• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጃዋር ሰለባዎች ዝርዝር በከፊል!

October 28, 2019 04:16 am by Editor Leave a Comment

ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው የጫትና የመጠጥ ሱሰኛው ጃዋር መሐመድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሃን ዝርዝር የሚከተለው ነው፤ ጃዋርን የምትደግፉ እፈሩ! ኅሊና ካላችሁ ወደምታምኑት አምላክ ንሰሐ ግቡና ተመለሱ፤ ከሌላችሁ ከሱ ያላነሰ ፍርድን በራሳችሁ ወይም በልጆቻችሁ እንደምታገኙ አትጠራጠሩ፤  

አምቦ

በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ በጥይት ከተገደሉት መካከል የ80 ዓመቱ አዛውንት አቶ ሞሮዳ ሞሳ የሚባሉ ይገኙበታል በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። አቶ ሞረዳ ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት ከጸጥታ አስከባሪ ኃይል በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአምቦ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎቸ በጥይት ተመትተዋል።

የአምቦ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ደበበ ፈጠነ፤ “14 ሰዎች በጥይት ተመተው እኛ ጋር መጥተዋል። ሁለቱ ህይታቸው አልፏል። 9 ሰዎች ደግሞ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የተቀሩት ቀላል ህክምና ተደርጎላቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል” በማለት ያስረዳሉ።

አቶ ደበበ ወደ ሆስፒታላቸው የመጡት ሰዎች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ዕድሜያቸውም ከ17-80 እንደሚገመት ተናግረዋል። በዚህም በአምቦ ትናንት 3፤ ዛሬ 2 በድምሩ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል።

ዶዶላ 

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል።  ሐሙስ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል።  ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር።

ምስራቅ ሐረርጌ 

ረቡዕ እና ሐሙስ በምስራቅ ሃረርጌ በነበሩ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 6 መድረሱን ሰምተናል።  በዞኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ዴሬሳ፤ በጉሮ ጉቱ 5 እንዲሁም በሃማሬሳ 1 ሰው መገደሉን ተናግረዋል።

ባለሜንጫውና ቀድሞ የጃዋር ተቃዋሚ የነበረው አፈንዲ ሙተቂ

አቶ አየለ፤ ትናንት 5ቱ ሰዎች የተገደሉት ጉሮ ጉቱ በምትባል ከተማ ወደ ብሄር በተቀየር ግጭት ስለመሆኑ ይናገራሉ። “አንድ ባለሃብት የደህንነት ስጋት ተሰምቶት ሁለት ሰዎችን በጥይት ተኩሶ ገደለ። ከዚያም በቂም በቀል ግለሰቡ እና ሁለት የቤተሰብ አባላቱ ተገደሉ” ሲሉ ሁኔታውን ለቢቢሲ አስረድተው ነበር። 

የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ስለመገደሉ የአወዳይ ከተማ ከንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ሐረር 

በሐረር ከተማ ረቡዕ ዕለት 3 ሰዎች መገደላቸውን ከነዋሪዎች ሰምተናል።

ድሬ ዳዋ

በድሬዳዋ ከተማም ረቡዕ 1 ሰው የተገደለ ሲሆን ዛሬ ደግሞ 4 ሰዎች ተገድለዋል። የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብዱራሃማን አቡበከር ለህክምና ከመጡት ሰዎች መካከል 4ቱ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ባሌ ሮቤ

በባሌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሮቤ ከተማም ባለፉት ሁለት ቀናት ግጭት ተከስቶ በሰው እና በአካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል። ቢቢሲ በዞኑ በተከሰቱት ግጭቶች በሰው እና በአካል ላይ የደረሰውን ጉዳት ከገለልተኛ አካል ለማጣራት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። 

ይህ የሟቾች አሃዝ ከሆስፒታል ምንጮች፣ ከመንግሥት አካላትና ከሟች ቤተሰቦች የተገኘ ሲሆን ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ። መንግሥት በግጭቱ ምክንያት የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል እንደሆነ ግልጽ ባያደርግም፤ ግጭት በተከሰተባቸው ስፍራዎች የመከላከያ ሠራዊት እንዲሰማራ መደረጉን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ዛሬ ከሰዓት አስታውቀዋል። 

የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሰረት በአምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬ ዳዋ እና ሐረር የመከላከያ ሠራዊት እንዲሰማራ መደረጉን ተናግረዋል።

1. ወጣት እሱባለው – ድሬዳዋ ገንደቆሬ ሰፈር፤ (ይህ ወጣት ገና የ8 ወር ጨቅላ ልጅ አባት ነበርም ተብሏል)

2. ደረጄ ሀይሉ (ምስራቅ ሀረርጌ – በሮዳ)

3. ዳመና ሀይሉ (ምስራቅ ሀረርጌ – በሮዳ)

4. አቶ ሞረዳ (አምቦ በራፋቸው ላይ የተገደሉ)

5. ወ/ሮ ወላንሳ ፍቅረ (የአቶ ዳመና ሀይሉ ሚስት – ምስራቅ ሀረርጌ በሮዳ)

6. መስፍን አለማየሁ (ሀረር ከተማ ቤቱ ተቃጥሎ በደቦ ፍርድ ተገድሎ አስከሬኑ የውሀ ቦይ ውስጥ የተጣለ)

7. አምቦ ከተማ ውስጥ ሶስት ወገኖች እንደተገደሉ VOA ዘግቧል።

8. አቶ ገላሁንና ሌሎች ሶስት ኢትዮጵያውያን (ወለቴ – አዲስአበባ አካባቢ በቄሮ የተገደሉ)

9. አቶ አነጋግር ደሴ – ባሌ ዶዶላ

10. አቶ ዝናቡ ጌታሁን – ባሌ ዶዶላ

11. አቶ ግርማ ተስፋዬ – ባሌ ዶዶላ

12. ወጣት ምህረተአብ ደጀኔ – ባሌ ዶዶላ

13. ወጣት እሸቱ ተስፋዬ – ባሌ ዶዶላ

14. አቶ ሃይሉ አስማረ – ባሌ ዶዶላ

15. ሰመር ኑሪ – ናዝሬት

16. ፍጹም ወጋየሁ – ናዝሬት

17. አቢቲ ታምራት – አርሲ ኮፈሌ

18. አቶ ታምራት ጸጋዬ – አርሲ ኮፈሌ – ልጃቸውም የተገደለ

19. አብርሃም ክንዴ – ድሬዳዋ

20. ትዕግስት – ገንደሀራ ናዝሬት

ከላይ በቢቢሲ አማርኛ ከተዘገበው ጋር ይህ ዝርዝር ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰበሰበና ስማቸው እስካሁን የታወቀው ብቻ ነው። ሰበታ አካባቢ ሶስት ጋሞ ኢትዮጵያውያን እንደተገደሉ መረጃ አለ። ደብረ ዘይት ከስድስት በላይ ወጣቶች ተገድለዋል። ቢቢሲ የመንግሥት ምንጮችን ጠቅሶ እስካሁን ህይወታቸው የተቀጠፈው ኢትዮጵያውያን ቁጥር 67 መድረሱን ዘግቧል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

(ፎቶ፤ ከአፈንዲ ፎቶ በስተቀር ሌሎቹ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ በመሆናቸው የሰሞኑ ግድያ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የለም፤ የደረሰውን ጭፍጨፋ ለማሳየት የቀረቡ ናቸው)

Filed Under: News Tagged With: jawar, Left Column, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule