የኢትዮጵያ መንግሥት ባፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ተብሏል
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትሕነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ። መረጃው የአፍሪኮም አዛዥ ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከተመካከሩ በኋላ መውጣቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት ብቻ ሳይሆን አቅጣጫ ጠቋሚም ነው ተብሏል።
“ከባድ ሚስጥራዊ መረጃ፡- ጄ/ል ሳሞራ ዬኑስ በሱዳን 8ሺህ ወታደር እያሰለጠኑ ነው!” በማለት Ethiopian Think Thank Group የተሰኘው ድረገጽ ዛሬ ባስነበበው መሠረት መረጃው የተገኘው ከደኅንነት ሠራተኛ መሆኑን ተናግሯል። ሲቀጥልም “ህወሓቶች ሱዳን ውስጥ ወታደራዊ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ከፍተው ወደ 8ሺህ ሰራዊት በድብቅ እያሰለጠኑ እንደሆነ፣ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖችን መቀሌ ላይ በመሰብሰብ እየሸረቡት ያለው ሤራ፣ መቀሌ ላይ የመሸገው የህወሓት ማፊያ ቡድን በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም አንዳንድ የደቡብ ልሂቃን ከህወሓት ጋር በመመሳጠር በተለይ በወላይታ ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየሠሩት ያለው ሥራ በሪፖርቱ ተካትቷል። ይህ ሪፖርት በአጠቃላይ ሰባት ገፆች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስቱ ገፅ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን” እንደደረሰው ተናግሯል።
ካለፈው ዓመት (2011) ሐምሌ ጀምሮ ስምንት ሺህ የሚገመቱ ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከቅማንት፣ ከኦሮሞና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተውጣጡት ሠልጣኞች ምዕራብ አርማጨሆና ምዕራብ ሁመራ አካባቢ የሱዳን መሬት ላይ በሚገኘው ይዞታ እየሠለጠኑ መሆኑን በሪፖርቱ ተመልክቷል።
በአሁኑ ጊዜ ወታደራዊ ሥልጠና እያካሄዱ መሆናቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ በዋናነት ኦፐሬሽኑን እየመራ ያለው ሳሞራ የኑስ መሆኑን ጠቅሷል፤ ታደሰ ወረደም አብሮት በዚህ ሥራ ላይ እንደተሠማራ በዘገባው ተገልጾዋል።
ይህ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቃዋሚዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ ያለ ኦፐሬሽን መሆኑን የጠቀሰው አፈትላኪው ዘገባ “ደህነት ሀገረ ኤርትራ” (ኤርትራን ማዳን) በሚል አጀንዳ የሚንቀሳቀሱ የኢሳያስ ተቃዋሚዎች ከውጭ አገር በመግባት ከህወሓት አመራሮች ጋር በ18/02/2012ዓም ስብሰባ ማድረጋቸውን ያስረዳል። በስብሰባው ላይ የተገኙትን በስም ዘርዝሮ አስቀምጧል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለዚህ የህወሓት አሸባሪ ተግባር “አንዳንድ የደቡብ ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦች” ከህወሓት ጋር በጥምረት እየሠሩ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፤ አሰፋ ወዳጆ የተባለውን ዋንኛውን አስተባባሪ በስም በመጥቀስ ከህወሓት ጋር እንዴት እየሠራ እንደሆነ ሪፖርቱ ያስረዳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማክሰኞ በሶማሊያ ያልተጠበቀ ጉብኝት ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጄኔራል ስቴፈን ታውንሴንድ በቀጣዩ ቀን ረቡዕ ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር መገናኘታቸው ተዘግቦ ነበር። ጄኔራሉ ሞቃዲሾን በጎበኙበት ጊዜ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ፋርማጆ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን የዕዙ ድረገጽ ዘግቧል።
“አልሸባብና አይሲስ ለአፍሪካ አጋሮቻችን፤ ዩናይትድ ስቴትስ በምሥራቅ አፍሪካ ላይ ላላት ጥቅም አደጋ ናቸው” ያሉት ጄኔራል ታውንሴንድ አሸባሪነትን ለመከላከል አገራቸው “ወሳኝና ብቃት ያለው የሶማሊያ መከላከያ ዓቅም ማሳደግ” የምትሠራበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። “ለጠንካራ መንግሥት ደኅንነትና መረጋጋት ወሳኝ” መሆናቸውን የጠቆሙት ታውንሴንድ ለተግባራዊነቱ “የማያቋርጥ ጥረትና የተቀናጀ ድጋፍ ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም” እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
በቀጣዩ ቀን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከምክትል ኤታማጆር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ጋር የተገናኙት ጄኔራል ታውንሴንድ በነበራቸው ቆይታ በደኅንነት ጉዳዮች፤ በምስራቅ አፍሪቃ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ መረጋጋት ለማስፈን ከኢትዮጵያና ከአፍሪካ ኅብረት ሚሽን ጋር አገራቸው እንዴት ትብብር እንደምትሠራ መምከራቸውን የዕዙ ድረገጽ አስረድቷል።
በውይይቱ ወቅት “ኢትዮጵያ በቀጣናውና በመላው አህጉር ወሳኝና አስፈላጊ የአመራር ሚና የምትጫወት” መሆኗን የጠቀሱት ጄኔራል ታውንሴንድ “አሸባሪነትን ለመመከትና ሰላም ለማስጠበቅ የምታደርገው ጥረት ቀጣናውን ሰላማዊ በማድረግ መርዳቱን” ጠቁመዋል።
በውይይቶቹ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይኖር “በለውጥ ጎዳና ላይ ያለችው ኢትዮጵያ የሕዝቧን መብቶችና ደኅንነት ለማስከበር ከምታደርገው ጥረት አኳያ በቀጣናው መረጋጋት እንዲኖር የምታደርገው ወሳኝነት ያለው ጉዳይ” ነው ብለዋል። በመቀጠልም “እነዚህን ጠቃሚ ሚናዎች በመጫወት ላይ ያለውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ብቃት ለማጠናከር በጋራ በምንሠራው ሁሉ ደስተኞች ነን” ብለዋል።
ይህ በዲፕሎማሲዊ ቋንቋ የታጀበው የከፍተኛ ኃላፊዎቹ ጉብኝት ከተካሄደ ሁለት ቀናት በኋላ ይህ ህወሓት በድብቅ እያሰለጠነ ስላለው ሠራዊት የወጣው መረጃ ጉዳዮች ወዴት እያመሩ እንደሆነ ጠቋሚ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በተለይ አምባሳደሩ ባለፈው ወደ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ሹሞች ጋር መነጋገራቸውን አብረው ይጠቅሳሉ። ጉብኝቱ በተካሄደበት ጊዜ ዜናውን ሦስት ጊዜ የቀያየረው ህወሓት በአሜሪካ በኩል ከፍተኛ ጫና እየተደረገበት ለመሆኑ በቀጣይ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ይህንን የህወሃት አሸባሪነት ተግባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለይም አየር ኃይል በዒላማው ውስጥ ሊያስገባው ይገባል በሚል የሚናገሩ፤ በሱዳን አየር ላይ ለመብረር አሁን ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላት ወዳጅነት እንደማይከለክላት ያስረዳሉ። ሌሎች ደግሞ በዶ/ር ዐቢይ ድጋፍ ወደ ሥልጣን የመጣው የሱዳን የሽግግር መንግሥት ከህወሓት ጋር በመወገን በኢትዮጵያ ላይ ሊያሤር አይችልም፤ ባይሆን ይህ የአሸባሪዎች ሥልጠና በአልበሽር ዘመን ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ወንበዴው ህወሓትና አልበሽር ካላቸው ቅርርብ አኳያ ሁኔታውን አምኖ ለመቀበል የሚያስገድድ ይሆን ነበር ሲሉ ይናገራሉ።
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው የጫትና የመጠጥ ሱሰኛው ጃዋር መሐመድ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ በግፍ 87 ወገኖች ከተጨፈጨፉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባሰሙት ንግግር ላይ “… ገዳይና ሟች፤ አሳዳጅና ተሳዳጅ በጋራ ሊቆሙና አገር ሊያጸኑ፤ ብልጽግናን ሊያረጋግጡ አይችሉም … መንግሥት ህግ የሚፈቅድለትን ለማድረግ ዐቅምም፣ ዝግጁነትም ብቃትም አለው” ማለታቸው ይታወሳል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Dawit says
ጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ:- አሁን አንተ ጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ ምኑ ላይ ነህ? እንደፈለገ የሚነዳውና ማሰብ የተሳነው ቄሬ ተብሎ እንዴት ይፃፋል? እናንተን ነበር በደንብ አድርጎ መግረፍ።አሁንም ይዘገያል እንጂ እይቀርልሃችሁም።መንግስት እናንተ ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት እንጠቁማለን።ፈሪ ሁላ!!
Bertu says
Terrorism Has officially entered Ethiopia thanks to Jawar Mohammed and OLF. Terrorism is an extreme violent act against humanity which is so easy to start but can not be stopped even by those who unleashed it. Burning churches, crucifying believer on the cross, slaughtering Christians on camera are all hallmark of international terrorism imported to Ethiopia by these extremists who are coordinating their efforts with TPLF itself.
Egypt and the Gulf States are the main architects.