• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”

November 17, 2020 03:36 am by Editor 5 Comments

በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት።

ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል።

ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ እንዴትና ለምን ገጠሙ?

ጃዋር እስር ቤት ሆኖ “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” ሲል እርግጥም ሰሚን ያስደነግጣል። ጃዋርና የአንድነት ኃይሎች ምን አገናኛቸው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ጃዋር ብልጽግና ፓርቲ መቋቋሙ እጅግ እንዳንገበገበው ሲናገር አንድነትን በመቃወም መሆኑን በራሱ አገላለጽ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች በተደጋጋሚ አረጋግጧል። የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ገብቶ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳልነበረው ባንደበቱ በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ጃዋር፣ በድንገት ኦፌኮን ሲቀላቀል ፍላጎቱን የሚያሳካበት ካርታና ስልት ማዘጋጀቱ አይገርምም። ፖለቲካ ውስጥ ሲገባ ዓላማው ሥልጣን ነውና “የአንድነት ኃይሎች” ከሚላቸው ጋር ድር አደራ።

በአንድ ወቅት “አስክንድር ነጋ ምን እንደሚፈልግ አውቃለሁ” ሲል እንዳጫወታቸው፣ ይሁን እንጂ ዝርዝር ጉዳዩን እንዳላብራራላቸው የሚናገሩት ሰው፣ ጃዋርን እስር ቤት ሊጠይቁት ሄደው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” ሲላቸው በርካታ ጉዳዮች ተሳስመውላቸዋል።

ኢትዮጵያዊ እምነት ካላቸው የኦሮሞ ተወላጆች ድጋፍ የሌለው ጃዋር፣ እነዚህንና ቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀልብ ለመሳብ ሲል በገሃድ ወጥቶ “ኢትዮጵያ” ብሎ ቢሰብክ ጽንፍ የያዙትና ጽንፍ ያስረገጣቸው ይነሱበታል። በመሆኑም በገሃድ “ኦሮሞ ፈርስት” እያለ በጓሮ ከአንድነት ኃይሉ ጋር ገጠመ። ተናብበውም መሥራት ጀመሩ። ምርጫ ላይ እንዴት እንደሚያሸንፍ አብሯቸው ሰጥቶ በመቀበል መርህ ዶለተ። ይህ መስመር አሁን የሚወተረተሩትንና ቀደም ሲል የተገፉትን ፖለቲከኞች ያጡትን ምኞት አጋለ። እናም አንድ ሆነው ዕቅዳቸውን ለመተግበር ተነሱ።

ምርጫ ወይም ሞት

ቀደም ብለው በኢትዮጵያ ምርጫ እንደማያስፈልግ ሲወተውቱ የነበሩ ታጠፉ። ትህነግ የዚህ “ምርጫ ይካሄድ” ዘመቻ ፊታውራሪ በመሆን መንግሥት ለመሆን የተዶለተውን ዕቅድ በገሃድ ያቀጣጥል ገባ። ጃዋር “ምርጫ ወይም ሞት” በሚል ዙሩን አከረረ። በዘጠና ሰባቱ ምርጫ ዕርቃኑን የቀረው ልደቱ “ሕግ ተቀይሮም ቢሆን ምርጫ መደረግ የለበትም” በሚል ሽንጡን ገትሮ ሲሟገት እንዳልነበር አዲስ ካባ ለብሶ ተነሳ። ልክ እንደ ጃዋር ሁሉ በታላቅ ወኔ “ምርጫ ወይም ሞት” አለ። አዲስ ኅብረት ከፈጠሩት እነ ይልቃል ጌትነት ጋር ሆነው የምርጫ ይደረግ ቅስቀሳቸውን አማራ ክልል ውስጥ ውስጡንና በገሃድ አጧጧፉ።

“ከምርጫ ወይም ሞት” ቅስቀሳ ጎን ለጎን ምርጫውን እንዴት እንደሚያሸንፉ ሒሳብ ተሰራ። በስሌቱ መሠረት ልደቱ አያሌው፣ ይልቃል ጌትነትና ለዛሬ ስማቸው የማይጠቀስ ሰዎች በአማራ ብልጽግና አባላትን በመጨረሻ ሰዓት የማስኮብለል ሥራ በምልምል ወኪሎች አማካይነት ተጀመረ።

