦርነቱን ስንጀምር በጣም ብዙ ሰዎች በአጠረ ጊዜም ብቻ ሳይሆን ማሸነፍም ይከብዳል የሚል ግምግማና ግምት ይናገሩ ነበር፤ ይሄ አልሆነም፤
- እኛን የሚዋጉን ሰዎች ዘመናዊ ጦርነት አያውቁም፤ የጦርነት ሳይንስ አያውቁም፤ የሚያውቁት የሽምቅ ውጊያ ነው፤ እሱ የሽፍቶች ውጊያ ነው፤ እሱ በሰው ሃይልና በተተኳሽ ቁጥር ማሸነፍ የምናረጋግጠብት ውጊያ ነው፤
- የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ስንት ሺህ ወጣት እንዳስከፈለን ስንት ጊዜ እንደወሰደ እናውቀዋልን፤ ይሄ የአሁኑ ኦፕሬሽን ደግሞ በምን ያህል ባነሰ የሰው ሃይልና መስዋዕትነት ለድል እንደበቃን ታውቃላችሁ፤
- ከሁመራ መቀሌ በእግር መጓዝ ማለት ብዙዎች አዲስ አባበ ሆነው ዝም ብሎ ጀግና እንደሚሉት አይደለም፤ በዚህ መልክዐ ምድር በዚህ ሙቀት ስንቅና ትጥቅ ተሸክሞ ይሄንን ያህል ጉዞ መጓዝ የማንም አገር ወታደር አይደግመውም፤
- ይሄንን ጀግንነት ወንጀለኞችን በመያዝ መድገም ያስፈልጋል፤ ወታደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ መቶ በመቶ አሳክቷል፤ የሚቀረው ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ነው እሱንም በፍጥነት ማከናወን ያስፈልጋል፤
- ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የትግራይ ህዝብ ሃላፊነት አለበት፤ የተደበቁትን ሰዎች፣ ከመኪና ወርደው እግረኛ የሆኑትን ሰዎች በመያዝ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለትግራይ አስተዳደር ማስረከብ አለበት፤ ያ ካልሆነ ወታደሩ አገር የመጠገን ጊዜውን ወንጀለኛ በማደን ስለሚያሳልፍ የሚጎዳው ራሱ ህዝቡ ነው፤
- ከኢትዮጵያ መንግስት ልማት ድጋፍ መጠየቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ወንጀለኞችን አሳልፈው መስጠት ደግሞ ግዴታ ነው፤ ይህ ስምምነት ካለ ነው ስራችንን በአጭር ጊዜ በማከናወን ወደልማት የምንገባው፤
- በርካታ ወንጀለኞችን እንደተያዙ፤ የተቀሩትም የት እንዳሉ መረጃው አለኝ፤
- የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ህዝቦች ኩራት መሆኑን፤ በዚህ ቀጣና የሚነሳ ማንኛውንም አደጋ በሚፈለገው ልክ ለመመከት የሚያስችል ብቃት ያለው ጦር መሆኑን በድጋሜ አረጋግጧል፤
- የጁንታው ሃይል በቁጥር ከ80 ሺህ በላይ ይገመታል፤ አዳዲስ መሳሪያዎችን ታጥቋል፤ ከፍተኛ የተተኳሽ ዲፖዎች ነበሩት፤ ኮማንዶ ሜካናይዝድ ሮኬት መተኮስ የሚችሉም ሰዎችነበሩት፤ እኛ ግን መቀሌ እስከገባንበት ቀን ድረስ ሮኬት አልተኮስንም በእኛና በጁንታው መካከል ያለው ልዩነት ይሄ ነው፤ እኛ ያልተኮስነው ህዝባችን እዚህ እንዳለ ስለምናውቅ ነው፤
- እኛ ሮኬት የተጠቀምነው ጁንታው መቀሌን ለቆ በረሀ ለበረሃ ለማምለጥ ሲሞክር ነው፤ ይሄ የእውነት ይሄ የፍትሃዊነት ልዩነታችን አሸናፊ አድርጎናል (ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
የምንም ነገር ታሪክ ተገልባጭ ነው። ያረጅና ይረሳል፤ የቆመለት ሃውልትም በአዲሱ ትውልድ ይወገዛል፤ አልፎ ተርፎም ተጎትቶ ትቢያ አመድ ይሆናል። ወያኔ ህዝቡን ሲያታልልበት የኖረው የፈጠራ ታሪክ ዘግይቶም ቢሆን የራሱ ማነቆ እንደሚሆንበት አልገባውም። ደብተራው፤ ቃልቻው፤ ሃሳዊ ነብዪና ገበሬው፤ የከተማና የገጠር ኑዋሬው አክ እንትፍ እንዳላቸው አላወቁም። ዘመናቸውን ሁሉ ተጨፈኑና እናሞያችሁ ሲሉ የኖሩት እነዚህ ከሃዲና ናዚዎች ይኸው ዛሬ የሮምን አወዳደቅ ወደቁ። የፓለቲከኞች መጠጊያ መሳሪያና ጉራ አይደለም። ህዝብ እንጂ። ወያኔ በህዝብ የተጠላ ጭራቅ ድርጅት ነው። በህዝባችን ላይ በ45 አመት አፈሙዝ አገዛዙ የፈጸመው በደል ስፍር ቁጥር የለውም። በቅርብ ከአይን ምስክር ወታደር በሁመራ ግንባር ከደረሰኝ እንሆ።
በተጠና መልኩ ሳናስበው በተኛንበት ተኩስ ተከፈተብን። ወጣ ብዬ መሳሪያን እንደያዝኩ ሳይ ለዋርድያ የተመደቡት ሰዎች ተኩሰው ሲገሏቸው አየሁ። እኔም ፈቀቅ ብዬ አንድ ስፍራ ፊት ለፊት ከቆመው ታንክ ጥግ በሆዴ መሳሪያየን እንደያዝኩ ተኛሁ። ከዚያ ወታደሩ እየተሯሯጠ ወደ መሳሪያ መካዝን ሲሄድ እየመቱ ጣሉት። አንድ ታንከኛ ቶሎ ብሎ ዘሎ ታንክ ውስጥ ሲገባ ሌላው መሳሪያ የያዘ የትግራይ ወታደር ከላይ ሆኖ ተኩሶ ሲመታው ታየኝ። ከዚሃ ሌላ የእኛ ታንከኛ የሆነ የትግራይ ልጅ አምጥተው ሁለቱ አስከሬኑን ከታንክ ሲያወጡ አየሁ፡፤ አወጡና ወረወሩት። እኔም መሳሪያን አቀባበልኩና ጠጋ ብየ ሁለቱን በሩምታ ገደልኳቸው። አላሰቡትም። ብዙ ተኩስ አለ። ከዚያም አፈግፍጌ ወደ ሱዳን ድንበር ተጠግቼ በህዋላ ከአማራ ሚሊሻ/ፋኖ/ልዪ ሃይል ጋር ጦሩን ተቀላቀልኩ አለኝ። ግፈኛው ወያኔ የትግራይን ልጆች አስጨርሶ ራሱን ዳግም ሚኒሊክ ቤተመንግስት ለማስገባት ያሰበው እቅድ ባጭር ቀረበት። አሁን የአዲሱን ቀን ጸሃይ እየሞቁ ከሞት የተረፉት የሰራዊቱ ክፍል እያሳደደ እግረኛ ሲያደርጋቸው ምን ይሰማቸው ይሆን?
ወያኔ አውሬ ነው። አሁን ሰራዊቱ ገጠር ናቸው፤ ዋሻ ናቸው ይበል እንጂ እነርሱ ከተማ ውስጥ ከዘመድና ከወያኔ አድናቂዎች ቤት ተሸጉጠው እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ውስኪና ጮማ የለመደ እንዴት ሆኖ ነው ከጊንጥ ጋር ዋሻ ውስጥ በእርጅና የሚኖረው። ውሸት ነው። ወያኔ ለኢትዮጵያ ወታደር ዲኮይ ነው መኪኖቻቸውን የተጠቀሙበት። እነርሱ ከተማ ውስጥ ናቸው። እያንዳንዷ ቤት መፈተሽ አለባት። ሌላው የሚገርመኝ ነገር የፌዴራል ፓሊስ ረዳት ውሾችን አለመያዙ ነው። ከሰው በበለጠ የጠላትን ጠረንና ዱካ አድኖ ለመያዝ የሰለጠኑ ውሾች አስፈላጊዎችን ነበሩ። ግን ምን ይደረግ ሰው ውሻ በሆነበት ሃገር ውሻን ማሳደግ ይከብዳል። ሌላው በተጠና መልኩ በማይካድራና በሌሎች ስፍራዎች ሰዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃት፤ የተጠቀሙቧቸውን መሳሪያዎች፤ ለምሳሌ አንድ ጄኔራል ሲናገር ጣውላ ላይ ምስማር ሰክተው ሰው ይመቱ ነበር ብሏል። ይህ ጉዳይ የኦሮሞ ገዳዮች የተጠቀሙበትን አይነት እንደሆነ ያመላክታል። መረጃን በመረጃ እያስደገፉ ለህዝባችን ማሳየት ተገቢ ነው። ሲኖ ትራክ ተነድቶባቸው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች፤ ወታደሩ ሊረሸን የተቆፈረው ጉድጓድ ሌሎችም ልቅም ተብሎ በፎቶ፤ በቪዲዪ በማስቀረት ከአይን ምስክሮችና ከሰለባው ተራፊዎች ጋር ለህዝብ መቅረብ አለበት። ቃል ብቻውን ባዶ ነው። መረጃ አስፈላጊ ነው። የሚገርመው አማላጅ ቄስ ሆነው የተመለሱት ራሳቸው የወያኔ ከፍተኛ መኮንኖች ናቸው። ስማቸው፤ ማእረጋቸው፤ ክፍያቸው ሁሉ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ መፋቅ አለበት። በሃገር ቤትም ሆነ በትግራይ የሰሩት ቤትና ንብረት መወረስ ይኖርበታል። ኢትዪጵያን ገድሎ ሃብት ለልጅ ለትውልድ ማስተላለፍ ወይም ከበርቴ እንደሆኑ መቀጠል የለባቸውም። በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ በማምለጥ ተደብቀው ያሉ የወያኔ ባለስልጣኖችን ከኢንተርፓል ጋር በማበር የወንጀላቸውን ዝርዝር፤ ከነሙሉ ስማቸው ይፋ ማድረግ ያስፈልጋል። አሁንም በሰራዊቱ ውስጥና በልዪ ልዪ የሃገሪቱ ከተሞች ትግራይን ጨምሮ ሰው ሲያሰቃዪ፤ ሲገርፉ፤ ሲገሉ፤ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ የነበሩ ሁሉ ተለቅመው መያዝ አለባቸው። የሰሜን እዙን ጄ/መርዝ ያበላው ማን ነው? ምርመራ ከበላበት ቤት ጀምሮ እስከ ላይ ድረስ መሰራት አለበት። የወያኔን አመራሮች እጅ ስጡ ማለት ወንጀል ነው። ባሉበት መደምሰስ ብቻ ነው። ኦ ስንት ግፍ ሰርተዋል። በትግራይ በረሃዎችና ከተሞች የወደቁት አጽሞች ይፋረድ። በትግራይ ከመሬት በላይና በታች ሰዎች የታገቱባቸው እስር ቤቶች ይመስክሩ። ግፍ ጽዋው ሞልቶ መፍሰስ ከጀመረ 45 ዓመት አለፈው።
በመጨረሻም እያንዳንዷ በትግራይ መሬት ውስጥ ያለች እስር ቤት፤ በእስር ቤቱ ዙሪያና በፍርድ ቤቶች አካባቢ ያሉ ፋይሎች ሁሉ በመረጃነት መያዝ አለባቸው። የሰው አጽም ወድቆ ስለተገኘ ጥሎ ማለፍ ትክክል አይደለም። ተለቅሞ፤ ወድቆ የተገኘበትን ቦታ መልክት በማድረግ ሊፈተሽና ማን መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስሽችሉ ብላቶች በመጠቀም አሁን ባይሆን ወደፊት መለየት ስለሚቻል ሰብስቦ ማስቀመጥ ይበጃል። ከማህል ሃገር እየታፈኑ ትግራይ ተወስደው የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩ እልፍ ናቸው።
የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔ ብቻ አይደለም። ሱዳንም ናት። ወያኔ እዚህ እንዲደርስ ከፍተኛ ድጋፍ ካደረጉት መካከል የሱዳን መንግስት አንድ ነው። ለሱዳን የኢትዮጵያ ስደተኞች የገቢ ማስገኛ ናቸው። ከዚያም አልፎ እያሰለጠኑና እያስታጠቁ ሃገራችን የሚያተራምሱት እነርሱ ናቸው። ንግግሩ ከሱዳን መንግስት ጋር ብቻ መሆን የለበትም። ምክንያቱም ሱዳን የግብጽ እስረኛ ናት። የሱዳን ህዝብ ግን ለኢትዮጵያ ጥሩ ልብ አለው። በስሙ መንግስታቸው የሚያደርገውን በይፋ ማሳወቅ ተገቢ ነው። ከሱዳን ጋር ውል መፈረም ማለት ከመንፈቅ ህጻን ጋር እንደመጫወት የሚቆጠር ነው። አይታመኑም። በጭላጭል ሳስብ ወያኔ ቀድሞ ወደ ሱዳን ባሻገራቸው ወጣቶች በመረዳት እንደገና ጦርነት መጀመሩ አይቀሬ ነው። ወደ ሱዳን ሲወጡ የማይካድራን ህዝብ እንዲገሉ ያደረገውም መመለስ እንዳይችሉ ነው። ማሰብ አስፈላጊ ነው። በሱዳን ካምፕ ውስጥ ያሉ ስደተኞች የወያኔ ደጀን ናቸው። ግብጽም ወጣ ገባ እያለች እንደሆነ ሰምተናል። ፉከራው ቀረርቶው ጭፈራው ቀርቶ መደራጀት አስፈላጊ ነው። እንዴት አድርገን ነው ከሱዳን በኩል የሚመጣውን ጥቃት መመከት እምንችለው በማለት እቅድ ሊወጣ፡ በቅርብና በሩቅ ያሉ ሃገር ወዳድ ወገኖችን ማሰልጠንና ማስታጠቅ አስፈላጊ ነው። እንዴት እየተናበቡና አንድ ላንድ እንዲደርስለት በሚያስችል ሁኔታ ሊደራጅ ይገባል። በቃኝ!