ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ምንም ጊዜ የማይቀየር፣ ሊስተባበል የማይችልና ልዩ የሆነ መለያ አላቸው። ይህም ለክህደትና ለመሸጥ፣ በኢትዮጵያውያን አገላለጽ ለባንዳነት የተጋለጡ ወይም መደምደሚያቸው ባንዳነት ነው። ሌሎቹን እንተዋቸውና በአገራችን ዋና ምስክር የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግን) ማንሳት ይበቃል። ጥሩም መከራከሪያ የሚቀርብበት የዘመኑ አፍላ ታሪክ ነው። ቃለ ምልልሱ ከተካሄደ ቆይቷል። ሰሞኑን ግን የሩሲያ መንግሥት ቲቪ በድጋሚ ሲያሳየው ነበር። ጋዜጠኛው ቭላዲሚር ፑቲንን ይጠይቃል። ይህን የቆየ ቃለ መጠይቅ ማስተላለፍ የተፈለገው በቀድሞ ወጥ ቀቃይ የሚመራውና አሁን ቫግነር የተባለው ኢመደበኛ አደረጃጀት ከሩስያ መከላከያ ጋር የገባበትን መፈታተን ተከትሎ ነው። ጥያቄ - ይቅርታ ታደርጋለህ?ፑቲን - አዎ፤ ግን ለሁሉም አይደለም፤ጥያቄ - ይቅር ለማለት የማይቻለው … [Read more...] about ኢመደበኛነት – አገር አፍራሽ የዘመኑ ባንዳነት