በኦሮሚያ ጃዋርና አንዳንድ ታዋቂ ናቸው የሚባሉ አካላት፣ ሃይማኖት አካባቢ ባሉ ሰፊ ተከታይ ባላቸው ጥቂት ሰዎች አማካይነት የኦሮሚያ ብልጽግና ሰዎች ባለቀ ሰዓት እንዲከዱ ውስወሳው ተፋፋመ። ከትህነግ በኩል አስተማማኝ ሰላሳ አምስት የፓርላማ ድምጽ ስላለ መንግሥት ለመመሥረት ይቻል ዘንድ በተሠራ ስሌት ኦሮሚያና አማራ ክልል በቂ ድምጽ በማስፈለጉ በክልሉ ያሉትን የገዢ ፓርቲ ዕጩዎች ከምርጫ በኋላ ለማስኮበለል በጀት ተመደበ። የሚያማልል በጀት ተመድቦ ተሠራ።

ይህ መስመር የአብን አመራሮችና ደጋፊዎች ሙሉ በሙሉ አውቀው ይሁን አይሁን ባይታወቅም ምርጫው ላይ አብን የሚያገኘውን ድምጽ ይዞ እንዲቀላቀል በምርጫው ወቅት ሰፊ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግለት እነ ልደቱና ይልቃል የቤት ሥራቸውን አጧጧፉ።

ይህ ሁሉ ሩጫ ተግባራዊ እንዲሆን በገሃድ በሚዲያዎች በሚደረግ ዘመቻ ተራገበ። ለዚህ ሃሳብ ማራመጃ የሚሆኑ እየተጋበዙ ዘመቻውን እንዲያግሉ ተደረገ። እነ ልደቱ የቀድሞውን ኃጢያታቸውን አራግፈው በታላቅ የወሳኝነት ስሜት ዘመቻውን አቅጣጫ በሚያሲያዝ መልኩ በፈለጉት ሚዲያዎች ይረጩ ጀመር። የገባውም ሆነ ያልገባው ሚዲያ ለሳንቲም ለቀማ እንደ ሕንድ ፊልም ሬክላም እየለጠፈ ሤራውን ያራግብ ገባ። ኮሮና ምክንያት ሆኖ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫ ማካሄድ እንደማይችሉ ይፋ ሲያደርጉ ዘመቻውና ዕቅዱ ሁሉ በቅጽበት ቆፈን ያዘው። ሕግ ተጠቅሶ ምርጫው ሲራዘም ከጩኸቱ ጎን ለጎን አዲስ ዕቅድ ተሰራ። የአንድነት ኃይሉና ጃዋር በትህነግ አንደርዳሪነትና ቆስቋሽነት መንግሥት እንደማይኖር ቀነ ቀጠሮ ተቀምጦ ዜና ሆነ። ሳንቲም ለቃሚ ሚዲያዎች በተለይ በዳያስፖራ ያሉ አሁንም “መንግሥት የለም” እያሉ ሬክላም በመለጠፍ አራገቡ።

መንግሥት በቀነ ገደብ እንደማይኖር ይፋ መሆኑና – ኩዴታው

አሁን ባልደራስ የሚመዘዝበት ጊዜ ሆነ። በውጭ አገር የቀድሞ የህወሃት ቃል አቀባይ የአሁኑ የባልደራስ ምክትል ኤርሚያስ ለገሰ የተካተተበት ባልደራስ የእስክንድርን ስም በመጠቀም ለአዲሱ ዕቅድ ግንባር ሆነ። እነ ጃዋር ከመስከረም ሃያ አምስት በኋላ መንግሥት የለም እያሉ ባለ በሌለ ኃይላቸው ሚዲያዎቻቸውን ተጠቅመው ሲቀሰቅሱና ሲያስተባበሩ እነ ልደቱ ጎን ለጎን የሽግግር መንግሥት ሰነድ አዘጋጁ።

ይልቃል ጌትነት የፓርቲ መዋቅር በማዘጋጀት ከልደቱ ጋር ሆነው በመዋሃድ፣ በትብብርና አብሮ በመሥራት ስም ባልደራስን ማገዝ ጀመሩ። ባልደራስ በመዋቅር ዝርጋታና በድርጅት ቅርጽ ደካማ በመሆኑ እስክንድር በቀጣይ አዲስ አበባን እንዲመራ በተዘጋጀው ዕቅድ መሠረት ባልደራስ ድርጅታዊ መዋቅሩ እየተበጀ በዚያው መንግሥት የሚወገድበትን ስልት እንዴት እንደሚረዳ ዋናዎቹ በዘረጉት ማዕቀፍ ውስጥ ሰመጠ።

