ለቀረበለት ሕጋዊ ደብዳቤ ዛቻን አስቀድሟል ከለውጡ በኋላ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የመጠጋጋት ህልምና ውጥን እንደሌለው ሲወተውት የነበረው ጃዋር በቅርቡ ኦፌኮን መቀላቀሉን ተከትሎ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ሊልክለት በዝግጅት ላይ መሆኑ ትላንት በመረጃ ገልጸን ነበር። ዛሬ (ማክሰኞ) የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳመለከተው ጃዋር የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ እጁ ገብቷል፤ ፈርሞ ተቀብሏል። ደብዳቤው እንዳይዘጋጅ ያደረገው ሩጫ ሳይሳካ በመቅረቱ ዛቻ እየሰነዘረ መሆኑም ታውቋል። በተደጋጋሚ የሕግ የበላይነትን በማንሳት ዲስኩርና ማብራሪያ የሚሰጠው ጃዋር፣ ምርጫ ቦርድ በጻፈለት ደብዳቤ መቆጣቱና ወይዘሪት ብርቱካን ላነሱት የሕግ ጥያቄ መልስ ከመመለስ ይልቅ ዛቻን መመረጡን የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ይፋ አድርገዋል። በሚያስተዳድራቸው ሠራተኞቹና አበል … [Read more...] about ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