የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመሥራች አባላት ጉዳይን አስመልክቶ ፓርቲው ያቀረበው የመሥራች አባላት ዝርዝር ላይ ቦርዱ 50 የሚሆን ናሙና በመውሰድ ያደረገው ማጣራት ስለ ትክክለኛነቱ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባው በመሆኑ፤ ቦርዱ ጉዳዩን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልኮት እንደነበር ይታወሳል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንም ባደረገው የማጣራት ሥራ ከሶማሌ ክልል 1145 መሥራች አባላት፣ ከአፋር ክልል 72 መሥራች አባላት፣ ከኦሮሚያ ክልል 23 መሥራች አባላት፣ ከአ.አ. ከተማ አስተዳደር 58 መሥራች አባላት በጠቅላላው የ1298 መሥራች አባላት በተጠቀሱት አድራሻ ያለመኖራቸውን ማረጋገጡን የሚያስረዳ መግለጫ በመስጠቱ የቦርዱም ሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ የማጣራት ሥራ የሚያሣየው ፓርቲው እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው በቃለመኃላ በተረጋገጠ ሰነድ ያቀረበው የመሥራች አባላት ሥም ዝርዝር በተጭበረበረ ተግባር የፓርቲውን የዳግም ምዝገባውን ሂደት ማስፈጸም መፈለጉን እንደሆነ ተረድቷል።
ስለዚህ በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 98/1/ /ሠ/ መሠረት የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ እንዲሰረዝ ተወስኗል። ጉዳዩም በአቃቤ ሕግ በኩል ክስ ተመስርቶበት ይገኛል።
የተለያዩ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም ሰነዶችን አሟልተው እንዲያቀርቡ ተገልጾላቸው የማጣራት ሂደታቸው ካልተጠናቀቁት ፓርቲዎች መካከል የሚከተሉት ላይ ቦርዱ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ሀ. በቂ ማብራሪያ በማቅረብ መስፈርቱ ሟሟላት አጠናቀው ምዝገባቸው የፀደቀ ፓርቲዎች
• ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – 43%
• ሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ሐዲድ/ (የመስራች ቁጥር የማይመለከታቸው አነስተኛ ቁጥር ያለው ብሔረሰብ ፓርቲ)
• የመላው ኢትዮጵያዊያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) – 62%
ለ. የማጣራት ሂደታቸው የተጠናቀቀ ነገር ግን የቴክኒክ መስፈርቶች ይቀራቸው ከነበሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሂደታቸውን አሟልተው ያጠናቀቁና ተቀባይነት ያገኙ
• ህዳሴ ፓርቲ /ሕዳሴ/ – 100%
• የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት /ካሕዴኅ/ – 71%
• የሲዳማ አንድነት ፓርቲ /ሲአፓ/ – 85%
ሐ. ከቦርዱ በተሰጠው አስተያየት መሠረት በሰነዶች ላይ ማስተካከያ ባለማድረግ የተሰረዘ
• የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጉሕዴን/
መ. በፓርቲ አርማቸው ላይ ቅሬታ በመቅረቡ ለአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የኢትኖግራፊ የትምህርት ክፍል የባለሞያ ማብራሪያ የተጠየቀበት
• የራያራዩማ ፓርቲ
5. ከዚህም በተጨማሪ አፈጻጸሙ በተጀመረው የ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ መሳተፍ የሚችሉት ፓርቲዎች በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፉት 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሆናቸውን ቦርዱ ያሳውቃል። ለመሳተፍ ቅቡልነት ያላቸው እስከአሁን ያለውን ሂደት ያጠናቀው የጨረሱ ፓርቲዎች መሆናቸውን ያሳውቃል። (ምንጭ የምርጫ ቦርድ ፌስቡክ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ያሬድ ሰለሞን says
ለሀገረችን አንድነትና ሰላም ማጠት ዋና ምክንያት አቅም አልባ የፖሎቲካ ፓርቲዎችና ስግብግብ የሀይማኖት ተቋሞች ናቻው ስር ነቀል ላውጥና ጥብቅ
ቁጥጥር ያስፈልገል #