የሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ፣ የቀድሞው የአብን ተመራጭና የአሁኑ የኢህአፓ/ትብብር እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ዶ/ር አበባው ደሳለው በሰጡት ቃለ መጠይቅ በምርጫው ማሸነፍ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ብስጭትና ንዴት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ተወዳድረው ከትብብሩ እና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሕዝብ የተመረጡትንም በብልጽግና ችሮታና ድጋፍ የተመረጡ፣ በምርጫ ሳይሆን በቅርጫ ያሸነፉ በማለት ወርፈዋል። ወደ ፓርላማ አለመግባት ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የተከበሩ አቶ አበባው ብሔር ተኮር ከሆነው አብን ወጥተው ወደ ኢህአፓ የገቡበትን ምክንያት አስረድተዋል። “ኢህፓን የመረጥኩበት ምክንያት ደግሞ እንደሚታወቀው ጠንካራ ታጋዮች የወጡበት ፓርቲ ነው። ለተራ ጥቅም ብለው ለተራ ኢኮኖሚ ጉዳይ ብለው ህሊናቸውን የማይሸጡ … [Read more...] about ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ
Election 2026
እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር
* ሚስጥረ፤ “ወደ ምርጫው የገባኹት አምኜበት አይደለም” የኢህአፓና የትብብሩ ዋና ጸሐፊ የሆነችው ሚስጥረሥላሴ ታምራት ከአዲስ ኢንሳይደር ጋር ባደረገችው ውይይት ወደ ምርጫው የገባችው አምናበት እንዳልሆነ ተናገረች። ትብብሩ የተከፋፈለ መሆኑን ያልካደችው ሚስጥረ የአውሮጳ ኅብረትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ምርጫውን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ “ለእኛ” ከነገሩን ጋር የተለያየ ነው በማለት ኅብረቱ የሐሰት መግለጫ እንዳወጣ እንደምታ የሚሰጥ አስተያየት ሰጥታለች። ከምርጫው በፊት ቅድመ ሁኔታ እንዳስቀመጡና እነዚያ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ወደ ምርጫ መግባታቸውን በተመለከተ ስትመልስ እንዲህ ብላለች፤ “ወደ ሰባት የሚሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሚደረግ ምርጫ አምባገንነትን ነው እንጂ የሚያዋልደው በፍጹም የዲሞክራሲ መገለጫ ሊሆን አይችልም በሚል … [Read more...] about እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር
የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ “ትብብር” የተሰኘው ቡድን ያወጣው መግለጫ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) እና የእናት ፓርቲ አመራሮች “ትብብር” የተባለውን ስብስብ ወክለው ኢኤምኤስ ለተባለው ዩትዩብ የተናገሩት በሀገር ውስጥና በዲያስፖራው ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ አስነሳ። ሚስጥረሥላሴ ከኢህአፓና ጌትነት ከእናት ፓርቲ ሆነው “ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ያልሆነ የጨረባ ምርጫ ነው” በማለት ውድቅ ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሕዝቡ ግን “ቀድሞውኑ ለገዢው ፓርቲ አጃቢና ድራማ አድማቂ ለመሆን የገባችሁ የፖለቲካ ድንኮችና ሆዳሞች ናችሁ” በማለት በብርቱ እያወገዛቸው ይገኛል። የፖለቲካ ተንታኞችና የውስጥ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ የኢህአፓ እና የ“ትብብር” ጥምረት መሪዎች ቀድሞ የነደፉት … [Read more...] about የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ
አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች በሌሎች አገራት ምርጫዎችና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ የሚደነግገውን መመሪያ ይፋ ካደረገ ቆይቷል። እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2025 በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ተፈርሞ ለሁሉም የአሜሪካ ኤምባሲዎች የተላከው ይህ ይፋዊ መመሪያ፤ አሜሪካ ለረጅም ዓመታት በሌሎች አገራት ምርጫዎች ላይ ስታደርግ የነበረውን የቁጥጥር፣ የክትትልና የትችት ሚና በከፍተኛ ሁኔታ የገደበ ነው። የመመሪያው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ የአገራትን ሉዓላዊነት ማክበር፦ መመሪያው የአሜሪካን "ቅድሚያ ለአሜሪካ" (America First) የተሰኘውን መርህ የሚከተል ሲሆን፣ የሌሎችን አገራት ብሔራዊ ሉዓላዊነት ማክበር እንደሚገባና አሜሪካ የራሷን የፖለቲካ አስተሳሰብ በሌሎች ላይ መጫን እንደሌለባት … [Read more...] about አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ




