• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር

January 21, 2020 12:45 am by Editor 2 Comments

ሕግን በማስከበር ስመጥር የሆኑትና ለዚህም የቀድሞው ታሪካቸው የሚመሰክርላቸው የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለጃዋር መሃመድ የማስጠንቀቂና የማብራሪያ ደብዳቤ ሊልኩ መሆኑን ታወቀ። ጃዋር ለደብዳቤው በቂ ምላሽ ካልሰጠ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚያደርጋቸው የፖለቲካ ተግባራት በሙሉ ሊታገዱ እንደሚችሉ አብሮ ለመረዳት ተችሏል።

የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ በላከው መረጃ መሠረት ምርጫ ቦርድ ለጃዋር ለመላክ ያረቀቀው ደብዳቤ ጃዋር በየትኛው የሕግ አግባብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሳይኖረው በኢትዮጵያ የምርጫ ሒደትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ማስረጃና ማብራሪያ በቀነ ገደብ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው።

በምርጫ ቦርድ ውስጥ የሚገኙ የጃዋር ሰዎች ደብዳቤው ሊላክለት መሆኑን ያስታወቁት ሲሆን ጃዋርም ደብዳቤው ወጪ ከመደረጉ በፊት የቦርዱ ሰብሳቢዋን ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማግኘት ሙከራ እያደረገ መሆኑን ጎልጉል ያለው መረጃ ይጠቁማል። ይሁን እንጂ የሕግ የበላይነትን በማጽናትና ከፍ በማድረግ የሚታወቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ከአቋማቸው ንቅንቅ እንደማይሉና ሕግን በማስከበሩ መንገድ እንደሚገፉት ለመረዳት ተችሏል።

በአገሪቱ ሕገመንግሥትና ሌሎች ህጎች መሠረት አንድ ሰው በምርጫ ለመሳተፍም ሆነ ማንኛውንም ከምርጫ ጋር የተያያዘ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዲኖረው ይደነግጋል። ይህ በበርካታ የዓለም አገራት የሚሠራበት ሕግ ሲሆን ጃዋር መሃመድ ደግሞ የአሜሪካ ዜግነት እንዳለው ይታወቃል። ሆኖም ይህንን እውነታ በመቃረን ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመሩት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፓርቲ ጃዋርን በፓርቲው አባልነት ከመቀበል በተጨማሪ “ዜግነት ኢትዮጵያዊ” የሚል የመታወቂያ ካርድ ሰጥቶታል።

በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሕግ አካሄድ ከሆነ ጃዋር አቅርብ የሚባለውን መረጃ ለማቅረብ ስለማይችል ከኦፌኮ ሊታገድና እስካሁን ያለፈቃድ ስላከናወነው በሕግ ሊጠየቅ እንደሚችል ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ኦፌኮም እንደ ፓርቲ በዚህ ዓይነት ተግባር ውስጥ አባሉ እንዲሳተፍ ማድረጉ፣ “ኢትዮጵያዊ” የሚል የመታወቂያ ሰነድ መስጠቱ በህግ እንደሚያስጠይቀው ከወዲሁ የሚሰጡ አስተያየቶች ይጠቁማሉ።

በተያያዘ ዜና ኦፌኮ ሰሞኑን በሰላሌ ባደረገው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ኃይለሚካኤል ታደሰ የተባለ ከጃዋር መሃመድ ጋር በመሆን ያደረገውን ሕዝብን ከሕዝብ ደም የሚያፋስስ ቅስቀሳ በተመለከተ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዜጋ ለወ/ሪት ብርቱካን ደብዳቤ ጽፈዋል።  

ስማቸው ዮናስ መኮንን መሆኑን የገለጹት ግለሰብ እንደተናገሩት “እርስዎ የሚመሩት የምርጫ ቦርድ በምርጫ ህጉ መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው የድርጊት መርሐግብር ከተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ ውጪ ምንም ዓይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንዳያደርጉ በቅርቡ ማዘዙ ይታወቃል።

“በተጨማሪም በፖለቲካ ፓርቲዎች እና በምርጫ ቦርድ መካከል በተደረገ ውይይት መሠረት የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያደርጉት የምርጫ ቅስቀሳ ከአመጽ የፀዳ እንዲሆን ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህንን ሳያደርጉ ቢገኙ ፈቃድ እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እንደነበርም እናስታውሳለን።

“ይሁን እንጂ ኦፌኮ የምርጫ ቦርድን ትእዛዝ እና መመሪያ በመጣስ በጠራው የምርጫ ቅስቀሳ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆንን ዜጎችን ሕገመንግሥታዊ የአምልኮ መብት የሚጥስ እና አማኞቹን ሰቀቀን ውስጥ የሚከት ለጥቃትም የሚያጋልጥ ጠብ አጫሪ ቅስቀሳ አድርጎብናል።

“ከምርጫ ሕጉ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ “በህዝብ ደህንነት ሰላምና ተረጋግቶ መኖር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች” በሚለው ክፍል ሥር በአንቀጽ 492 “የተፈቀደውን የሃይማኖት ሥርዓት ማወክ፣ ማስተሃቀር የሚያስቀጣ ወንጀል ነው!” የሚለውን ድንጋጌ በአደባባይ ጥሷል።

“ስለዚህም እርስዎ በኃላፊነት የሚመሩት የምርጫ ቦርድ ኦፌኮ ዜጎችን አላስፈላጊ ፍጥጫ ውስጥ ከሚከት እና ኦርቶዶክስ አማኞችን ለጥቃት ከሚያጋልጥ ጠብ ጫሪ ቅስቀሳው እንዲታቀብ እና ገብረጉራቻ ላይ አድርጎት ለነበረው ጥፋትም በይፋ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ እንዲያደርግ እንደ አንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባል እና ኢትዮጵያዊ ግብር ከፋይ ዜጋ እጠይቃለሁ” በማለት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት ጃዋር መሃመድ ከኤልቲቪ ቤተልሔም ታፈሰ ጋር ባደረገው ጭውውት የዜግነቱን ጉዳይ እየሠራበት እንደሆነና በቀናት ጊዜ ውስጥ ይህንን ጉዳይ እንደሚጨርስ መናገሩ ይታወሳል። ሆኖም በዜግነት ጉዳይ ላይ ባለሙያ የሆኑ እንደሚናገሩት ከአሜሪካ ዜግነት ለመቀየር መሟላት ያለባቸው የግብርና መሰል በርካታ መሥፈርቶች ያሉ ሲሆን ሒደቱም እስከ አስራአምስት ወራት ሊፈጅ እንደሚችል ይናገራሉ። 


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

          

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: birtukan midekssa, Full Width Top, jawar, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    January 22, 2020 08:45 am at 8:45 am

    የአሜሪካ የዜግነት ሕግ፣ የግለሰቦችን የዜግነት መቀየር ሕጋዊ መብት ያከብራል፡፡ ዜግነታቸውን ለመቀየር ለሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎችም ግልጽ የሆኑና አመልካቾቹ ማድረግ ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡
    አመልካቹ በየአሜሪካ መንግሥት የተዘጋጁትን ለተለያዩ ዓላማ የታቀዱትን ቅጽ DS-4079, 4080,4081, 4082 እና 4083 የተባሉትን በትክክል መሙላትና ማመልከቻውን ፕሮሴስ ለማድረግ የሚረዳ $2,500 የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ወይም በቼክ ፈርሞ መስጠት ይኖርበታል፡፡ መሞላት ካለባቸው ብዙ ቅጾች አንዱ፣ አመልካቹ ባለፉት አምስት ዓመታት እንደ አንድ የአሜሪካ ዜጋ በአሜሪካም ሆነ በውጭ አገር በኖረበት ወቅት አስፈላጊውን የመንግሥት ግብርና ቀረጥ በአግባቡ መክፈሉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
    አመልካቹ በቆንሲላው የሚፈለጉ ዶኩሜንቶች በሙሉ መሟላታቸውን ካረጋገጠ በኋላ ለወደፊት ሊኖርበት በሚፈልግበት “አዲስ አገር” በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቆንሲላ ጽህፈት ቤት ሄዶ ዶኩሜንቶቹን ለማስረከብ ቀጠሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ በቀጠሮው ቀን አመልካቹ በግንባር የመቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

    አመልካቹ የአሜሪካን አገር የቀረጥ/ግብር ዓመታዊ ፎርም (IRS 8854) መሙላቱን እርግጠኛ መሆን አለበት፡፡ ከአሜሪካ ዜግነት መላቀቅ ማለት ከግብር ዕዳ ነጻ መሆን ማለት ስላልሆነ በዚሁ በመጀመርያው ቀጠሮ ወቅት ይህንን ፎርም በትክክል ሞልቶ በቆንሲሉ ፊት ፈርሞ ማስረከብ አለበት፡፡ በሕጉ መሠረት የአመልካቹ ግለሰብ ዓመታዊ ገቢ ከአንድ መቶ ስድሳ አምስት ሺህ ዶላር በታች ከሆነ ግለሰቡ ዜግነቱን በመቀየሩ የሚያስከትለው ችግር እምብዛም አይኖርም፡፡ ከዚያ በላይ ጥሬ ሃብትና የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት ያላቸው አመልካቾች ግን ለየት ያለ ፎርም መሙላት አለባቸው፡፡

    ቆንሲሉም የቀረበለትን ዶኩሜንት ትክክለኛ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ በሚሠጠው ሁለተኛ ቀነ ቀጠሮ በግንባር ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ማድረግ የአመልካቹ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ የመጀመርያው ቃለ መጠይቅና አመልካቹ ከሚፈጽመው መሃላ በኋላ ቆንሲሉ፣ ዜጋው “ዜግነትን ለመቀየር” ማመልከቻ ማስገባቱን ብቻ የሚያስረዳ ሴርቲፊኬት ለአመልካቹ ይሠጣል፡፡ የግለሰቡ የዜግነት መልቀቂያ ማመልከቻ በተለያዩ የአሜሪካ መንግሥት ተቋማት (CIA, FBI, Homeland Security etc) በሚገባ ተጠንቶና አመልካቹ ዜግነቱን መልቀቁ የአሜሪካንን መንግሥት ጥቅም የማይነካ መሆኑ ከታመነበት በኋላ ወሳኙ የዜግነት መቀየር ሴርቲፊኬት (Certificate of Loss of Nationality– CLN) በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒቴር ተፈርሞ በቆንሲሉ በኩል ለአመልካቹ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ የዜግነት መቀየር ሴርቲፊኬት ተፈርሞ እስኪመጣ ድረስ የተወሰነ የጊዜ ገደብ ባይኖረውም፣ በአማካይ ግን ከአምስት እስከ አሥራ አምስት ወራት እንደሚፈጅ ልምዶች ያመለክታሉ፡፡ በአሜሪካን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈረመው “የዜግነት መቀየርያ ሴርቲፊኬት”(Certificate of Loss of Nationality –CLN) የመጨረሻውና ወሳኙ ከአሜሪካን ዜግነት የመላቀቂያ ማረጋገጫ ዶኩሜንት ነው፡፡
    *******************************
    የኢትዮጵያ የዜግነት ሕግ በአንቀጽ 20(1) ላይ፣ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በራሱ ፍላጎት የሌላ አገር ዜግነት ካገኘ የኢትዮጵያ የዜግነት ሕግ በአንቀጽ 20(3) ላይ በማናቸውም ሌላ ምክንያት ተመሥርቶ በሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት የተነሳ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ኢትዮጵያዊ፣
    ሀ) ባገኘው የሌላ አገር ዜግነት መብቶች መጠቀም ከጀመረ ወይም፣
    ለ) በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያገኘውን የሌላ አገር ዜግነት ትቶ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ለመቀጠል መምረጡን ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ ዜግነቱን በፈቃዱ እንደተወ ይቆጠራል” ይላል።
