ስሙ የክህደት መጠሪያ ሆነ እንጂ የስሙ ትርጉም ግሩም ነው። ይሁዳ የሚለው ቃል በእብራይስጥም “ይሁዳ” ማለት ነው፤ “ያዳ” ነው ሥርወ ቃሉ ይላሉ የሙያው ባለቤቶች። ይህ ደግሞ ትርጉሙ “ማመስገን” ማለት ነው። በግሪክም ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው - “የተመሰገነ”፣ “ምስጉን” ማለት ነው። “የአስቆሮቱ” የሚለው ቃል ደግሞ የክፋት መጠሪያ አይደለም። በተለምዶ “የአስቆሮቱ ይሁዳ” በማለት ከሃዲዎችን ስንጠራቸው “አስቆሮቱ” የይሁዳ የክፋት ማዕረግ ይመስለናል። ሊቃውንቱ እንደሚሉን ከሆነ ትርጉሙ “የኬሪዮት ሰው” ወይም “የአራዳ ልጅ” እንደ ማለት ነው ይላሉ። ስለዚህ በከሃዲነቱ ባናውቀው ኖሮ “ተመስገን ያራዳ ልጅ” ብለን እንጠራው ነበር። ስሙ ግን ከግብሩ ፍጹም የራቀ ነው፤ እንዲያውም ተጻራሪ። ይሁዳ ከሃዲ ብቻ አይደለም፤ ማሳካት የሚፈልገው ዓላማ ያለውና የሚያደርገውን … [Read more...] about የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
lidetu ayalew
ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
“አማራውም ሆነ አፋሩ ምንም ዓይነት የኅልውና አደጋ አላጋጠመውም፤ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም በትህነግ የደረሰበት ችግር የለም፤ አማራውም ሆነ አፋሩ በትህነግ በጅምላ አልተጨፈጨፈም፤ ማይካድራ፣ ጭና፣ አጋምሳ፣ ጋሊኮማ፣ ወዘተ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው እንጂ በዲሲፒሊን የታነጸው ትህነግ እንዲህ ዓይነት ግፍ አይፈጽምም፣ በአጠቃላይ “ሒሳብ እናወራርድብሃለን” የተባለው የአማራው ሕዝብ በትህነግ ምንም ግፍ አልደረሰበትም፤ ወልቃይት የምዕራብ ትግራይ አካል ነው፣ ራያም የትግራይ ነው፤ ወዘተ። ስለዚህ ትህነግ ሳትሞት በሽግግር መንግሥት ምሥረታ የአፍ ለአፍ ትንፋሽ እንስጣትና እንታደጋት”።ልደቱ አያሌው ትህነግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሲገባ ለመታደግ ከሚረባረቡት “ቅምጥ” ቡድኖች መካከል በቀዳሚነት የሚሰለፈው ልደቱ አያሌው ነው። ከእርሱ ሌላ የቀድሞ የትህነግ … [Read more...] about ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወቱን አሀዱ ብሎ የጀመረው 1983ዓ.ም. ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የከተማዋን ወጣቶች የማደራጀት ስራ ላይ ከተሰማሩ ወጣቶች አንዱ ሆኖ ነው። በዚያ ወቅት ወጣቱ ልደቱ ለወያኔ መንግስት የመወገን ጫና በነበረበት የወጣት ማህበር ምስረታ ሂደት ንቁ ተዋናይ ነበረ። በመሆኑም የማህበሩ ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎት እንደነበረው በወቅቱ አብረውት የነበሩ የመሰከሩት ነገር ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በይፋ ሲመሰረት ወጣቱን በማደራጀት ምንም ተሳትፎ ያልነበረው የዳዊት ዮሃንስ (አፈጉባዔ የነበረ) ሚስት ወንድም የሆነው ወጣት ታጠቅ ካሳ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ይሄኔ ነው እንግድህ የልደቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋም እጥፋት የተጀመረው። የታጠቅን በሊቀመንበርነት መመረጥ አሚን ብሎ መቀበል አልፈለገም። … [Read more...] about ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት። ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል። ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ … [Read more...] about ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
ልደቱ የ98 ምርጫ ወቅት ከህወሓት ደኅንነት ሽጉጥ መቀበሉን ለፍርድ ቤት አመነ
ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው በህክምና ምክንያት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ፥ መርማሪ ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዷል። በምስራቅ ሸዋ ዞን የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ በቀረቡት አቶ ለደቱ አያሌው ላይ መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ተጨማሪ 14 ቀናት ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን የምርመራ ስራዎች ገልጿል። አቶ ልደቱ እጅ ላይ የተገኙ ሁለት ሽጉጦች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የተላላኳቸውን የስልክ መልዕክቶች በፎረንሲክ እያስመረመረ መሆኑን ተናግሯል። በእጃቸው ላይ የኢትዮጵያ ህዳሴ እርቅና አንድነት የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሚልና ሌሎች የፖለቲካ ሰነዶችን ማግኘቱን የገለፀው መርማሪ ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን … [Read more...] about ልደቱ የ98 ምርጫ ወቅት ከህወሓት ደኅንነት ሽጉጥ መቀበሉን ለፍርድ ቤት አመነ