በዕገዛ በተዘጋጀው መዋቅር መሰረት ባልደራስ እንዲፈጽም የታዘዘውን እቅድ እንዴት እንደሚተገብር ተማረ፤ ተረዳና ለመተግበር ተስማማ። ጃዋር “እስክንድር ምን እንደሚፈልግ አውቃለሁ፤ የእርሱ ጉዳይ አያሳስብም” ሲል አስቀድሞ የገለጸው ሃቅ ዕውን ሆነ። በሽግግር መንግሥቱ እስክንድር ከንቲባ፣ ልደቱና … እንደየ ተሳትፏቸው ኃላፊነት ወጥቶላቸው የሽግግር መንግሥቱ ጊዜያዊ “ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋር መሃመድን” አጅበው ብቅ ሊሉ ተማማሉ።

የማስፈጸሚያ መንገዶች

1 – ያሲን ጁማ የተባለ ኬኒያዊ ጋዜጠኛ
ያሲንና ጃዋር

ያሲን ጁማን እዚህ ላይ ማንሳት አግባብ ይሆናል። ያሲን ጃዋር ቤት በጀት ተመድቦለት የሚያከናውነው ተግባር ጃዋር በትረመንግሥቱን ሲጨብጥና ጊዜያዊ የኢትዮጵያ መሪ ሲሆን ያሲን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ወዲያውኑ ቀና ሪፖርት እንዲያቀርቡ፣ ታላላቅ ሚዲያዎች በይሁንታ ሪፖርታቸው ጃዋርን እንዲያሞግሱና ለዓለም እንዲያቀርቡ፣ የጃዋርን ሥልጣን ዓለም አሜን ብሎ እንዲቀበል ጫና መፍጠር በሚችሉ ሚዲያዎች ዘጋቢ ፊልሞች እንዲተላለፉ … መሥራት ነበር። እሱ ሲያዝ በጃዋር መኖሪያ ቤት በርካታ ጃዋርን ለዓለም የሚያስተዋውቁና ለየሚዲያዎቹ የሚበተኑ የእንግሊዝኛ ተራኪ ክሊፖች መገኘታቸውን ልብ ይሏል።

2 – ሚዲያዎች

በትህነግና በነጃዋር በሚመሩት በዳያስፖራ ባሉት ሚዲያዎች በቀን ከአንድ ጊዜ በላይ “መንግሥት የለም” በማለት ፕሮፓጋንዳውን ከሚያጦዙት በተጨማሪ በየብሔረሰቡ ቋንቋ የሚተላለፉ በርካታ የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች በአገር ውስጥ እንዲከፈቱ ዝግጅቱ ተጠናቋል። ከዚህም በላይ አስፈላጊ አጫጭር (የቴክስት) መልዕክቶችን ለማድረስ ይቻል ዘንድ ከቴሌ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ሰነድ ለጃዋር እንዲሰጥ ተደርጓል። በሥራ ላይ ያሉት ወይ አክቲቭ የሆኑት ሲም ካርዶች ላይ ትኩስ ዜና በተለቀቀ ቁጥር ወዲያውኑ እንዲደርሳቸው የጃዋር የአይቲ ባለሙያዎች ዝግጅት አጠናቀው ነበር። ከዚህ በተጨማሪም አልጃዚራ በቀን የአራት ሰዓት ስርጭት በኦሮሚኛና በአማርኛ እንዲያስተላልፍ በቂ ዝግጅት ተደርጓል።

3 – ጸጥታ

ትህነግ የደኅንነቱን፣ የመከላከያውንና የፖሊስ ኃይሉን ዳግም በመቀበል መልሶ የቀድሞውን ሠንሠለት በማደስ አገር እንዲያረጋጋ ኃላፊነት እንዲወስድ ተደርጓል። ለዚህም ነበር የትህነግ ቀላጤዎች “ዐቢይ በቅርቡ ለፍርድ ይቀርባል” እያሉ ሲያስተጋቡ የነበሩት። በጸጥታው ዘርፍ የኦነግ ሸኔ ወታደሮች የጎላ ሚና እንዲኖራቸውን ዳውድ ኢብሳ መከላከያ ሚኒስትር እንዲሆኑ ይደረጋል። በሒደት የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና ሰፊው ክፍል እንደቀድሞው ይበተናል። የሚታሰረው እንዲታሰር ይደረጋል። ሰሞኑንን መከላከያ ሠራዊት ላይ የተወሰደው ጥቃትና የተፈጸመው ጥቃት ይህን ያሳያል።

4 – አፈጻጸም

ከላይ የተዘረዘሩት ዝግጅቶች እየተደረጉ ጎን ለጎን ሲሸረብ የነበረው ዕቅዱ እንዴት እንደሚተገበር ነበር። ለዚህም የተመረጠው ስልት እምቢተኛነትን በሕዝቡ ውስጥ ለማስረጽ የሚዲያ ዘመቻ ማካሄድ። ደግሞ ደግሞ መንግሥት ከተቀመጠለት ቀን ውጪ ዋጋ እንደሌለውና በአገሪቱ መንግሥት እንደሌለ የማሳመን ሥራ መሥራት ሲሆን ዕቅዱ መጠናቀቂያው ሲቃረብ የቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ የአገር መከላከያ ሠራዊት መንግሥትን እንዲከዳ፣ እንዲነጠል፣ እንዳይታዘዝ ሲሆን በሌላ ቋንቋ እነሱን እንዲታዘዝ ነበር። ይህን ትህነግ መከላከያ ውስጥ ባሉት አባላቱ ቀድሞ የሠራው ሥራ ነበር።

ዋናው የዕቅዱ መተግበሪያ አንኳር ሃሳብ አመጽ ነበር። አመጹ በኦሮሚያና አማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ እንዲቀጣጠልና ሁኔታውን ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ ማድረግ። በደቡብ ኢትዮጵያ የክልልነት ጥያቄ የጠየቁ የአካባቢውን አስተዳደር እንዲረከቡ ማድረግ። ልክ በወላይታ እንደሆነው።

እነጃዋር ያዘጋጁት ኃይል ቀኑ ሲደርስ ወይም ፊሽካው ሲነፋ ወደ አዲስ አበባ እንዲተም። አዲስ አበባ የገባና የመሸገው ኃይልም የተሰጠውን የቤት ሥራ እንዲወጣ። እዚህ ላይ ባልደራስ ታላቁን ሚና እንዲጫወት፤ በድጋፍ በተዘረጋው መዋቅሩ አማካይነት የተሰጠውን “ተነሱ፣ ሊያርዷችሁ መጡ” በሚል ሕዝብ ራሱን ለመከላከል በሚል በቀረበለት ቁሳቁስ አጠገቡ ባለው ወገኑ ላይ እርምጃ እንዲወስድ። በሥልጣን ጥም ሰክረው በነደፉት ዕቅድ ወገን እርስ በርስ ሲጨፋጨፍና የርስ በርስ ግጭቱ እየተዛመተ አገሪቱን ሲወር በተዘጋጀው የሚዲያ መስመር የሽግግሩን ጊዜ ማወጅ።

የጎልጉል ዘጋቢ የኦሮምኛ ሙዚቃ ተጫዋች የነበረው ሃጫሉ ሁንዴሳ ድንገት መገደሉ እንደተሰማ ባደረገው ቅኝትና የተለያዩ ነዋሪዎችን አነጋግሮ እንዳረጋገጠው የባልደራስ አባላት የሆኑ “መጡላችሁ፣ ተነሱ፣ ሊያርዷችሁ ነው…” እያሉ ቤት ለቤት ይቀሰቅሱ እንደነበር ተረድቷል። ለዚሁ የሚረዳ ቁሳቁስ የሚያድሉም ነበሩ።

ሃጫሉ ሁንዴሳ

ከድርጊቱ በኋላ ይፋ እንደሆነውና ከሃጫሉ ቤተሰቦች አንደበት እንደተሰማው አርቲስቱ ከመንግሥት ወገን ጠላት የለውም። ይህ የለውጥ አርበኛ በገሃድ ትህነግን መቃወሙና ከለውጥ በኋላ የኦሮሞ ድርጅቶች ከትህነግ ጋር የመሠረቱትን አዲስ ፍቅር እሹሩሩ “ክህደት” እንደሆነ ደጋግሞ መግለጹ ጥርስ እንዲነከስበት ቢያደርግም በዋናነት በኦሮሚያ ረብሻ ለማስነሳት ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል። አርቲስቱ እንዴት እንደተገደለ ማብራራት የዚህ ሪፖርት ዓላማ ባለመሆኑ ግድያውን ተከትሎ የተፈጸሙት ሁነቶች እንዴት ለጃዋር የጠቅላይ ሚኒስትርነት፣ ለእስክንድር ከንቲባነት፣ ለዳውድ ኢብሳ መከላከያ ሚኒስትርነት፣ ለእነ ልደቱ ሚኒስትርነት፣ ለትህነግ ዳግም ወደ ሥልጣን መመለስ እንደተጠቀሙበት ማሳየቱ አግባብ ይሆናል።

አስከሬን

ቤተሰቡ አስከሬን ይዞ ወደ አምቦ ሲሄድ ከልክሎና ነጥቆ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ የተቀመጠበት ሥፍራ መወሰዱ፣ አስከሬኑ ከቤተሰብ ፈቃድ ውጪ አስር ቀን አዲስ አበባ ተቀምጦ ሰፊው ኦሮሞ ከተሰባሰበ በኋላ ቀብር እንዲፈጸም “ወዲያው ዕቅድ” መውጣቱ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁሉም ነገር በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍ መደረጉ፣ መንግሥት የለም የሚለው አስተምሮ በሰፊው ሲናኝ መንግሥት በተመሳሳይ የማያወላዳ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳስብ ነበር።

በዚሁ የቀጥታ ስርጭትና ተውኔት በየአካባቢው ተልዕኮ የተሰጣቸው ሕዝብ አረዱ፣ ንብረት አወደሙ፣ ዘረፋ አካሄዱ። ይህ ያልገባውና የምናብ ከንቲባነትን የተረከበው ባልደራስ ይህ ሁሉ ሲሆን አልገባውም። ይህ ሁሉ ሲሆን ከነማን ጋር እንደተሰለፈ እንዳያይ በክህደት የተካነው ልደቱ አያሌው አጥልቶበታል። እናም ዕቅዱ ይሳካ ዘንድ “መጡላችሁ” እያለ የትርምስ ነዳጁን ያርከፈክፋል።

የአንድነት ኃይሉ

የአንድነት ኃይሉ ልክ ኦሮሚያ ላይ ሻሸመኔ እንደሆነው ትርምሱን ያቀጣጥለዋል ተብሎ መተማመን ላይ ቢደረስም እንደታሰበው ባለመሆኑና መንግሥት ባስቸኳይ እርምጃ ወስዶ በመቆጣጠሩ፣ እነ ጃዋርም ወደ ማረፊያ መወሰዳቸው፣ ደኅነንቱ መዋቅሩን ይረዳውና ይከታተለው ስለነበር ባስቸኳይ እንዲመክን ማድረጉ ዛሬ ጃዋርን ሃዘን ውስጥ ጥሎታል።

በቅርቡ በዚሁ ሚዲያችን “የአማራ ክልል ሰላም መሆን የታሰበውን መንግሥት በኃይል የመናድ ዕቅድ አከሸፈው” በሚል ትህነግ መገምገሙን ስናስብ፣ ተቃዋሚ ነን የሚለው የአንድነት ኃይሉ አማራ ክልል በመንግሥት ላይ እንዲነሳ የማድረግ አቅም እንዳለው ሙሉ በሙሉ አምኖ የከንቲባነትን ዕድልን በገጸ በረከትነት ያቀረበው የጃዋር ዕቅድ ተነፈሰ።

ዛሬ እንኳን አማራው ኦሮሚያ ላይ ጃዋር ኪሣራ ውስጥ እንደሆነ ያስባል። በስሜት ተጀምሮ ያደገው የበቀለ ገርባና የጃዋር የትግል አጋርነት ዛሬ በማረሚያ ቤት ወደ መናረት መቀየሩ እየተሰማ ባለበት ወቅት ጃዋር የአንድነት ኃይሉ እንደከዳው አውቆም ይሁን በድንገት አምልጦት መናገሩ ሊሰመርበት እንደሚገባ መረጃውን ያቀበሉን ያምናሉ።

በስምና በዝና፣ ትህነግ በሠራባቸው ግፍ ምንክያት ብቻ የጀገኑትን ያለማወላዳት ልክ አምላክ እንደቀባቸው አድርጎ መውሰድ ኢትዮጵያን ዋጋ እያስከፈላት ባለበት በአሁኑ ወቅት ይህ የጃዋር ጸጸትና ቁጭት እያደር በርካታ ጉድ ይዞ እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም። “የዲቃላ ፖለቲካ” እስከማራመድ የደረሰው በቀለ ገርባስ ምን ይል ይሆን? በኦሮሚያ አብዛኛው ቁጥር የሆነውን የተዋለደ ሕዝብ አሸማቅቆ መንግሥት ለመሆን ባልደራስን የተቆናጠጠው የጃዋር ስልት ስንቱን ከሃዲድ እንደገፋና ከጀርባው ያስከተለው ጠባሳ ቀጣዩ አጀንዳ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ሌላውን ሳይጨምር 152 ሚሊዮን ብር በጥሬ አካውንቱ ውስጥ የተያዘበት ጃዋር አገር ቤት በዚህ መልኩ የአንድነት ኃይሉን ሲጋልብ፣ ከውጪስ እነማን ይሆን የሚጋልቡት?


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: eskinder, jawar, jawar massacre, lidetu ayalew, operation dismantle tplf, tplf, yilikal

Reader Interactions

Comments

  1. የዓምደፅዮን ልጅ says

    November 17, 2020 03:31 pm at 3:31 pm

    ዓቢይ ስንት ከፈለህ? የምር ግን ይችን ዓይነት አጻጻፍ ከትሕነግ ነው አይደል የተማርካት።
    በርግጥ ዐማራ የእግዚአብሔር ምስጢራዊ ሕዝብ መሆኑን ከG20 ሀገራት በቀር የሚያውቀው ስለሌለ ብዙዎች እንዳንተ ሊያጠፉት ይቋምጣሉ። ግን ምንም አይችሉም። አትችልምም።
    ና በርታ ተቀጣሪ አቃጣሪው።

    Reply
  2. ቦምቡ ፍቅርሽ says

    November 18, 2020 05:49 pm at 5:49 pm

    ውድ የጎልጉል ድሕረ ገፅ አታሚ !

    ከዚህ በላይ በረጅሙ የቀረበውን ሐተታ አነበብኩት ! ምንም እንኳን ዋናው ጉዳይ የሚያጠነጥነው በ አቶ ጃዋር የፖለቲካ አካሔድና ክሽፈት ዙሪ ቢሆንም በተያያዥ ሌሎችንም ተዋንያን ያካተተ ሆኖ ስላገኘሁት .. በተለይ ደሞ ሰላ ባልደራስና መሪው እስክንድር ነጋ የተጠቀሱት ጉዳዮች እጅግ የተለጠጡ የተሳሳቱና ሐሰተኛ ውንጀላን ይዞ የቀረበ መስሎ አግኝቸዋለሁ. በዕገዛ በተዘጋጀው መዋቅር ባልደራስ…….ከሚለው ጀምሮ እስከ እስክንድር ምን እንደሚፈልግ አውቀዋለሁ …..የእርሱ ጉዳይ አያሳስብም ሲል አስቀድሞ የገለፀው ሀቅ ሆነ የሚለው የትንታኔ ክፍል ጀዋርን ተጠቅሞ እስክንድርን በሀስት ለመወንጀል የቀረበ አሳፋሪ ክስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ. በመጀመሪያ እስክንድር ምንም እንኳን የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቢያነሳም እንደመፍትሔ የቀረበው ጉዳይ ግን የባለሙያተኞች ወይም የምሑራን ተሳትፎን ያካተተ እንጂ እራሱን ወይም ድርጅቱን በቀጥታ ተሳታፊ ለማድረግ እንዳልነበረ መረሳት የለበትም. ስለዚህም እንደሌሎቹ የሥልጣን ጥመኛ እንዳልነበረና በዚህም ምክንያት በነጃዋር የሥልጣን ክፍፍል ቀመር ውስጥ ሊመደብ ሰለማይችል በጃዋር ለሚመራው ወጥመድ አይመጥንም ወይም አይመችም ማለት ነው… ከዚህም በተጨማሪ እስክንድርን በፎቶ ከ በቀለ ገርባ ጋር ለማቅረብ ተሞክሯል ያም ሸር የትሞላበት ሙከራ መሆኑን ያሳያል.›.

    በአጠቃላይ አሁን ከአለንበት ወሳኝ ወያኔን የማስወገድ ጦርነት ጊዜም ጋር አብሮ የማይሔድ ትኩረት የሚበትን ከፋፋይ ሊሆን የሚችል ሐተታ ማቅረቡ በራሱ የሚይስተዛዝብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ.

    ድል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት
    ከአክብሮት ጋር

    Reply
  3. Meron Simeneh says

    November 19, 2020 05:17 am at 5:17 am

    የመጨረሻ ቀጣፊ ስም አጥፊ ቆሻሻ ሰው እንደ እዚህ አይነት ፅሁፍ የፃፈው አጭበርባሪ ሌባ ነው! ህፃን ልጅ ቢያነበው ይስቃል እንኳን እኛ! ማፈሪያ ውርደታም! እስክንድርን ለእንደዚህ የበከተ ተግባራችሁ ተባባሪ ለማስመሰል የምትሄዱበት መንገድ የትም አያደርሳችሁም! እውነት ነፃ ታወጣዋለች! ጸሃፊው ቅሌታም ነህ!

    Reply
  4. Mእስፊን says

    November 19, 2020 03:58 pm at 3:58 pm

    ወይ ግዜ ! ወይ ዘመን ! ጎልጉል እናንተስ እንደው መዋሸትም አትችሉ !! ጃዋርን ከ እስክንድር ጋር አጋር ብላችሁ ታቀርባላችሁ? አይ አድርባይነት ! ይህች ቀን ታልፋለች የውሽት እናት ሆናችሃልና ድስ ይበላችሁ !!
    ይህ ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን መወገዱ ተጀምሮአልና የእናንተም ውሸት እንዲሁ ተኖ ይጠፋል ፤ ከልቤ አዝኜባችኋለሁ!!
    የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወያኔና ጃዋር እድሜያችሁን ያሳጥረው።
    ሁለተኛ ይህንን ድህረገጽ ላለማየት ወስኜአለሁ

    መሰፍን

    Reply
  5. Berhan Kirubel says

    November 25, 2020 12:22 am at 12:22 am

    ትንሽ ሽሮ ወደአሻሮ ጠጋ አይነት ወሬ ይመስላል:: ጃዋርና ህወሀት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የማይጎነጉኑት ተንኮል እንደሌለ የታወቀ ሲሆን ተቀናብሮው ግን fact ሳይሆን fiction ነው ታሪኩ:: ልደቱና ጌትነት ምላስ እንጂ እንደ ጃዋር ፀረ ኢትዮጵያ አይደሉም:: ስለዚህ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ውስጥ ስልጣን ግን ይመኛሉ:: ጃዋርና ወያኔ የሚፈልጉት የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት ነው የሚጠሉት:: ስለዚህ በሀጫሉ ሞት ቄሮን አሰልፎ ቤተመንግስት ሊገባ ነበር ፕላኑ ግን ሁሉም ሰላም በሀገሪትዋ እስኪሰፍን ድረስ በእስር ቤት መቀመጣቸው ተገቢና ለዝብም ደህንነት አስፈላጊ ነው:: ልደቱ አዋቂና ፓለቲካ የሚያውቅ መስሎ ቢታይም ግን ችግር እለበት እሱም ሰዎችን የመያዝና influence የማድረግ ችሎታ ስለሌለው መቼም ቢሆን መንገዱን ካልቀየረ ፈቀቅ አይልም ሀሳቡ : ግን ከሀዲ አይደለም ብቻ የዶር ብርሀኑ ግሩፕ ያደርጉት character assasination ተደርጎበታል:; ኢንጅነር ጌትነት ነው የሚሉት ignorant ሰው ነው ትእቢት እንጂ ፓለቲከኛ አይደለም:: ለማንኛውም ሀገር እናስቀድምና ሌላውን በሁዋላ ታቦኩታላችሁ:;

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule