* ሚስጥረ፤ “ወደ ምርጫው የገባኹት አምኜበት አይደለም” የኢህአፓና የትብብሩ ዋና ጸሐፊ የሆነችው ሚስጥረሥላሴ ታምራት ከአዲስ ኢንሳይደር ጋር ባደረገችው ውይይት ወደ ምርጫው የገባችው አምናበት እንዳልሆነ ተናገረች። ትብብሩ የተከፋፈለ መሆኑን ያልካደችው ሚስጥረ የአውሮጳ ኅብረትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ምርጫውን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ “ለእኛ” ከነገሩን ጋር የተለያየ ነው በማለት ኅብረቱ የሐሰት መግለጫ እንዳወጣ እንደምታ የሚሰጥ አስተያየት ሰጥታለች። ከምርጫው በፊት ቅድመ ሁኔታ እንዳስቀመጡና እነዚያ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ወደ ምርጫ መግባታቸውን በተመለከተ ስትመልስ እንዲህ ብላለች፤ “ወደ ሰባት የሚሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሚደረግ ምርጫ አምባገንነትን ነው እንጂ የሚያዋልደው በፍጹም የዲሞክራሲ መገለጫ ሊሆን አይችልም በሚል … [Read more...] about እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር

