የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ለማከናወን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሆነውና የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት/ የሚያስገቡበት መርሃ ግብር መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፀድቋል። በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወሰዱ
nebe
የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ
የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመሥራች አባላት ጉዳይን አስመልክቶ ፓርቲው ያቀረበው የመሥራች አባላት ዝርዝር ላይ ቦርዱ 50 የሚሆን ናሙና በመውሰድ ያደረገው ማጣራት ስለ ትክክለኛነቱ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባው በመሆኑ፤ ቦርዱ ጉዳዩን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልኮት እንደነበር ይታወሳል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ባደረገው የማጣራት ሥራ ከሶማሌ ክልል 1145 መሥራች አባላት፣ ከአፋር ክልል 72 መሥራች አባላት፣ ከኦሮሚያ ክልል 23 መሥራች አባላት፣ ከአ.አ. ከተማ አስተዳደር 58 መሥራች አባላት በጠቅላላው የ1298 መሥራች አባላት በተጠቀሱት አድራሻ ያለመኖራቸውን ማረጋገጡን የሚያስረዳ መግለጫ በመስጠቱ የቦርዱም ሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ የማጣራት ሥራ የሚያሣየው ፓርቲው እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው በቃለመኃላ በተረጋገጠ ሰነድ ያቀረበው የመሥራች አባላት ሥም ዝርዝር … [Read more...] about የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