ስሙ የክህደት መጠሪያ ሆነ እንጂ የስሙ ትርጉም ግሩም ነው። ይሁዳ የሚለው ቃል በእብራይስጥም “ይሁዳ” ማለት ነው፤ “ያዳ” ነው ሥርወ ቃሉ ይላሉ የሙያው ባለቤቶች። ይህ ደግሞ ትርጉሙ “ማመስገን” ማለት ነው። በግሪክም ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው - “የተመሰገነ”፣ “ምስጉን” ማለት ነው። “የአስቆሮቱ” የሚለው ቃል ደግሞ የክፋት መጠሪያ አይደለም። በተለምዶ “የአስቆሮቱ ይሁዳ” በማለት ከሃዲዎችን ስንጠራቸው “አስቆሮቱ” የይሁዳ የክፋት ማዕረግ ይመስለናል። ሊቃውንቱ እንደሚሉን ከሆነ ትርጉሙ “የኬሪዮት ሰው” ወይም “የአራዳ ልጅ” እንደ ማለት ነው ይላሉ። ስለዚህ በከሃዲነቱ ባናውቀው ኖሮ “ተመስገን ያራዳ ልጅ” ብለን እንጠራው ነበር። ስሙ ግን ከግብሩ ፍጹም የራቀ ነው፤ እንዲያውም ተጻራሪ። ይሁዳ ከሃዲ ብቻ አይደለም፤ ማሳካት የሚፈልገው ዓላማ ያለውና የሚያደርገውን … [Read more...] about የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
tamrat layne
“ብቃት የለኝም፤ የሥነምግባር ችግር አለብኝ” ታምራት ላይኔ
https://youtu.be/fWtD-akMhSU?t=400 ታምራት ስለ ራሱ የሥነምግባር ጉድለት በአደባባይ የተናገረውን ቪዲዮውን በመጫን ይመልከቱ የወንበዴው ቡድን አምበል በሆነው መለስ ዜናዊ በያኔው “ፓርላማ” ፊት ሌብነቱ ተዘርዝሮ እና የሥነምግባር ብልሹነቱን አምኖ ከፓርላማው የተባረረው ታምራት ላይኔ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን እየተመኘ ነው። ከበረኻ ወዳጆቹ እነ ሰዬ አብርሃ ጋር በመሆን ነው በዚህ ሥራ የተጠመደው። ታምራት በመለስ ትዕዛዝ በፓርላማው ፊት ሌብነቱን፣ ሥነ ምግባሩ የጎደፈና መሪ መሆን የማይችል መሆኑን አምኖ መባረሩ ትክክል ነው በማለት ተቀብሎ የላሰውን ስኳር ሳያጣጥም ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ነበር የተወረወረው። ጥያቄያችን ያኔ በዚህ መልኩ ብቃት የለኝም፣ ሥነ ምግባሬ ለተቀመጥኩበት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር … [Read more...] about “ብቃት የለኝም፤ የሥነምግባር ችግር አለብኝ” ታምራት ላይኔ