በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሰረት መንግሥት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ላገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች በየዓመቱ የበጀት ድጎማ ያደርጋል፡፡ በዚሁ መሠረት የ2015 በጀት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ለማከፋፈል በምርጫ ቦርድ ቀመር መሰረት የገንዘብ ክፍፍሉ መደልደሉን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ ቦርዱ ይህንኑ አስመልክቶ ቅዳሜ መጋቢት 2/2015 ከፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ውይይት በአገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፓርቲዎች 65 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ መደበኛ በጀት የበጀት ሲሆን፣ ፓርቲዎች ለሚያከናውኑት የሲቪል ትምህርት 41 ሚሊዮን ብር መመደቡን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል፡፡ ፓርቲዎች የሚደርሳቸው ገንዘብ በዋና ዋና መስፈርቶች የሚመዘን ሲሆን፣ በሴት አባል ብዛት፣ በሴት አመራር ብዛት፣ በአካል ጉዳተኛ አባል ብዛትና በአካል ጉዳተኛ አመራር ብዛት ተሰልቶ የሚመደብ መሆኑ … [Read more...] about ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ
birtukan midekssa
የመንግሥት ሚዲያዎች ፍትሃዊነታችንን አጉድላችሁብናል – ወ/ት ብርቱካን
“ዛሬ እዚህ የምትቀርጹን የመንግስት ሚዲያዎች በጣም በትህትና ልነግራችሁ እፈልጋለሁኝ። የመንግስት ባለሥልጣናት ኮታቸው ላይ የተሰካው ማይክራፎን የማይወልቅ ይመስል ሌት ተቀን የእነሱን ካምፔን እና ቅስቀሳ ስታስተላልፉ ቆይታችሁ የተቃዋሚዎችን 10 እና 15 ደቂቃ ማድረጋችሁ ፍትሃዊነታችንን አጉድሎብናል። እንዳላየ ያለፍነው ግማሹ የኛ ሥልጣን ስላልሆነ ነው። የእኛን ስልጣን እንደምናከብር የሌሎችንም እናከብራለን” የምርጫ ውጤት በማሳወቂያ መርሃግብር ላይ ይህንን የተናገሩት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ሰብሳቢዋ "ኢትዮጵያ ሁልጊዜ በምርጫ ብቻ ስልጣንን የምታሸጋግር አገር መሆኗን አሳይታለች" ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውጤት ማሳወቂያ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። መርኃ-ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር … [Read more...] about የመንግሥት ሚዲያዎች ፍትሃዊነታችንን አጉድላችሁብናል – ወ/ት ብርቱካን
ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ውጤት አሳወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በ440 የምርጫ ክልሎች የተከናወነውን አጠቃላይ ምርጫ ውጤት ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓም በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ መርሐ ግብር ይፋ አደረገ፡፡ ቦርዱ እስካሁን በሒደት ካሳወቃቸው የተረጋገጡና ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች በማስከተል ምርጫው በተከናወነ በ20 ቀናት ውስጥ የምርጫውን ውጤት ማሳወቅ እንደሚኖርበት በሕግ በተደነገገው መሠረት ቅዳሜ ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ መርሃ ግብር አስታውቋል፡፡ ቦርዱ ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረትም፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድምጽ ከተሰጠባቸው 425 የምርጫ ክልሎች መካከል ብልጽግና ፓርቲ 410 መቀመጫዎችን ያሸነፈ ሲሆን፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አምስት፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ አራት፣ በኦሮሚያ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ውጤት አሳወቀ
“ቀኑ ለመራጮችና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ለአገራችንም ጥሩ ነው” ወ/ሪት ብርቱካን