    በተለያየ ምክንያት የኢትዮጵያን ዜግነት ትተው የሌላ አገር ዜግነት የወሰዱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟሉ፣ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰው የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን መልሰው ለማግኘት ይችላላሉ። ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ሕጉን ተከትለው፣ የውጪ ዜግነቱን አስረክበውና፣ ማስረከባቸውንም የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከማመልከቻቸው ጋር አያይዘው ለኢትዮጵያ የደህንነት የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ማስረከብ አለባቸው ማለት ነው። የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣንም ጉዳዩን ለኮሚቴ አቅርቦ እስኪያስጸድቅላቸው ድረስ ግን፣ እንደ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በሕግ በተሰጣቸው መብት መሠረት እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖርና ከፖሊቲካ ውጭ በሆነ ማንኛውም የሥራ መስክ ተሰማርተው አገራቸውን ማገልገል ይችላሉ።
    ***************
    የአብይ አህመድ የሕግ አማካሪዎች ሁሉ የውጭ የህግ ተማሪዎች ስለሆኑ ሕገመንግስት፡ መመሪያና ደንቦችን ሁሉ በተረኝነት ስሜት እንደፈለጋቸው የመቀየርም የማሻሻልም የመሰረዝም ሙሉ መብት አላቸው አንዳንዴም አባገዳና ገዳ ካልተጠቀሰ ሞተን እንገኛለን ይላሉ፡ አንድ ትልቅና ሉዓላዊት ሀገር እንደመንደር ዕድርና ዕቁብ ለማስተዳደር መንደፋደፋቸው በጣም ይገርማል፡፡ አንዳንዶች ታሪክና ህግ እስኪያበላሹ በአማካሪነት ቀጥለዋል ሌሎች በቆንፅላ በውጭ ሀገር ቢሮ አማካሪ ሆነው ተረኝነታቸውን ቆርጦ በመቀጠል ከውስጥም ከውጭም የጥፋት ተልዕኮአቸውን ከህወሓት ትግራይ ቡድን በፈጠነ መልኩ የተማሩትን እየተገበሩ ናቸው፡፡
    ** አቶ ባይሳ ዋቆያ ቀድሞ የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣን የነበሩ የዓለም አቀፍ ሕግ ባላሙያ የጃዋር መሀመድን ዜግነት መመልስና በተፋጠነ መልኩ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን “የሜንጫ አብዮት” መሪ በመሆኑ ያደረገው አስተዋፆ ታሳቢ ተደርጎ ህጉ ተጥሶ ለምርጫ እንዲደርስ የሚከተለውን ፅፈዋል” የመጀመርያው፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የውጭ አገር ዜጋ “ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋዖ ያበረከተ” መሆኑ ከታመነበት ምንም እንኳ በሕጉ የተካተቱትን ቅድመ ሁኔታዎችን ባያሟላም በኢትዮጵያ የዜግነት ሕግ አንቀጽ 8 መሠረት አመልክቶ ዜጋ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን መንግሥት እንዳስፈላጊነቱ ለሚያስፈልገው ግለሰብ የሚሠጠው “ችሮታ” እንጂ ሕጋዊ መብት ስላልሆነ የመሳካት ዕድሉ የጠበበ ይመስለኛል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፣ የጣምራ ዜግነትን አስፈላጊነት የኢትዮጵያን ሕዝብ አሳምኖ፣ የዜግነት ሕጉን ማሻሻል ነው፡፡ጄኔቫ፣ ጥር 13 ቀን 2020 ዓ/ም ፡፡
    እንዲህ ተሆኖ ነው የምንሻገረው ከየት ወዴት?

    Reply
  2. Ayele Teklemariam says

    January 22, 2020 07:35 pm at 7:35 pm

    የመናገር መብት እና ገንዘብ ፤ፖለቲካና ዜግነት

    ምንዛሪ በብዛቱ ልክ ልክ እንደ ፏፏቴ ድምጹ የመጉላትና የማነስ ባህርይ እንድሚይሳይ በጆሮንም ሆነ በልብን የመደምጥና ወደ ህሊናም ዘልቆ የይሁንታን ፍቃድና የአሉታን ንፍገት ማስቻያና ማሣጫ መሆኑ ታምኖበት ፤በሰለጠነውና በምእራቡ ዓልም የጥቂት ሰዎች ብዙ ምንዛሪ ጫጫታ የብዙሐኑን ንግግር እንዳያዳፍነው ተብሎ ግለሰቦችና ኩባንያዎች እንዲሁም ቡድኖች ለግለሰብና ለተወሰነ ፓርቲ ሊሰጡት የሚችሉት የገንዘብ መጠን በሕግ የተወሰነና በግልጽም ህዝብ እንዲያውቀው የተመዘገብ ነው።
    ምናልባትም አይነተኛውና ዋናው ተወዳዳሪዎችንና የፖለቲካ ቡድኖችን የሚያአስከሥና ከጨዋታ ውጭ የሚያስደርጉ የፖለቲካ ውድድር የህግ ጥሰቶች የፖለቲካ የውድድሮች የፋይናንስ ህግ ጥሰት ነው፤ የሚዘወተረውም እርሱ ነው ምናልባትም ፖለቲካ ብዙ ስለሚያስወራ ፖለቲከኛም የበለጠ ማውራት ስለሚኖርበትና ማውራትም ስላለበት ያስርባል መሰለኝ ፤የራበው ይበለል የበላ ደግሞ ያወራል፤ ብዙ የበላም ብዙ ይጮሀል ደህም ባልበላ አንጀቱ የሚተነፍሳት ብጠገበ ጩኅት ትዳፈናለች። ባስራዘጠነኛው ክፍለዘመን ዲሞክራሲ የአንድ የሀብታም ምንዛሪ ቢበዛ የሽህ አሊያም የመቶ ደሀ ንብረት ቢያክል ነበርና ባለጸጋ በንብረቱ ቢንጫጫ ደሀም በቁጥሩ ይመዝነው ነበር። በሀያአንደኛው ክፍለዘመን የዓልምን 50% ጠቅላላ ንብረት ከ10% የዓለም ህዝብ በቅጥር ያነሱ ሰዎች በተቆጣጠሩበት ዓለም የሚሊዮኖችን ጩኅት ያንድ ባለጸጋ ንብረት 1% ጭጭ ምጭጭ ልታሰኘው የመቻሏን ያህል ዲሞክራሲን ለማስቀጠል ሲባል በፖለቲካ የውድድር ፋይናንስ ድንባ ህግ የለው ግብግብ ቀጣይና አግባብም ያለው ነው።
    ሌላው የዘመኑ ችግርና ጸጋ ድንበሮች ሁሉ ለካፒታልና ፋይናንስ ውንፊት መሆናቸውና ለዜግነትና ለእልና ብዙም ደንታ የሌላቸው መሆናቸውና ፖለቲካ ባንጻሩ ዛሬም ምናልባትም ነግና ተነገወዲያ ጭምር አካባቢያዊና ሀገራዊ መሆናቸው የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ከቷቸዋል።ምናልባትም የነዚህ ቅራኔዎች ነጸብራቅ ባለፍው 3 ዓምታት የአሜሪካ ፕለቲካ ክሰተት ታይቶአል ብል የተሳሳተ ግምት አይመስለኝም።
    ፖለቲካ በትንሽ ነጸብራቁ ብወረዳ ወይንም በቀብሌ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የለት ተለት ኑሮአቸውን ያለስጋትና ቸግር ለመምራት በሚያስችሏቸው የግዴታ፤ የመብት፤ የግልና የጋራ ግንኙነቶች ላይ መግባብት ላይ ለመድረስ የሚደርግ ድርድር፤ፉክክርና እሰጥ አገባ እንደመሆኑ በየርከኑ የፖለቲካው መጫወቻ ጆግራፊ እየጨመረና ባለግባም ቁጥር እየጨመረ በመጣ ቁጥር መነጋገሪያና መግባቢያ የሚሆኑትም ችግሮችና ሀሳቦች እየገዘፉና በቁጥራቸውም እየቀነሱ ስለሚመጡ ባዓልም ደረጃ የምንስማማባቸው ነጥቦችና የምንጋራቸው እሴቶችም ሆኑ ጋሬጣዎች ዓልማቀፋዊ ገጽታ ያላቸው ብቻ ይሆናሉ።ያ ማለት ዛሬ ያለንበትን የጆግራፊ ክልል ለቀን ሌላ ጆግራፊ ክልል ሄደን መኖር ስንጀምር ያዲሱ መኖሪአ ክልላችን እሴትም ሆነ ፈተና ባለድርሻ እካሎች ስለምንሆን ፖለቲካችንም ከነበርንበቱ ተላቆ ካለንመቱ ይጣውራል የነብሩ ስምስምነቶችንም መቀበል የምንገደደውን ያህል ባዳዲሶቹም እንደራደራለን። ባንጻሩ ግን የአውሮፕላን ጉዞ ባንድ ቀን ከስሜን የዓለም ዋልታ ደቡብ የመሬት ዋልታ ሊያደርሰን ይችላልና ዛሬ ተነስተን ካንዱ ጫፍ ወደሌላው ጫፍ ተጉዘን በተቀመጠውና ባልተቀልነው የአካባቢው ህብረተሰብ ስምስምነት፤ ያካባቢወን ችግርና እሴቶች ጊዜ ወስደን ባልተረዳንበት ዘሎ የፖለቲካው ትእይንት ውስጥ ክታዛቢነት በላቀ መልኩ መዘፈቅ ልክ ትላንትም መጡ ዛሬ እዚህም ሆኑ እዚያ ብርነታቸው እንደማይቀየረው እንዳቶ ብሩ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ ወይም ነገ ባሉንና በሚኖሩን ህግጋት አግባብነት ያለውና የሚኖረው አይመስሉኝም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule