* "እኛ የገባነው ልናፈርሰው ነው" ሕዝቅኤል ገቢሣ በሰላማዊ ትግል መንግሥት ለመጣል ማቀዱን አስታውቆ ሃያ አንድ ቦርድ አባላትን ሰይሞ የሰነበተው የ-አብሮነት ማኅበር ሰባት ሥራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ታወቀ። ማኅበሩ “ለቦርድ አባላት” በሚል ባሰራጨው የ“እንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት አቶ ልደቱ፣ ከአማራ የማኅበሩ ፕሬዚዳንትና ሊቀመንበር ሆነዋል። መቅደስ አዳነ ከወላይታ (ምክትል)፣ አሸናፊ አብርሃም ከደቡብ (ጸሐፊ)፣ ሙሉጌታ ዘለቀ ከአማራ (ገንዘብ ያዥ)፣ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ሕዝቅኤል ገቢሣ /በተለይ እንግሊዘኛና ትግርኛ ጠንቀቀው ስለሚያውቁ/ ከኦሮሞ፣ የድርጅት አስተባባሪ እስማኤል ጎርሴ ከሶማሌ፣ የውጭ ግንኙነት ኦፊሰር መስፍን አየነው ከትግራይ መመረጣቸው ይፋ አድርጓል። ቀደም ሲል ምርጫው ከመደረጉ በፊት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላቶች ሕቡዕ እንደሚሆኑ … [Read more...] about የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ
sebhat nega
“ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ)
ልደቱ አያሌው ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር ያስተባበረው “አየር አንቀጥቅጥ” ትዕይንት ቅዳሜ ቀን ተካሂዷል። ልደቱ በስተመጨረሻ እንዳለው ከታሰበው በላይ የተሳካው የአየር ትዕይንት 15 ሰዎች ተናግረዋል፤ ሕዝብ በሳተላይት እና በተገኘው መንገድ ሁሉ ሰምቷል ብሏል። አገዛዙ ፈርቶ ኢንተርኔት አፍኗል፤ ዳታ ታቅቧል፤ ዩትዩብ እንዳይሠራ ተደርጓል ብለው ልደቱም፣ ቴዎድሮስም እየደጋገሙ ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህ የአየር ላይ ትዕይንት “ስልቴዎች” ማለትም ስብሃት፣ ልደቱ፣ ቴዎድሮስ በልዩ ሁኔታ የቀመሩትና ትህነግን በመታደግ ለሻዕቢያ የተሠራ ልዩ የስልቴዎች ስልት ነው። ንግግር ያደረጉት ሰዎች ጥቂቶቹን ስንቃኝ፤ … የድግሱ መሪ ቴዎድሮስ መደረጉ በራሱ ብዙ የሚለው ነገር አለ። ቴዎድሮስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወገኖቼን (የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ወያኔዎችን) የፈጀች ኢትዮጵያ ጥንቅር … [Read more...] about “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ)
ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ
ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው ሲሉ ስብሐት ለፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ክሱን ያቀረቡት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት ነው። አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል። በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍርድ ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍርድ … [Read more...] about የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
“ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ስዩም፣ አባይና አስመላሽ ተደመሰሱ፤ ደብረጽዮን 24 ሰዓት ተሰጥቶታል መከላከያ ሠራዊት ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ። ደብረጽዮን በ24 ሰዓት ውስጥ እጁን ካልሰጠ እንደሚደመሰስ ተነግሮታል። የመከላከያ ሠራዊት ሀይል ሥምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል። አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል። የህወሐት ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ … [Read more...] about “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ
ለትምህርት እንዲሆነን
ታላቁ መጽሐፍ የተጻፈበትን ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” ተጻፈ ይላል። በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ እጅግ ዘግናኝ ጊዜያት አሳልፈናል። በሥልጣን የተቀመጠ የሚወርድ እስከማይመስለውና ሰብዓዊነቱን እስኪዘነጋ ድረስ ሕዝብን ሲበድል ይኖራል። የሕይወቱ መጽሐፍ ሲጠናቀቅ ይሰናበታል። ስንብቱ ግን በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ሲሆን መመልከቱ በየዘመናቱ የመሰከርነው ሐቅ ነው። ንጉሡ በደርግ ሲተኩ፤ ደርግ “ለለውጥ ባጎፈረው” ህወሓት ሲተካ፤ አሁን ደግሞ አይደረስብንም፣ አንበገርም፣ እንደ ደርግ አንሆንም፣ ዓቅምም፣ ገንዘብም፣ ሁሉም ነገር አለን ሲል የነበረው በረኸኛው የወንበዴ ጥርቅም ከየጉድጓዱና ሰርጡ እንደ አውሬ … [Read more...] about ለትምህርት እንዲሆነን
“ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
አባይ ወልዱ እና አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ከገቡትና አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ካደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መካከል፤ አባይ ወልዱ የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበረ አብርሃም ተከስተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበረ ረዳኢ በርሄ የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ ሙለታ ይርጋ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ ዕቁባይ በርሄ የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ ጌታቸው ተፈሪ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ ኪሮስ ሃጎስ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች ንጋቱ አንገሶም አምደማርያም ተሰማ እነዚህ የጁንታው ከፍተኛ … [Read more...] about “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ
የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 4 የቡድኑ አባላት ደግሞ እርምጃም ተወስዶባቸዋል። የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ብሎ የገለፀውን የጁንታው አፈቀላጤ ጨምሮ 4 ከፍተኛ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ በርካቶች ሲደመሰሱ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህም መሰረት፣ ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) 1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ 2. ዘርአይ አስገዶም … [Read more...] about የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ
ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል። በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት … [Read more...] about ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ህጻናትን የሚማግደው የሌቦቹ ጀርባ
አዲሱ ህወሃት በአሮጌ አቁማዳ በትግራይ መቀሌ መሽገው የ13 አመት ልጅ እየመለመሉ ስልጠና ሲሰጡ የከረሙትና ትላንት በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉት ሁለቱ ሙሰኛና የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ጄኔራሎች በፎቶው የሚታዩት ናቸው! ብ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ፤ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ሲመጣ “ተደምሪያለሁ” በማለት ጊዜ ገዝቶ፤ ሚስቱንና ሶስት ሴት ልጆቹን አሜሪካ ወስዶ፤ ቤት ገዝቶ፤ አመቻችቶ፤ እንዲሁም ከመጀመሪያ ሚስቱ የወለደው ዳንኤል የተባለውን ልጁ በካናዳ እንዲኖር ያደረገው ተክለብርሃን፤ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ወደ መቀሌ ሸሸ። ሁለት ትላልቅ ህንፃዎች በመገናኛ ወደ ሃያት በሚወስደው መንገድ ያሉት (ተገትረው የቀሩ) በኦሮሚያ በርካታ መሬቶች የሸጠ፣ ለበርካታ ዘመዶቹ በሃብት ጥግ ያደረሰ ሙሰኛ ነው! ሁለተኛው ብ/ጀነራል ኃ/ሥላሴ … [Read more...] about ህጻናትን የሚማግደው የሌቦቹ ጀርባ










