• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ

June 3, 2026 08:50 pm by Editor Leave a Comment

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች በሌሎች አገራት ምርጫዎችና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ የሚደነግገውን መመሪያ ይፋ ካደረገ ቆይቷል።

እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2025 በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ተፈርሞ ለሁሉም የአሜሪካ ኤምባሲዎች የተላከው ይህ ይፋዊ መመሪያ፤ አሜሪካ ለረጅም ዓመታት በሌሎች አገራት ምርጫዎች ላይ ስታደርግ የነበረውን የቁጥጥር፣ የክትትልና የትችት ሚና በከፍተኛ ሁኔታ የገደበ ነው።

የመመሪያው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

  • የአገራትን ሉዓላዊነት ማክበር፦ መመሪያው የአሜሪካን “ቅድሚያ ለአሜሪካ” (America First) የተሰኘውን መርህ የሚከተል ሲሆን፣ የሌሎችን አገራት ብሔራዊ ሉዓላዊነት ማክበር እንደሚገባና አሜሪካ የራሷን የፖለቲካ አስተሳሰብ በሌሎች ላይ መጫን እንደሌለባት ያሳስባል።
  • ከአስተያየት መቆጠብ፦ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ዲፕሎማቶች በማንኛውም አገር ስለሚካሄድ ምርጫ ፍትሐዊነት፣ ግልጽነት ወይም ስለታዩ ጉድለቶች በይፋ አስተያየት መስጠት አይችሉም። አስተያየት መስጠት የሚቻለው ጉዳዩ “የአሜሪካን ቀጥተኛ የውጭ ጉዳይ ጥቅምን የሚነካ” መሆኑ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
  • የምስጋና መልዕክት ብቻ፦ አሜሪካ በሌላ አገር ምርጫ ላይ መግለጫ መስጠት በሚኖርባት ጊዜም ቢሆን፣ መግለጫው አጭር፣ አሸናፊውን ዕጩ “እንኳን ደስ አለህ/ሽ” የሚልና በጋራ ጥቅሞች ላይ ብቻ ያተኮረ መሆን አለበት። የምርጫውን ሂደት መተቸትም ሆነ መገምገም በጥብቅ የተከለከለ ነው።
  • የታዛቢ ድርጅቶችን አለመደገፍ፦ ቀደም ሲል የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እንደ ካርተር ሴንተር (Carter Center) ያሉ ገለልተኛ የምርጫ ታዛቢ ድርጅቶች የሚያወጧቸውን የትችት ሪፖርቶች ይደግፉና ያሰራጩ ነበር። ነገር ግን ከዋሽንግተን ቀጥተኛ ፈቃድ ካልተሰጠ በስተቀር አሁን ላይ እነዚህን ሪፖርቶች መደገፍ ተከልክሏል።

መመሪያው በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ያለው ተጽዕኖ

ይህ የአሜሪካ የፖሊሲ ለውጥ ሰኞ ግንቦት 24፤ 2006 ዓም ለተካሄደው ምርጫ ትልቅ ትርጉም አለው። ቀደም ባሉት ዓመታት ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ምርጫ ወቅት ስለ ሂደቱ ዲሞክራሲያዊነት፣ ስለ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እና ስለ ምርጫው ነጻና ፍትሐዊነት ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን ትሰጥ ነበር።

ነገር ግን በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፣ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ምርጫ ማንኛውም የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን ወይም በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በምርጫው ሂደት ላይ ምንም ዓይነት የትችትም ሆነ የድጋፍ አስተያየት አይሰጥም። ይህም ማለት የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በኢትዮጵያ የውስጥ የፖለቲካ ውድድር ውስጥ ጣልቃ ከመግባት ሙሉ በሙሉ ይቆጠባሉ ማለት ነው።

ይህ የአሜሪካ አካሄድ በተለይ በዳያስፖራ የሚገኘውን ተቃዋሚ አንገት ያስደፋና ያለ ተስፋ ያስቀረ ሆኗል። መመሪያው የዛሬ ዓመት የወጣ መሆኑን የማያውቁ ግን ፖለቲካ እንተነትናለን የሚሉ አሁንም ከአሜሪካ የውግዘት መግለጫ እየጠበቁ እንደሆነ ጎልጉል ባደረገው ማጣራት ለመረዳት ችሏል።

በመሆኑም ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ቦርድ አሸናፊውን ፓርቲ ይፋ ሲያደረግ ከአሜሪካ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለፓርቲውና ለፕሬዚዳንቱ የሚደስር ይሆናል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: America First, Election 2026, Trump, Trump Will Fix It

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
  • የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ October 9, 2026 12:33 pm
  • ሴቶችን በመሾም ኢትዮጵያ በእርግጥ ተወዳዳሪ የሌላት ነች?  October 8, 2026 11:20 pm
  • Ethiopian Defense Forces Capture Advanced TPLF Military Drones and Documents Linked to Sudan October 7, 2026 12:40 pm
  • በሱዳን በኩል ለትህነግ የተላኩ የM6 ድሮኖችና ወታደራዊ መሣሪያዎች በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተገለጸ October 7, 2026 11:20 am
  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
Copyright © 2026 · Goolgule