ስሙ የክህደት መጠሪያ ሆነ እንጂ የስሙ ትርጉም ግሩም ነው። ይሁዳ የሚለው ቃል በእብራይስጥም “ይሁዳ” ማለት ነው፤ “ያዳ” ነው ሥርወ ቃሉ ይላሉ የሙያው ባለቤቶች። ይህ ደግሞ ትርጉሙ “ማመስገን” ማለት ነው። በግሪክም ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው - “የተመሰገነ”፣ “ምስጉን” ማለት ነው። “የአስቆሮቱ” የሚለው ቃል ደግሞ የክፋት መጠሪያ አይደለም። በተለምዶ “የአስቆሮቱ ይሁዳ” በማለት ከሃዲዎችን ስንጠራቸው “አስቆሮቱ” የይሁዳ የክፋት ማዕረግ ይመስለናል። ሊቃውንቱ እንደሚሉን ከሆነ ትርጉሙ “የኬሪዮት ሰው” ወይም “የአራዳ ልጅ” እንደ ማለት ነው ይላሉ። ስለዚህ በከሃዲነቱ ባናውቀው ኖሮ “ተመስገን ያራዳ ልጅ” ብለን እንጠራው ነበር። ስሙ ግን ከግብሩ ፍጹም የራቀ ነው፤ እንዲያውም ተጻራሪ። ይሁዳ ከሃዲ ብቻ አይደለም፤ ማሳካት የሚፈልገው ዓላማ ያለውና የሚያደርገውን … [Read more...] about የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
yared tibebu
“ዳፍንታም” ነኝ – ያሬድ ጥበቡ
“ጆሊው” ጀቤሳውን በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊነቷና “ኦሮማዊነቷ” ተምታቶባት ከነበረችው ቤተልሔም ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ አዳመጠሁት። ስለ ቤተልሔም ለመናገር ባይሆንም ዋናው ሃሳቤ፤ ቤተልሔም ከለውጡ በፊት ኦሮሞነቷን በአቅራቢያዋ የነበሩ ሰዎች እንኳን አያውቁም ነበር። በኋላ ግን እነ ጃዋር አራት ኪሎን በቅርብ ርቀት ማየት ሲጀምሩ “አኝከህ አኝከህ ወደ ወገንህ ዋጥ” ተብሎ በአማርኛ የተነገረው ብሒል ትዝ አላትና “ልትውጥ” ወደ “ዘመዶቿ” ዞር አለች። “ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ ቢኖር ኦሮሞ እንደሚሆን እርገጠኛ ነኝ” ብላ አምላክን ኦሮሞ አድርጋውም እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ወደ ጉዳዬ ስመለስ … ቃለ ምልለሱ ሲጀመር የሚታየው አጅሬው ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) በዚያ አዛውትነቱ ነጭ ሸሚዙን ከደረቱ አጋማሽ ድረስ ከፈት አድርጎ ከውስጡ ካኔተራው እየታየ … [Read more...] about “ዳፍንታም” ነኝ – ያሬድ ጥበቡ