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እኩለ ቀን ላይ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ቀኑ ለመራጮች፣ ለፓርቲዎችና በአጠቃላይ ለአገራችን ጥሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በመጀመርያው ዙር የምርጫ ሒደት እስካሁን አንድም የፀጥታ ችግር አልገጠመንም፡፡ አምቦ አንድ ጣቢያ ላይ ምንም የተፈጠረ ነገር ሳይኖር ለአስፈጻሚዎች በደረሳቸው መረጃ በመደናገጥ ለጊዜው ገለል ብለዋል፡፡ ነገር ግን እናስቀጥለዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከባድ ችግር የለም፡፡ ምርጫው መደረግ ባለባቸው ሁሉም ሥፍራዎች እየተካሄደ ነው፡፡ ዜጎችም እየመረጡ ይገኛሉ፡፡ ምርጫው መደረግ ባለባቸው ጣቢያዎች በአብዛኛው በሚባል ሁኔታ በሰዓቱ ከፍተው መራጮችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ 9 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ኃላፊነት የጎደላቸው አስፈጻሚዎች በቦታቸው ባለመገኘታቸው ጣቢያዎቹ ሳይከፈቱ ቆይተዋል፡፡ … [Read more...] about “ቀኑ ለመራጮችና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ለአገራችንም ጥሩ ነው” ወ/ሪት ብርቱካን
“ለአንድ ፓርቲ የማደላ ከሆነ ሄጄ እዚያው ፓርቲ እገባለሁ” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከቀደምቶቹ አምስት ምርጫዎች ለየት ያለና ሕዝቡ በምርጫ ሒደት እምነት እንዲያገኝ የሚያስችለው እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ እንዲሁም መንግሥት በተደጋጋሚ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል፡፡ ይኼ ምርጫ በመንግሥት ትኩረት እንደተሰጠው ከሚያሳዩ ጉዳዮች አንዱ የተመደበለት በጀት መጠን ሲሆን፣ በአገሪቱ የምርጫ ታሪክ ከፍተኛ የሆነው 2.5 ቢሊዮን ብር ለምርጫ ዝግጅት በፓርላማ ፀድቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ምርጫው በአንድ ዓመት እንዲራዘም ከተደረገ በኋላ፣ ቦርዱ ለፓርላማ የ1.1 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ይኼ ከመንግሥት የቀረበለት በጀት ሲሆን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር የምርጫ ድጋፍ አማካይነት ደግሞ፣ በዓይነት የሚደረግ 1.8 ቢሊዮን ብር ገደማ … [Read more...] about “ለአንድ ፓርቲ የማደላ ከሆነ ሄጄ እዚያው ፓርቲ እገባለሁ” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ
ለቀረበለት ሕጋዊ ደብዳቤ ዛቻን አስቀድሟል ከለውጡ በኋላ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የመጠጋጋት ህልምና ውጥን እንደሌለው ሲወተውት የነበረው ጃዋር በቅርቡ ኦፌኮን መቀላቀሉን ተከትሎ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ሊልክለት በዝግጅት ላይ መሆኑ ትላንት በመረጃ ገልጸን ነበር። ዛሬ (ማክሰኞ) የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳመለከተው ጃዋር የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ እጁ ገብቷል፤ ፈርሞ ተቀብሏል። ደብዳቤው እንዳይዘጋጅ ያደረገው ሩጫ ሳይሳካ በመቅረቱ ዛቻ እየሰነዘረ መሆኑም ታውቋል። በተደጋጋሚ የሕግ የበላይነትን በማንሳት ዲስኩርና ማብራሪያ የሚሰጠው ጃዋር፣ ምርጫ ቦርድ በጻፈለት ደብዳቤ መቆጣቱና ወይዘሪት ብርቱካን ላነሱት የሕግ ጥያቄ መልስ ከመመለስ ይልቅ ዛቻን መመረጡን የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ይፋ አድርገዋል። በሚያስተዳድራቸው ሠራተኞቹና አበል … [Read more...] about ጃዋር ቀነ ገደብ ያስቀመጠውን የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ፈርሞ ተቀበለ
የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር
ሕግን በማስከበር ስመጥር የሆኑትና ለዚህም የቀድሞው ታሪካቸው የሚመሰክርላቸው የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለጃዋር መሃመድ የማስጠንቀቂና የማብራሪያ ደብዳቤ ሊልኩ መሆኑን ታወቀ። ጃዋር ለደብዳቤው በቂ ምላሽ ካልሰጠ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚያደርጋቸው የፖለቲካ ተግባራት በሙሉ ሊታገዱ እንደሚችሉ አብሮ ለመረዳት ተችሏል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ በላከው መረጃ መሠረት ምርጫ ቦርድ ለጃዋር ለመላክ ያረቀቀው ደብዳቤ ጃዋር በየትኛው የሕግ አግባብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሳይኖረው በኢትዮጵያ የምርጫ ሒደትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ማስረጃና ማብራሪያ በቀነ ገደብ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው። በምርጫ ቦርድ ውስጥ የሚገኙ የጃዋር ሰዎች ደብዳቤው ሊላክለት መሆኑን ያስታወቁት ሲሆን ጃዋርም ደብዳቤው ወጪ ከመደረጉ በፊት የቦርዱ ሰብሳቢዋን … [Read more...] about የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር