ጃዋር የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙ ሕገወጥ ነው ሲል የዳውድ ኦነግ ከሰሰ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው አንዱ ኦነግ ጃዋር መሐመድ ገለቶማ በሚለው የአውሮጳና የአሜሪካ ስብሰባ ላይ የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙን ኮነነ። ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይጠቀም ትዕዛዝ አዘል ደብዳቤ ለኦፌኮ ጻፈ። በዳውድ ኢብሳ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተብሎ የተመዘገው ፓርቲ ባንዲራዬን ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀመ ነው ሲል መረራ ጉዲና ለሚመራው ኦፌኮ ቅሬታውን አሰምቷል። ከሁለት ቀናት በፊት በተጻፈውና በዳውድ ኢብሳ በተፈረመው ደብዳቤ ጉዳዩ በሚለው ርዕስ ሥር በሕጋዊ መልኩ በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግን ባንዲራ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መልኩ መጠቀሙን ስለማስቆም የሚል ነው። ደብዳቤው ሲያጠናቅቅም ከረር ያለ ማስጠንቀቂያ … [Read more...] about ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት
jawar
እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ?
ሕግ በረጅም ገመድ ያሰረው ጃዋር! ቅድሚያ “ኢትዮጵያዊ ፣ አባ ሜንጫ፣ አክቲቪስት፣ ተንታኝ፣ ፖለቲከኛ፣ አሁን ደግሞ “ሐጂ” ሆንኩ ያለው ጃዋር ማነው ነው? የሚለው ድብልቅልቅ ጉዳይ መመልከት ያሻል። ወይም የተለያዩ ማንነት ያለበት ጥያቄ መመለስ ግድ ነው። ጃዋር ወደ ፖለቲካ ሲመጣ በዳያስፖራ ያሉትን አገር ወዳዶች ለማማለል ፍጹም ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ በንግግሩ ሁሉን አስደምሞ ነበር ብቅ ያለው። ነገሮች መስመር ሲይዙለትና ደጋፊ ሲያገኝ እነዚህኑ ወደ ላይ የሰቀሉትን መሳደብና ኢትዮጵያን ማበሻቀጥ ጀመረ። በወቅቱ ተው ብለው አዛውንቱ የዳያስፖራ ምሁራን መከሩት። ወደላይ እየወጣ ስለነበር ይልቅ እኔን ብትሰሙ ይሻላል አላቸውና አልፏቸው ተስፈነጠረ። በቀጣይ ለኦሮሞን ትግል “አዲስ ትንፋሽ ነኝ” በማለት ራሱን መሪ አድርጎ ሾመ። የቀድሞ የኦሮሞ ታጋዮችን በተለይም ዕንቅፋት ይሆኑብኛል … [Read more...] about እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ?
የጃዋር ቅዠትና የበቀለ የተላላኪነት ፖለቲካ – የለማ ሃዲድ መሳት
አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ተፈተው አሜሪካ እስከገቡ፣ ከአሜሪካም ሜኖሶታ ከጃዋር ጋር ጫጉል ቆይተው እስኪወጡ የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን የሚያውቁ፣ የሚያመልኩትን አምላክ ተግሳጽ መስማት የሚችሉ፣ በዙሪያቸውም ሆነ በሩቅ ባሉ ክብር ያላቸው ፖለቲከኛ እንደነበሩ ስምምነት አለ። ይህ ስምምነት ነበር አቶ በቀለን በኢትዮጵያ ለውጥ ቢፈጠር ሁሉንም አቻችለው ወደ በጎ መንገድ እንዲመሩ ከሚታሰቡት መካከል ቀዳሚው አድርጓቸው የነበረው። የዲሲ ነዋሪው ገመቹ በቀለ ከሜኖሶታ "ተሃድሶ" ይለዋል ተመርቀው ሲወጡ "የአንጎል ቀዶ ጥገና ተድርጎላቸዋል" ባይ ነው። የዘወትር የጎልጉል አስተያየት ሰጪ ገመቹ እንዳብራራው አቶ በቀለ ጃዋር በዝግ ቤት ከሰው ለይቶ ቀዶ ጥገና ካደረጋቸው በኋላ ሙሉ በሙሉ ሌላ የማይታወቁ ሰው ሆኑ። "በቀለ ይፈታ" እያሉ ሲጮሁ የነበሩ ወገኖችን ከነ ባንዲራቸው … [Read more...] about የጃዋር ቅዠትና የበቀለ የተላላኪነት ፖለቲካ – የለማ ሃዲድ መሳት
የኬሪያና የጃዋር ድብቁ ግንኙነትና አዲሱ የቤት ውስጥ እስር
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ በዋስ መፈታታቸው ተሰምቷል። ፖሊስ ለችሎት እንዳስረዳው ወይዘሮዋ የተፈቱት ቀዳሚ ምርመራ እስኪሰማ ድረስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 28 መሰረት ነው። ፋና ችሎቱን ጠቅሶ እንደዘገበው ወይዘሮ ኬሪያ ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ የሚቆዩት በሰርቪስ ማረፊያ ነው። የህግ ማስከበሩ ሲጀመር ሌሎች ሲሸሹ መቀሌ ሆነው እጃቸውን የሰጡት የቀድሞ አፈ ጉባኤ፤ እጃቸውን ከሰጡ በኋላ ክስ ሳይመሰረትባቸው መቆየቱ ይታወሳል። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እንዴት ወደ መቀሌ ሄዱ? አፈጉባዔዋ ወደ መቀሌ የሄዱት ከአዲስ አበባ ተገፍተው መሆኑንን ጉዳይን በወጉ ሲከታተሉ የነበሩ ይናገራሉ። ኬሪያ ሃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ከማስታወቃቸው በፊት ከአቶ ጃዋር ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዲመሠርቱ … [Read more...] about የኬሪያና የጃዋር ድብቁ ግንኙነትና አዲሱ የቤት ውስጥ እስር
ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት። ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል። ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ … [Read more...] about ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
ተከሳሾቹ እነጃዋር “መንግሥት የለም” ብለው የመንግሥት አካል ነጻ እንዲያወጣቸው ተማጸኑ
በወንጀል ተከስሰው በእስር ቤት የሚገኙት ጃዋር ሲራጅ መሐመድ፣ በቀለ ገርባ ዳኮ፣ ሐምዛ አዳነ ታዬ እና ሸምሰዲን ጠሃ መሐመድ ከሰኞ መስከረም 25 ቀን ጀምሮ በሚመሠረተው የአደራ መንግሥት ለመሳተፍ ከእስር እንለቀቅ ብለው ተማጽንዖ አቅርበዋል። ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ልቅም ባለ አማርኛ ከሽነው በጻፉት ደብዳቤ መንግሥታዊ አካል ለሆነው “የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች” ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ በግልባጭ “ለፌዴራል ዐቃቤ ሕግ” እና “ለፌዴራል ወንጀል ምርመራ” ጥያቄያቸውን ልከዋል። ተከሳሾቹ መቀሌ ከመሸገው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድብ ህወሓት እና ከሌሎች ራሳቸውን ተቃዋሚ ፓርቲ ብለው ከሚጠሩ ጋር በመሆን ከመስከረም 25 ጀምሮ የአደራ መንግሥት እንመሠርታለን ብለው በተደጋጋሚ ሲናገሩና ሲሠሩ እንደነበር ይታወቃል። ተከሳሾቹ ያቀረቡት ደብዳቤ ከዚህ በታች ይገኛል፤ ጎልጉል የድረገጽ … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነጃዋር “መንግሥት የለም” ብለው የመንግሥት አካል ነጻ እንዲያወጣቸው ተማጸኑ
ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት እነ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት የክስ ፋይላቸው መቀየሩ ተዘግቦ ነበር። የዚያን ዕለት የቀረበባቸውም ክስ ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት በማድረግ፣ በተለይም በአማራ ብሔር ተወላጆችና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና የትስስር ድረ ገጾችን በመጠቀምና በአካል በመገኘት፣ በተገለጸው አግባብ ባስነሱት የእርስ በርስ ግጭት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የ13 ሰው ሕይወት እንዲያልፍና 48,026,526 ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል፣ በኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የ167 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ፣ 360 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸውና 4,673,031,142 ብር ግምት ያለው ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን በመጥቀስ ነበር ዐቃቤ ሕግ ክሱን … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
በተደጋጋሚ የክስ ቻርጅ እንዳይሰጠው ጥረት ሲያደርግ የነበረው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከግብርአበሮቹ ጋር “ተከሳሽ” የሚለውን መጠሪያ ትላንት ሰኞ መስከረም 11/2013 ተቀብለዋል፤ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በይፋ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በጃዋር መሐመድ እና ሌሎች 23 ተከሳሾች ላይ ክሱን በመሠረተበት ወቅት፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት፤ በውሎው የክስ ሰነዶቹ ለተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲከፋፈል አድርጓል። በመሆኑም እነ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል። ዐቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ ላይ 10 ክሶችን … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
አቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን አርብ መስከረም 8፤ 2013ዓም ነበር። ሆኖም በዚህ ክስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቅበት የመጨረሻው ቀን ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረው ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት ጃዋርና ሲራጅ መሐመድና ግብረአበሮቹ በ10 ተደራራቢ ክሶች ፋይል እንደከፈተባቸውና የክስ ቻርጁም መስከረም 11፤2013ዓም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደሚደርሳቸው አስታውቋል። ዐቃቤ ሕግ ያወጣው ጽሁፍ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድ፤አቶ በቀለ ገርባ፤አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ … [Read more...] about ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ። ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ። “ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል። “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር … [Read more...] about እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